ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.48K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ❤️🇪🇹❤️
ከ“እናት ዓለም ጠኑ” ቃለ ተውኔት የተወሰደ
(ብላቴን ጌታ ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን)
አፋዊ ሆንን!
ሕያዊ ሳንሆን አፋዊ!
ቃለ ሕይወት ሳንሆን፣ ብኩን ቃለ-አፍ ብቻ!
እንጂ! ቤታችን አንድ ነው፡፡
“ቤት” ብለን ለልጆቻችን ያወረስናቸው
ፍቅር የሞተበት ቤታችን! አንድ ነው፡፡
አባቶቻችን ልባም
እኛ አፋም፡፡
እሳት ዐመድ ወለደ ሆንን እንጂ- ቤታችንስ አንድ ነው፡፡
ነፃነት ብለን ባርነት
ሕይወት ብለን ሞት - ለልጆቻችን አወረስን፡፡
ብኩን ቃለ-አፍ!
ህይወት ብለን ንፍገት
ጀግንነት ብለን ፍርሃት - ከተብናቸው!
በወረረን ባዕድ ሞት ማግስት፣
አዲስ ተስፋ ለተራበ ህልውና፤ አዲስ የሃገር ውስጥ ሞት!
ለአዲስ ትንሳዔ በቃተተ ዓይን
አዲስ መቃብር ከፈትን!
አፋዊ! ጋዜጣዊ!- ብኩን የሃሰት ነፃነት ዘረጋን!
ልጆቻችን በተስፋ ልክፍት ቃ‘ተው መከኑ!!
አንዲት የዱር አውሬ - በምትወልድበት ሰሞን
ልጇን ትበላለች ይላሉ - ምጥ የበዛባት እንደሆን
ልጆቻችንን በላን!
ትናንት የነፃነትን ምጥ ከአፋፍ መንግለን
የጥላቻ ውርስ አቆይተን
አፋዊ ነፃነት አውርሰን
“ምነው?” ባሉ! ልጆቻችንን ገፍተን
አፋዊ እኩልነት- አፋዊ ክትባት ከትበን
ፍርሃት ወርሰን - ፍርሃት አውርሰን
ጥላቻ ወርሰን - ጥላቻ አውርሰን
ሕያው ሳንሆን አፋዊ
ቃለህይወት ሳንሆን ብኩን ቃለ አፍ
እንጂ ቤታችንስ አንድ ነው፡፡
ትናንት የነፃነትን ምጥ ከአፋፍ መንግለን
የጥላቻ ውርስ አቆይተን
አፋዊ ነፃነት አውርሰን
“ምነው?” ባሉ! ፈረድንባቸው!
በልጆቻችን ፈረድንባቸው!!
የህይወት ጣሙን ሳይሆን - ወጉን
የፍቅር ወዙን ሳይሆን - ስሙን
የነፃነት ግብሩን ሳይሆን - ተረቱን
እንዳወረስናቸው ባወቁብን
በነቁብን
ፈረድንባቸው፡፡
ፍቅራችን የሻል ወርቅ፣ የነጭ ጓንቲ፡ የተከፈለ ፎቶግራፍና የድግስ ጃዝ
እንጂ የልብ እውነት፣ የእሳትና አበባ ጉዳይ አለመሆኑን ባወቁብን፣
በነቁብን፤ ፈረድንባቸው፡፡
የዕውቀት ሙቀታቸውን
በበድን ቅዝቃዜያችን
ቸስቸስ አድርገን - አቀዘቅዝናቸው!
መንፈሳቸውን አኮላሸናቸው፡፡
አበው ያወረሱንን ሰብዓዊ የፍቅር ግለት በውስጣችን አክስለን
እንደመንጋ በዘፈቀደ መፈቃቀዳችንን
በልተን ጠጥተን - ጓሮ እንደመዞር መገናኘታችንን
ሆድሞልተን - ሜዳ እንደመውጣት መፈቃቀዳችንን
ፍቅርን እንደዐቃቢት ቃል ኑዛዜ፣ ምላሳችን ላይአሻግተን ማነብነባችንን
ልጆቻችን ነቅተው ባዩብን - ፈረድንባቸው!
አዎ! - እንጂ ቤታችንስ አንድ ነው፡፡
እኛ ፈላስሞቹ
እኛ ከተሜዎቹ
አዋጅ ነጋሪዎቹ
የዘመናዊ ስልጣኔ ሸቃጮቹ
ታደምንበት!
እኛ የአውሮፓ አደባባይ ጓሮ ቁራዎቹ
የየዩኒቨርስቲዎቻቸው ምሩቃኖቹ
ምሁራኑ!
የጉድ አዋጆቻቸው ተክሎች እኛ!
እኛ ታደምን!
የዘመኑ ድልድይ መሆናችን ቀርቶ - የዘመኑ አዘቅት
ናዳ ግድግዳ ሆነን - በብዙሃኑ ድል ተገደገድንበት!
ጨለማው ቀናችን!
ጭጋጉ ፀሃያችን!
ምሽቱ ንጋታችን ሆነንና ታደምንበት!
በነፍሳችንም አደፍን!
ፍቅር ደከመንና - የቁም ሞት ተወራረስን
ከልጆቻችን ዋጋ ይልቅ- የቀብራችንን ዋጋ አከበድን
የህይወት ቀርቶ - የመቃብር አምላኪዎች ሆንን
እንጂ….!
ፍቅር የሞተበት- ቤታችንስ ያው አንድ ነው!
ዱሮ ዱሮ፤ ሰው በሰው ነው አሉ ራሱን ፈልጎ ሚያገኝ
የራሱን ጉድለት፣
የራሱን ማንነትና ምንነት የሚረዳው
የሌላውን ቀርቦ መርምሮ አጥንቶ ነው ይባላል
እኛ ግን በተቀራረብን ቁጥር እንተጣጣለን
እንጠፋፋለን
አንገናኝም
በተጠጋጋን ቁጥር እንራራቃለን
የቃላት ክምችት ኳኳታ ብቻ ነን
የግስ ግሳንግስ እርባታ ቀፎዎች
ለዚህም ነው እንደአሸዋ ባህር
በቃላት ውጥንቅጥ! በቋንቋ ሽብር
በግስ ግሳንግስ ተጥለቅልቀን!
በቁምና በቅዠት አፋዊ ውዝግብ ስንንኳኳ የቀረን!
ላንግባባ! ቤታችን በቃላት ግሳንግስ ታጥኖ ታፍጎ
ለህሊናችን መተናፈሻ ቀዳዳ የጠፋብን ለዚሁ ነው
በዘፈቀደ ከየፍልስፍናው የአንቡላ ጭልጭ ፉት ያልነውን ጠራዝ ነጠቅ
የቋንቋ ብልጭታ ሌትና ቀን እያንባቧቸርን ስናስጎነብት አንድያችንን
ተጠፋፋን
ዓይናችንም እንደ አንደበታችን ግሳንግስ የደም ፍትወትን ለመደ!
የአይን ወረት ጭዳ የሰሰቀኑን ሱስ ለመደ!
ዓይናችን ጭምር!
የሰው ትራፊ - የሰው ዕድፍ - የሰው ጥንብ ማስተዋል ምሳችን ሆነ!
የሰዉን ጣር እንባ መሻት- የሰው ሰቀቀን ማነፍነፍ - ውሎ አድሮ
ባህላችን ሆነ!
ሌላው ካላደፈ የኛ ንፅህና!
ሌላው ካልተጎሳቆለ የእኛ ጥጋብ ጎልቶ አልታየን አለ!
ዓይናችንን የደም ፍትወት - የሰው ሰቀቀን ጭዳ አስለምደን
አይለከፉት ልክፍት ተለከፍን!
አዎን ፈራን!
የነፍሳችንን አንደበት ዘጋን!
ሰብአዊነታችንን ራሳችን - ከውስጣችን ነደን አክስመን
ሰው የምንለው ሰብአዊ ፍጡር ቢጤአችን
እያደር ከቶም አልገባን አለ!
በዘልማድ ብቻ! ሰውን ሰው - ውሻን ውሻ ብለን
አሜን ብለን እንቀበል እንጂ!
ሰው የሚባል - ረቂቅ ሰብአዊ ፍጡር
ሰው የሚባል - የእግዚአበሄር ተፈጥሮ ተዓምር
ከቶም አልገባን አለ!
እንጂ ቤታችንስ አንድ ነው!
ፍርሃት አስገብተን
ፍርሃት ፀነስን
በቁማችን ፍቅር ሞቶ
በቁማችን ህያውነት ሞቶ
ፍርሃት ባርነት
አፍአዊ ንፍገት
ብካይ ፀነስን
ብካይ!
ከዘመን ዘመን አንሰን
ቁልቁል አደግን
በመንፈስና በባህርይ አይጥ አከልን!
አይጥ አክለን
የነገን ተስፋ
የልጆቻችንን ተስፋ ሰርስረን
ቦርቡረን - ገዝግዘን በላን!
የሀፍረት እድሜ እርሻችንን ጨርሰን
ይኸው በነገው ትውልድ እድሜ ሰርገን
የልጆቻችንን ተስፋ በቁም ገንዘን በላን!
ብካይ ፀነስን
ፍርሃት ፀነስን
አፋዊ ሆንን!
ያም ሆኖ! ለልጆቻችን ሕይወት ብለን ያወረሰናቸው
ፍርሃት የሰፈነበት ቤታችን! ያው አንድ ነው!
ፍቅር የሞተበት
ብካይ የነገሰበት
ሕይወት ብለን ያወረስናቸው ወህኒ ቤታችን! ያው አንድ ነው!
አዎ እንጂ! ቤታችንስ አንድ ነው!
source #Tesfa Zion fb account
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1) የአለማችን ረጅሙ ህንፃ የሚገኝባት ሀገር የቱ ነው? ሀ) አሜሪካ ለ) ኢንግሊዝ ሐ) ዱባይ 2)የአባይ ተፋሰስ ሀገራት በመባል የሚታወቁት ሀገራት ስንት ናቸው? ሀ) 9 ለ)8 ሐ)11 3) የትኛው ድርጅት ነው በአለማችን ትልቁ ወንዝ የሚጠራው? ሀ) አማዞን ለ) ያሆ ሐ) Google 4) ከእነዚህ አንዱ ረጅም ነው ? ሀ) ቀጭኔ ለ) ዝሆን ሐ) ነብር 5) የትኛው Planet ነው ለፀሀይ ቅርብ?…
የትላንቱ ጥያቄዎች መልስ
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

1) ሐ ዱባይ

በዱባይ የሚገኘው ቡርዲ ከሊፋ በበመባል ሚታወቀው የአለማችን ረጅሙ ህንፃ ነው ፡፡ With the total height of 829.8 m (2,722 ft)

2) ሐ 11 እነሱም Tanzania,
Uganda , Rwanda, Burundi , the Democratic
Republic of the Congo , Kenya , Ethiopia , Eritrea,
South Sudan, Republic of the Sudan, and
Egypt.

3) ሀ አማዞን ሲሆን በደቡብ አሜሪካ የሚገኝ ትልቁ የውሃ ሃብት ነው ፡፡ ከአባይ ወንዝም በመቀጠል ረጅሙ ወንዝ በመባል ይታወቃል ፡፡

4) ሀ ቀጭኔ ምንም ክርክር የሌለው ቁመተ ለመለሎ እና አንገተ ብርሌ (ረጅም) የሆነች እንስሳ ናት ፡፡

5) ለ ሜርኩሪ ሜርኩሪ ትንሿ planet እና ለsolar system ለ ፀሀይ ቅርብ የሆነች planet nat .

* The smallest planet in our solar system and
nearest to the Sun, Mercury is only slightly larger
than Earth's Moon.*


(Source:- Wikipedia , https://solarsystem.nasa.gov/planets/mercury/overview/ )

መላሾች ፡- ብዙ መላሻች አግኝተናል ነገር ግን ከብዙ መላሻች ውስጥ ከ1-3 ያሉት

1) 5/5 የመለሱት🥇
#auser በሚል unknown idedentity 3 ሠው

# @Bemnetf (Tewulgn)
#ምን ይሻላል ለሰው ልጅ
#Kuma .e
#ምን ይሻላል ለሰው ልጅ
2) 4/5 የመለሡት 🥈

#Eyu @Ambesaye87
#Tekee @lmTeke
#Tesfa boy @HopeTGN
#Haile @haileT19
#princess

3) 3/5 የመለሡት🥉
#Amir Aman

ለአብሮነታችሁ እናመሰግናለን
#Share
#invite