ዳኒሽ (HIKMA)
120 subscribers
204 photos
26 videos
1 file
94 links
አሰላሙ አለይኩም🖐🤝
የተወደዳችሁ የቻናላችን ተከታታዮች በአሏህ ፍቃድ እናንተን እያዝናናን ኢስላማዊ እውቀቶችን እና ጠቃሚ ምክሮችን እናስተላልፋለን🙏

ለማንኛውም አስተያየት እና መልእክት💌
👇
@A2yshd

@ethiodanishbot
Join ለማድረግ
Download Telegram
#ረመዳን የራህመት ወር - የረመዳን መድረስ አስመልክቶ ታላቅ ምክር ከሸይኽ ሳሊሕ ፈውዛን:- "አንድ ሙስሊም አላህ ለረመዳን ወር እንዲያደርሰው እና አድርሶትም ፆሙ ላይ፣ ስግደቱ ላይ እና ሌሎች አምልኮዎች ላይ አላህ እንዲያግዘው አላህን መለመን አለበት። ምክንያቱም ይህ ወር በአንድ ሙስሊም ህይወት ዕድል ነው። ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:- "ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የፆመ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።" ስለዚህ ይህ ወር ላይመለስ የሚችል ዕድል ነው። ሙስሊም የሆነ ሰው ረመዳን ሲመጣ ይደሰታል፣ ተስፋም ያደርጋል፣ በደስታ እና በጉጉት ነው የሚቀበለው፣ እድሉን በደንብ በአላህ ትዕዛዝ ላይ ነው ሚያሳልፈው። ሌቱን በመቆም፣ ቀኑን በመፆም፣ ቁርዓን በመቅራት እና አላህን በማስታወስ ነው የሚያሳልፈው። ትልቅ ዕድል ነው። ነገር ግን አንዳንዶቹ ረመዳን ሲደርስ አዘናጊ ፕሮግራሞችን፣ ፊልሞችን፣ ዝባዝንኬዎችን፣ ውድድሮችን የሚያዘጋጁ አሉ። እነዚህ የሸይጣን ወታደሮች ናቸው። ሸይጣን ነው ለዚህ ተግባር ያዘጋጃቸው። አንድ ሙስሊም የሆነ ሰው ደግሞ ከነዚህ ሰዎች እና ከተግባሮቻቸው መጠንቀቅ አለበት። ረመዳን የፍንጥዝያ፣ የጨዋታ፣ የፊልም፣ የውድድር ወር አይደለም።" ያአላህ የረመዳንን ወር በሰላም አድርሰን፣ ደርሶም ከሚጠቀሙበት አድርገን🤲🤲🤲🤲 አሚን! ያረብ! #ዝክረ ረመዳን «ወደ ኸይር(መልካም) ያመላከተ እንደሰሪው ነው እና ይህንን ታላቅ ምክር እርሶ ጋር እንዲቀመጥ ብቻ አይፍቀዱ ለሌሎችም ያስተላልፉ!

@ethio_Danish
@ethio_Danish
@ethio_Danish
@ethio_Danish
@ethio_Danish
@ethio_Danish
#ረመዳን😍


ረመዳን~ቁርአን የወረደበት ወር

ረመዳን~የጀነት በሮች የሚከፈቱበት
የጀሀነም በሮች የሚዘጉበት ወር

ረመዳን~ሰይጣኖች የሚታሰሩበት ወር
ረመዳን~ከ1ሺህ ወር የምትበልጥ ሌሊት
ያለበት ወር

ረመዳን~ከምንጊዜውም በበለጠ ዚክርና
ቁርአን የሚቀራበት ወር

ረመዳን~'ሱንና' የሆኑ ነገሮች 'የፈርድ'
ግዴታ ደረጃ የሚሆኑበት _ዑምራ
መስራት እንደ ሀጅ የሚቆጠርበት ወር
ረመዳን~አላህ ለኔ ያለው ስራ ፆም
ከምንጊዜውም በበለጠ የሚከናወንበት ወር ቁርአን አንድን ባሪያ እንደሚያማልድ ፆምም አማላጅ እንደሚሆንም ተወስቷል

ረመዳን~አንድ ባሪያ አላህ ከፈቀደለት
ነገሮች ራሱን በማቀብ አላህን ፍራቻ
'ተቅዋ' የሚያገኝበት ወር

ረመዳን~ምንዳቸው ክፍያቸው ገደብ
ከሌላቸው ሰራዎች መካከል አንዱ
የሆነው ፆም; ወር ሙሉ የሚከናወንበት

═════ ═════
• እነዚህና ሌሎች መልካም ነገሮች
የሚገኝበት ወር በመሆኑ የአላህ መልክተኛ
ﷺ ጅብሪል ዐለይሂሰላም መጥቶ [አንድ ባሪያ የረመዳንን ወር አግኝቶ ወንጀሉን
ሳይማር ረመዳን የወጣበት እድለ-ቢስ ይሁን አሚን በል ሲላቸው ᐸአሚን>
ብለዋል
•••••••••••

አላህ በዚህ በተከበረ ወር መልካም ነገር ከሚሸምቱና ከእሳት ነፃ ከሚላቸው
ያድርገን !,,, ኣሚን