ዳኒሽ (HIKMA)
120 subscribers
204 photos
26 videos
1 file
94 links
አሰላሙ አለይኩም🖐🤝
የተወደዳችሁ የቻናላችን ተከታታዮች በአሏህ ፍቃድ እናንተን እያዝናናን ኢስላማዊ እውቀቶችን እና ጠቃሚ ምክሮችን እናስተላልፋለን🙏

ለማንኛውም አስተያየት እና መልእክት💌
👇
@A2yshd

@ethiodanishbot
Join ለማድረግ
Download Telegram
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ

👈‏قال ﷺ :

"أكثروا الصلاة علي يوم الجمعة وليلة الجمعة فمن صلى علي صلاة صلى الله عليه عشراً"
@Ethio_danish
قال المحدث الألباني : حسن

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል;

«በጁምዓ ለሊትና በጁምዓ ቀን ላይ በኔ ላይ ሰላዋት ማውረድ አብዙ፣ በኔ ላይ አንድ ሰላዋት ያወረደ አላህ በእርሱ ላይ አስር ሰላዋት ያወርድበታል።»
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
#ተጨማሪ_ኢስላማዊ_እውቀቶችን_ከፈለጉ
@Ethio_danish
@Ethio_danish
@Ethio_danish
Forwarded from ዳኒሽ (HIKMA) (TOW A YSHD)
🤲🤲ዱዐ🤲🤲

🤲ዱዐ:- ሁሉም ፍጡር ከአላህ ከጃይ ነው። አላህ ዘንድ ያለው ያስፈልገዋል። እርሱ(አላህ) ደግሞ ከፍጡራኑ የተብቃቃና ሀብታም ነው። አላህ የሚለምነውን ይወዳል። እሱን በመለመን ችክ ባዮቹንም ባሮች ይወዳል። ለዚህም ነው ሶሀቦች ለትንሽ ነገር ቢሆን እንኳን አላህን ከመለመን የማይቦዝኑት።

የዱዐ ደረጃ፡- ዱዐ አላህ ዘንድ ትልቅ ደረጃ አለው፤ የአላህን ቀደር ሊመልስ/ሊቋቋም/ ይችላል። ዱዐ ከእንቅፋቶች ከፀዳና ቅድመ ሁኔታው ከተሟላ ተቀባይነት አለው። አላህ(ሱ.ወ) እንዲህ ይላል «ጌታችሁም አለ ለምኑኝ እቀበላኋለው፤እነዛ እኔን ከመገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ጀሀነም ይገባሉ» 46፡60
«ባሮቼ በጠየቁህ ጊዜ እኔ ቅርብ ነኝ፣ የለማኝን ፀሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ…»02

ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ «ዱዐ እርሱ እራሱ አምልኮ ነው»
ቲርሚዚና ሌሎችም ዘግበውታል

በሌላ ቦታ ነቢዩ ሙሀመድ(ሰ.ዐ.ወ) በዘገቡት ሀዲስ «ዱዐ የኢባዳ መቅኒ ነው» ብለዋል።

ዱዐ በኢስላም ቁርዐንን ከማንበብና ከዚክር በመቀጠል በላጭ የሆነ ኢባዳ ነው።

🤲የዱዐ አይነቶች፡- ሁለት ሲሆኑ አምልኮታዊ(ሶላት፣ፆም…) ዱዐና የልመና(ጥያቄ) ዱዐ ይባላሉ። ለዱዐ ተቀባይነት የሚረዱ መስፈርቶች፡-
1.ግልፅ ምክንያቶች፡- ሰደቃ፣ውዱዕ፣ ሶላት፣ ወደ ቂብላ መዞር እጅን ማንሳት፣ አላህን በተገቢው ሁኔታ ማወደስ፣ በነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሶለዋት ማውረድ፣ ወንጀሉን ማመን፣ የአላህ ስሞችን እያነሱ መለመን… የመሳሰሉትን መጠቀም ናቸው።
2. ድብቅ ምክንያቶች፡- እውነተኛ ተውበትን ማስቀደም፣ በበደል የወሰዱትን ነገር መመለስ፣ ምግብን መጠጥን መኖሪያን ማሳመርና ከሀላል ማድረግ፣ ወንጀልና ከአጠራጣሪ ነገሮች መራቅ፣ ዱዐን ከልብ ማድረግ፣ በአላህ መተማመን፣ የተስፋ ስሜት ማዳበር፣ ወደ አላህ መጠጋት፣ ራስን ማስተናነስ፣ ችክማለት፣ ወደ አላህ መጠጋት፣ ሁሉን ነገር ወደርሱ ማስጠጋትና ከሌላው ተስፋ መቁረጥ ናቸው።

የዱዐ ወቅቶች፡- በለሊቱ መጨረሻ ላይ፣ በአዛንና በኢቃማ መካከል፣ ከውዱዕ በኋላ፣ በሱጁድ ውስጥ፣ ከሶላት ማሰላመት በፊት፣ ከሶላቶች በኋላ፣ በቁርዐን ማኽተሚያ ወቅት፣ ዶሮ ሲጮህ፣ ሙሳፊር ሰው፣ የተቸገረ ሰው፣ የአባት ዱዐ ለልጅ፣ ሙስሊም ወንድሙ በርቀት የሚያደርግለት፣ ከጠላት ጋር ሲገናኙ፣ በጁሙዐ ኩጥባ ሶላቱ እስኪያልቅና ከአሱር በኋላ፣ በረመዳን
በፊጥርና በሱሁር ወቅት፣ ለይለተል ቀድር፣ የአረፋ ቀን ናቸው።

🖼የዱዐ ቦታዎች፡- የዱዐ ቦታዎችን በተመለከተ በሁሉም መስጂዶች በተለይ ከካዕባ አጠገብ፣ መቃሙ ኢብራሂም ዘንድ፣ ሶፋና መርዋ ላይ፣ በሐጅ ጊዜ (በዐረፋ፣ በሙዝደሊፋና፣ በሚና) ላይ፣ ዘምዘምን በሚጠጡበት ጊዜ ናቸው።

#ዱዐን_ተቀባይነት_የሚያሳጡ_ነገሮች፡- በዱዐው ከአላህ ጋር ሌሎችን መለመን(ሽርክ)፣ በልመናው ውስጥ ዝርዝር ነገሮችን መጥቀስ፣ በራሱ ላይ ወይም በሌላው ላይ ዱዐ ማድረግ (በግፍ)፣ ለወንጀልና ዝምድናን ለመቁረጥ ዱዐ ማድረግ፣ ከፈለክ አድርግልኝ ስትፈልግ ማረኝ ማለት፣ መሰላቸት፣ በተዘናጋ ልብ ዱዐ ማድረግ፣ አላህ ፊት ተገቢውን ስርዐት አለመያዝ፣ በነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሶለዋት አለማውረድ፣ በግድ በግጥም መልክ ለማድረግ መልፋት፣ ድምፅን ከመጠን በላይ ማጉላት… የመሳሰሉት ናቸው።

ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) ቲርሚዚይ በዘገቡት ሀዲስ እንዲህ ብለዋል« ማንም ሙስሊም በወንጀልና ዝምድናን በመቁረጥ ባልተቀላቀለበት ዱዐ ካደረገ ከሶስት ነገሮች አንዱ ይሰጠዋል- የለመነውን ነገር በቀጥታ፣ ወይም ወደ አኺራ ተላልፎ ሊቀመጥለት፣ ወይም እንደ አቅሟ ሊያገኘው የነበረውን ክፉ ነገር በመከላከል ነው»

#ከዱዐ_መኩራራት፡- አላህ በርሱ ላይ የሚኩራሩትንና ተብቃቂ ለመሆን የሚሹትን በተለያዩ ቦታዎች ያስጠነቅቃል።
«…እነዛ እኔን ከመገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ጀሀነም ይገባሉ» 46፡60

ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) ኢብኑ ማጃህ በዘገቡት ሀዲስ «አላህ ልመናውን የተወን ሰው ይቆጣበታል» ብለዋል።

#በዱዐ_ድንበር_ማለፍ፡- በመጨረሻው ዘመን ሰዎች በዱዐ ላይ ድንበር እንደሚያልፉ ነቢዩ አስጠንቅቀዋል ይኸውም በአሁን ዘመን በመታየት ላይ ይገኛል።

ለምሳሌ፡- ድምፅን ከፍ አድርጎ መለመን፣ በጋራ ዱዐ ማድረግ፣ ቦታና ጊዜውን መወሰን… የመሳሰሉት ይገኙበታል ከሁሉ የከፋው ደግሞ ከአላህ ውጪ ያሉ አካለትን መለመን ሲሆን ነቢዩ እንዲህ ሲሉ ያስጠነቅቃሉ፡- «መለመን ስትፈልግ አላህን ብቻ ለምን፣ እርዳታ ብትፈልግ በአላህ ብቻ ተረዳ» ቲርሚዚ ዘግበውታል

አላህን በስርዐት ከሚገዙት ዱዐቸውንም ከሚቀበላቸው ባሮች ያድርገን።
አላሁመ አሚን!
#ተጨማሪ_ኢስላማዊ_እውቀቶችን_ከፈለጉ
@ethio_danish
@ethio_danish
@ethio_danish
@ethio_danish