EECMY Children Ministry: MY Sunday School
762 subscribers
904 photos
14 videos
171 links
MY Sunday School is the official page of EECMY Children Ministry.

Wholistic Growth For Our Children!

Access Sunday School learning materials at www.mysundayschool.org
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ዛሬ መግለጫ አውጥተዋል።

መግለጫቸው ፤ በአውሮፓ ኅብረት እና በአፍሪካ፣ በካሪቢያንና በፓስፊክ ሀገራት መካከል የተፈረመውንና የሳሞአ ስምምነት በመባል የሚታወቀውን የንግድና የኢኮኖሚ አጋርነት ስምምነት የተመለከተ ነው።

ጉባኤው ስምምነቱ ተካተውበታል ያላቸውን ጎጂ ሀሳቦች በዝርዝር አስፍሯል።

ከነዚህም መካከል ፦

- በስምምነቱ አንቀፅ 36.2 ላይ የተጠቀሰው የወሲብና የተዋልዶ ጤናና መብቶች" ("Sexual and Reproductive Health and Rights") የሚለው ሐረግ በቀጥታ ፦
* #ከግብረሰዶም መብቶች፤
* ከፆታ መቀየር፤
* ከውርጃ፤
* ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርትና ግልሙትናን ሕጋዊ ከማድረግ በቀጥታ የተያያዘ መሆኑ በአውሮፓ ፓርላማና በዓለም የጤና ድርጅት የመረጃ ምንጮች ላይ በግልፅ መቀመጡ፤

- በስምምነቱ የአፍሪካ ፕሮቶኮል አንቀፅ 40.6 ላይ በአህጉሪቱ ለሚገኙ ልጆችና ታዳጊዎች ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት (Comprehensive Sexuality Education) የተባለ እጅግ አደገኛ ኢግብረገባዊና ልቅ የወሲብ ትምህርት እንዲማሩ አስገዳጅ መሆኑ ለዚህም በዩኔስኮ የተዘጋጀውና እጅግ አደገኛ ይዘት እንዳለው የተረጋገጠው መተግበርያ "International Technical Guidance on Sexuality Education” በስም ተጠቅሶ መቀመጡ፤

- የፆታ ትንኮሳን (gender based violence) ማስቀረት በሚል በጣም አሻሚ የሆነ ግብረሰዶማዊ አስተሳሰቦችን ለማስረፅ እንዲረዳው በሰነዱ በበርካታ ክፍሎች ውስጥ " አካታች " (inclusive) በሚሉ ቃላት ተሸፍኖ እንዲገባ የተደረገ መሆኑ፤

- በበርካታ ሥፍራዎች የተጠቀሰው "Gender" የሚለው ቃል ወንድና ሴት ተብሎ እንደሚተረጎም በስምምነቱ በግልጽ ባለመቀመጡ ይልቁንም በርካታ ጾታዎች እንዳሉ በማስመሰል ሀገራትን የሚያደናግሩባቸው እንደ (sexual orientation እና gender identity)ን የመሳስሉ ግብረሰዶማዊ አስተሳሰቦችን የያዙ ዶክመንቶች በስም ተጠቅሰው በስምምነቱ ውስጥ መካተታቸው፤

- ስምምነቱ የወላጆችን መብት የሚጥስና የኢትዮጵያዊ ቤተሰብ እሴቶችን አደጋ ላይ የሚጥሉ አንቀፆችን የያዘ ስለመሆኑ በሰነዱ ላይ ከተደረገ የኤክስፐርቶች ጥልቅ ጥናት ተረድተናል...  የሚሉት ይገኙበታል።

ጉባኤው በነዚህ እና ሌሎች ጎጂ ምክንያቶች ፦

መንግስት የሳሞአ የንግድና የኢኮኖሚ የአጋርነት ስምምነትን በርካታ ጎጂ ጎኖች እንዳሉት በማመን ከዚህ ስምምነት #ኢትዮጵያ ራሷን እንድታገልል በማድረግ መንግስታዊ ኃላፊነቱንና አደራውን በተግባር እንዲወጣ በአጽንኦት ጠይቋል።

የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና በሥሩ ያሉ የሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች የስምምነት ሰነዱ ውስጥ በዝርዝር የቀረቡትን በተለይም ፦
° ከሰብኣዊ መብቶች፣
° ከወሲባዊና የተዋልዶ ጤናና መብቶች፣
° ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት፤
° አካታችነት እና መሰል በሰነዱ የተካተቱ አንቀጾች ወይም ይዘቶች ከግብረሰዶማዊነትና ጾታን ከመቀየር እንዲሁም ከልቅ ወሲብና ከውርጃ ጋራ በቀጥታ ተያያዥነት ያላቸው ጽንስ ሃሳቦች መሆናቸውን በመረዳት ይህንን እጅግ አደገኛ ስምምነት ባለማጽደቅ ህዝባዊና ታሪካዊ አደራውን እንዲወጣ በአጽንኦት ጠይቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ስለ " ሳሞአ ስምምነት " ያዘጋጀው ሰፊ እና ዝርዝር ዘገባ በዚህ ይገኛል ፦ https://t.me/tikvahethiopia/84172

@tikvahethiopia