AddisWalta - AW
45.2K subscribers
41.8K photos
204 videos
20 files
16.6K links
This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.

For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
Download Telegram
እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያ ከዋልታ ቴቪ ሰኔ 28/2014
https://fb.watch/e3ziDDCNs0/
ምክር ቤቱ በምዕራብ ወለጋ በንጹሀን ዜጎች ላይ የደረሰውን ግድያ በፅኑ አወገዘ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሽባሪው የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በንጹሀን ዜጎች ላይ ያደረሰውን አደጋ በፅኑ አወገዘ።

አሸባሪው የሸኔ ቡድን በጸጥታ ኃይሎች በከፍተኛ ሁኔታ ጥቃት እየደረሰበት በመሆኑ ከጥቃቱ በመሸሽም በምዕራብ ወለጋ ንጹሀን ዜጎች ላይ አደጋ ማድረሱን ጠቅሷል።

በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ዞን ውስጥ የሚገኙ ንጹሀን ዜጎቻችን ላይ የፈጸመው ጭፍጨፋ በእጅጉ የሚወገዝ መሆኑን ምክር ቤቱ ገልጿል።

ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው አሸባሪ ቡድኑን ለማስወገድ መላው ሁሉም ዜጋ በተለይም የአካባቢው ማኅበረሰብ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመተባበር እስከመጨረሻው እንዲያስወግድ ጥሪ ቀርቧል፡፡
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) በሀገር ውስጥ ሊግ በሚጫወቱ ተጫዋቾች የሚዋቀሩ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል ለሚካሄደው የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ ውድድር ማጣርያ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አደረጉ።

ከደቡብ ሱዳን ጋር የቻን ማጣሪያ የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስቡን ይፋ አድርጓል።

በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የቻን የአፍሪካ አገራት ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ ሱዳን ጋር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ እንደሚጠብቀው ይታወቃል።

ሐምሌ 15 እና 24 ቀን 2014 ዓ.ም ለሚደረጉት እነዚህ ሁለት ጨዋታዎች የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጨዋቾች ጥሪ ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል፡፡

ግብ ጠባቂዎች ፋሲል ገብረሚካኤል፣ በረከት አማረ እና አላዛር ማርቆስ ጥሪ እንደተደረገላቸው ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ከተከላካዮችም ሱሌይማን ሀሚድ፣ ሄኖክ አዱኛ፣ ምኞት ደበበ፣ ያሬድ ባየህ፣ ሚሊዮን ሰለሞን፣ አስራት ቱንጆ፣ ረመዳን የሱፍ እና ጊት ጋትኩት በጥው ተካተዋል፡፡

ጥሪ የተደረገላቸው አማካዮች ጋቶች ፓኖም፣ከነዓን ማርክነህ፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣፣በዛብህ መለዮ፣ በረከት ደስታ፣ አማኑኤል ዮሐንስ እና መስዑድ መሐመድ ናቸው፡፡

አጥቂዎች ደግሞ ቸርነት ጉግሳ፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል፣ ዳዋ ሆቴሳ እና ብሩክ በየነ መሆናቸውን ተነግሯል፡፡

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾችም ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ.ም በፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥር ቀርቧል፡፡
ጨፌው አሸባሪው ሸኔን ለመደምሰስ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል አለ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ክልል መንግሥት አሸባሪው ሸኔን ለመደምሰስ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አጠናክሮ እንሚቀጥል ጨፌ ኦሮሚያ አስታወቀ።

አሸባሪው ሸኔ በቄለም ወለጋ ሐዋ ገላን ወረዳ በንፁኃን ላይ ባደረሰው አሰቃቂ ጭፍጨፋ ከፍተኛ ሀዘን የተሰማው መሆኑን ጨፌው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የሽብር ቡድኑ መንግሥት የሕዝቡን ሰላም ለማስጠበቅ ሲል እየወሰደበት ያለውን የተቀናጀ እርምጃ መቋቋም ሲያቅተው በሰላማዊ ዜጎች ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ እየፈፀመ ነው ብሏል።

ሕዝብ ከዚህ አደጋ፣ ስቃይ እና እንግልት ለማዳን መንግሥት እየወሰደ ያለውን እርምጃ አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጾ፣ በዚህ መንግሥት እየወሰደ ባለው እርምጃ በደረሰበት ሽንፈት ተቆርጠው የቀሩ የሽብር ቡድኑ አባላት በሕዝብ ላይ በድንገት አሰቃቂ አደጋዎችን እያደረሱ ነው ብሏል።

በመሆኑም ኅብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የአካባቢውን ሰላም መጠበቅ እና ማረጋገጥ እንደሚጠበቅበት እንዲሁም ተንጠባጥበው የቀሩ የአሸባሪው ሸኔ አባላት ላይ የማያዳግም እርምጃ ሊወስድባቸው እንዲገባም ጨፌው ጥሪ ማቅረቡን ኢብኮ ዘግቧል።

ጨፌ ኦሮሚያ አሸባሪው ሸኔ በንፁሃን ዜጎች ላይ ባደረሰው አሰቃቂ ጭፍጨፋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች ሀዘኑን ገልጾ ለሟቾች ቤተሰቦች እና ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለመላው ሕዝብ መፅናናትን ተመኝቷል።
ጠ/ሚ ዐቢይ በ39ኛው የኢጋድ ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ናይሮቢ ገቡ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ39ኛው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የኬንያ መዲና ናይሮቢ መግባታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታወቀ።

ዛሬ በሚጀመረው የመሪዎች አስቸኳይ ስብሰባ በጉባኤው መሪዎቹ በአካባቢው የሚከሰተውን ድርቅ ማሸነፍ በሚቻልበት ሁኔታ፣ በሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!
የአማራ ክልል መንግሥት በቄለም ወለጋ በሚኖሩ ንጹሃን ዜጎች ላይ በደረሰው ጭፍጨፋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለጸ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) የአማራ ክልል መንግሥት በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ውስጥ በሚኖሩ ንጹሃን ዜጎች ላይ በደረሰው ጭፍጨፋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለጸ።

የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ግዛቸው ሙሉነህ በሰጡት መግለጫ አሸባሪው የሸኔ ቡድን ዛሬም ሰላምን በሚሻው ንጹሃን ሕዝብ ላይ የሞት ጽዋን የሚያዘንብ የጥፋት መልአክ ሆኗል ብለዋል።

የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ወገኖች ሰላምን በማይሹ የሀገርና የሕዝብ ጠላቶች እንዲህ የመጠቃታቸው ብቸኛው ግብ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማንበርከክ አልመው መሆኑን ገልጸዋል።

በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ውስጥ በሚኖሩ ንጹሃን ዜጎች ላይ በደረሰው ጭፍጨፋ ለመላው ሕዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል።

ዛሬም ሆነ ነገ የዚህ ችግር ብቸኛው መፍትሔ የሕዝባዊ አንድነት ጠላት እና በጋራ ሰርቶ የማደግ ደመኛ የሆኑ ፀረ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የሆኑ ሁሉንም ኃይላት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንደ ሕዝብ በአንድነት ታግሎ ማሸነፍ ሲቻል ብቻ መሆኑን አመላክተዋል።

ይህን መሰል ጥቃቶችን በመፈጸም መሪር ሀዘን ላይ የሚጥሉ ጠላቶቻች ታግሎ ለማሸነፍና ለዚህ ጉዳይ ከሥሩ መፍትሔ ለመፈለግ ደግሞ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድ ድምጽ ይህን ድርጊት በመቃወም የመፍትሔው አካል ሊሆን ይገባል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያና ሱዳን ችግሮቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ተስማሙ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሱዳን ሉዓላዊ ሽግግር ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጄኔራል አብደል ፈታህ አል-ቡሁራን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያልተፈቱ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ተስማሙ፡፡

ሁለቱ መሪዎች በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በናይሮቢ እየተካሄደ ካለው 39ኛው የኢጋድ ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ተገናኝተው መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

በውይይቱ ሁለቱ ሀገራት በሰላማዊ መንገድ ሊሠሩባቸው የሚችሉ በርካታ የትብብር መሠረቶች እንዳሏቸው ተጠቅሷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሀገራቱ ትሥሥር ከየትኛውም መከፋፈል የሚበልጥ ነው ብለዋል።

"ሁለታችንም ያልተፈቱ ቀዳሚ ጉዳዮችን በሰላማዊ መንገድ በውይይት ለመፍታት ቁርጠኝነታችንን ገልጸናል" ሲሉም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከሱዳን ወንድም ሕዝብ ጋር በትብብር ለመልማትና በሰላም ለመኖር ፅኑ አቋም እንዳላትም አረጋግጠዋል።

የሱዳን የሽግግር መንግሥት ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጀኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን በበኩላቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር እንደ ወንድም በመወያየት በሀገራቱ መካከል ያሉ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ተስማምተናል ነው ያሉት።

ኢትዮጵያና ሱዳን ጠንካራ መሰረት ያለውና የቆየ ወዳጅነት ያላቸው እህትማማች ሀገራት ናቸው ያሉት አልቡርሃን ከግጭት ምንም አናተርፍም ብለዋል።

https://www.facebook.com/489211707826282/posts/pfbid0YvCKNBHeE7EVnW8mRu6P4g6roEELD9q2qYzo489eY5eHRr2ewCU56zsisoMSmbNql/
ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ ተጨማሪ ጥቃትና ጭፍጨፋ እንዳይከሰት የሚሊሻ እና የኮሙኒቲ ፖሊሲንግ ስርዓት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይደረጋል አሉ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) በወገኖቻችን ላይ ተጨማሪ ጥቃትና ጭፍጨፋ እንዳይከሰት በሁሉም አካባቢዎች ተጋላጭ ቀበሌዎች እና መንደሮችን በመለየት አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግላቸው እንዲሁም ነዋሪው ራሱን በተደራጀ መልኩ እንዲከላከል የሚሊሻ እና የኮሙኒቲ ፖሊሲንግ ስርዓት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይደረጋል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡

በወለጋ አካባቢ አሁንም አሸባሪው የሸኔ ቡድን በንፁሃን ወገኖቻችን ላይ አሳዛኝ ጭፍጨፋ ማካሄዱን ገልጸው፤ “ጥቃቱ የአማራ ብሄር ተወላጆችን ዒላማ ያደረገና ተጠቂዎችን ለመከላከል ሙከራ ባደረጉ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጭምር ያነጣጠረ ነው” ብለዋል።

ይህ ቡድን ህፃናትን፣ እናቶችን እና ደካማ አረጋውያንን ለይቶ ተደጋጋሚ ጥፋት በመፈፀም ሀገር የማፍረስ ግልፅ ተልዕኮ ያነገበ የተስፋ ቢሶች ጥርቅም መሆኑን በተግባር አረጋግጧል ሲሉ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

መንግሥት በመላው ሀገሪቱ በተለይም ተደጋጋሚ ጥቃት በሚፈፀምባቸው አካባቢዎች ህግ ለማስከበር፣ ሰላም እና ፀጥታ ለማስፈን እንዲሁም ዜጎች የተረጋጋ ህይወት እንዲመሩ ለማስቻል ጠንካራ ርብርብ እያደረገ ቢሆንም፤ አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች አሸባሪ ቡድኑ በንፁሃን ዜጎች ላይ ያነጣጠረ ጥፋት ...
https://www.facebook.com/489211707826282/posts/pfbid02XTtEwG6NFdY3LvKTWPzDTB4Wbkx3GhbYwHRacqnUSya3pnxKzpLLJ3VFmZXWdyT8l/
በብዙ ውጣ-ውረድ ታጅበን ትልቅ ውጤት ማስመዝገብ ችለናል - አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) በብዙ ውጣ-ውረድ ታጅበንም ቢሆን ትልቅ ውጤት ማስመዝገብ ችለናል ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሠ ጫፎ የምክር ቤቱን የአፈጻጸም ደረጃ አመላከቱ፡፡

የምክር ቤቱ አማካሪ እና አስተባባሪ ኮሚቴዎች እንዲሁም የመንግሥት ዋና እና ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታዎች በተገኙበት የአሥራ አንዱም የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2014 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ተገምግሟል፡፡

አፈ ጉባዔ ታገሠ በዚሁ ወቅት ከመንግሥት ምስረታ ጊዜ ጀምሮ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን በማሳተፍ ምክር ቤቱ ለሀገር ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አንስተዋል፡፡

እንደ ሀገርና እንደ ተቋም የተሠሩ ሥራዎች አበረታች እንደሆኑ እና በቋሚ ኮሚቴዎች የቀረቡት ተጨማሪ ሀሳቦች አስተማሪ እንደሚሆኑ ነው ያመለከቱት።

ስለሆነም ቆም ብለን በማሰብ፣ ሀገራችንን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ፣ የሁላችንም ቀና ትብብር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
https://www.facebook.com/489211707826282/posts/pfbid0QRz7dX4JE2449pAzgsN9cjS2pusfaK7ALVHmmfTpUAjPp9SdTUWsjV18Mmk11jSwl/?app=fbl
መንግሥት በየቀኑ 10 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ እያስገባ መሆኑ ተጠቆመ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) መንግሥት በየቀኑ በአማካይ 10 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ እያስገባ መሆኑን የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ገለጸ።

ባለስልጣኑ በሐምሌ ወር በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ይኖራል በሚል ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት የምጣኔ ሃብት አሻጥር የሚፈጥሩ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድም አሳስቧል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሳህረላ አብዱላሂ እንዳሉት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከባለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ የተከሰተው የነዳጅ እጥረት መንስኤ አቅርቦት ሳይሆን በሥርጭት ላይ በሚፈጸሙ ችግሮች እንደሆነ ተረጋግጧል።

ቀደም ሲል በየወሩ መጨረሻ ቤንዚን ላይ እጥረት ይከሰት እንደነበር ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት ባልተለመደ ሁኔታ በናፍጣ ላይ የተከሰተው እጥረት የሀገርን ሃብት ለግል ጥቅም ለማዋል የተደረገ አሻጥር መሆኑን ተናግረዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ በባለፉት ሦስት ወራት መረጃ መሰረት ከጂቡቲ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው የነዳጅ አቅርቦት በየወሩ እየጨመረ ነው ብለዋል።

በዚህም መንግሥት በአሁኑ ወቅት በየቀኑ በአማካይ 10 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ እያስገባ መሆኑን ገልጸዋል።

https://www.facebook.com/489211707826282/posts/pfbid02AadnFUKyhwFg9i3v2wFHfNfrpeLb61zCbidK7Pb3fCWRaygYg4qB8HwutWmA4Tv3l/?app=fbl
39ኛው የኢጋድ ልዩ የመሪዎች ጉባኤ በናይሮቢ እየተካሄደ ነው

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) 39ኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ልዩ የመሪዎች ጉባኤ በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው መሪዎቹ በአካባቢው ሀገራት የሚከሰተውን ድርቅ ማሸነፍ በሚቻልበት ሁኔታ፣ በሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የኢጋድ አባል አገራት መሪዎች በጉባኤው ተገኝተዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
የሱዳኑ ወታደራዊ መሪ ሥልጣን ለመልቀቅ ፈቃደኛ መሆናቸውን ገለጹ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) የሱዳን ጦር ኃይል አገሪቱ ወደ ሲቪል አስተዳደር እንድትመለስ ለማድረግ ቦታውን እንደሚለቅ ወታደራዊው መሪ ጄኔራል አብዱል ፋታህ አል-ቡርሃን ተናገሩ።

የአገሪቱ ጦር ኃይል ሱዳን ወደ ዴሞክራሲ ለምታደርገው ሽግግር እንቅፋት እንደማይሆንና ምርጫ እንዲደረግ ወስኖ እየሠራ እንደሆነ ገልጸዋል።

ጄኔራል አል-ቡርሃን ጨምረውም በአገሪቱ ያለውን ፖለቲካዊ ቀውስ ለማብቃት ከሲቪል ቡድኖች ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ ጦር ሠራዊቱ የሚያደርገውን ተሳትፎ እንደሚያቋርጥ አሳውቀዋል።

ነገር ግን አገሪቱ ውስጥ ምርጫ ስለሚደረግበት እንዲሁም ጦር ኃይሉ ሥልጣን ስለሚያስረክብበት ሂደት የጊዜ ሰሌዳ ምንም አለማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በሱዳን ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲመሰረት የሚጠይቁት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ሠራዊቱ ከፖለቲካው እንዲወጣ በመጠየቅ ለወራት የዘለቀ ተቃውሞ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል።
አዲሱን የነዳጅ ድጎማ ተግባራዊ ለማድረግ መንግሥት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) አዲሱ የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተግባራዊ ለማድረግ መንግሥት እየሰራ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተግባራዊነት በሚመለከት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር እና የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን በዛሬው ዕለት በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገ/መስቀል ጫላ የነዳጅ ድጎማ ለመተግበር በተዘረጋው ሥርዓት መሰረት በየሦስት ወሩ መንግሥት ለነዳጅ የሚያደርገውን ድጎማ 25 በመቶ እያነሳ እንደሚሄድ ገልጸዋል።

ድጎማ የሚደረግላቸው የሕዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ድጎማ ደግሞ በቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ እንደሚነሳ ገልጸዋል።

በዚህም መንግሥት በየስድስት ወሩ ተፈፃሚ በሚያደርገው ሥርዓት መሰረት 10 በመቶ ድጎማን እያነሳ የሚሄድ ሲሆን በቀጣይ 5 ዓመታት ውስጥ በድጎማ የሚደገፋ የሕዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ከድጎማ የሚወጡ ይሆናል ተብሏል።

በሰለሞን በየነ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ከባንክ እንደተደወለ በማስመሰል የማጭበርበር ሙከራዎች እየተደረገ በመሆኑ ኅብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ ማሳሰቢያ ተሰጠ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) አጭበርባሪዎች ከባንክ እንደደወሉ በማስመሰል ገንዘብ ለማጭበርበር ሙከራዎችን እያደረጉ በመሆኑ ኅብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ጥሪ አቀረበ።

አገልግሎቱ አጭበርባሪዎች የግለሰቦች ስልክ ላይ በመደወል እና ከባንክ እንደደወሉ በማስመሰል ሽልማት ደርሷችኋል፣ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎታችሁን አስተካክሉ እና ሌሎች መሰል መልእክቶችን በማስተላለፍ ገንዘብ ለማጭበርበር ሙከራዎችን እያደረጉ እንደሆነ ጥቆማዎች ደርሰውኛል ብሏል።

ግለሰቦች እንደዚህ ዓይነት መልእክቶች በሚደርሳቸው ወቅት አቅራቢያቸው በሚገኝ የባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ከማረጋገጣቸው በፊት ምንም ዓይነት እርምጃ ከመውሰድ በመጠንቀቅ ራሳቸውን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቁ አሳስቧል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ሕዳሴ ግድብ ለአፍሪካ የግጭት መንስኤ ሳይሆን የልማት ጉዳይ መሆን ነበረበት!
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አገልግሎቶች የሀገራቱን ሕዝቦች ወዳጅነት ማዕከል ማድረግ እንዳለባቸው ተጠቆመ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የሚሰጡ የቆንስላ አገልግሎቶች የሁለቱን ሀገራት ሕዝቦች ወዳጅነት ማዕከል ማድረግ እንዳለባቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ገለጹ፡፡

ሚኒስትር ዴኤታዋ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የአሜሪካ ኤምባሲ ለዜጎች የሚሰጡትን አገልግሎት ቀልጣፋ ለማድረግ ስለሚችሉበት ሁኔታ ዝርዝር ነጥቦች ተነሥተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን በሚኒስቴሩ የሚሰጡ የተለያዩ የአገልግሎት ዓይነቶች ጊዜ እና ሁኔታን ከግምት በማስገባት ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ እና ለሰብዓዊ ዕርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች እየቀረቡ መሆኑን አስረድተዋል።

በኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ለደንበኞች የሚቀርቡ የቪዛ አሰጣጥ ሂደቶችን ቀልጣፋ እና ዘመናዊ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ገልጸው በሽግግር ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ጉድለቶችም በቅርቡ ይወገዳሉ ብለዋል።

በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የሚሰጡ የቆንስላ አገልግሎቶች የሁለቱን ሕዝቦች ወዳጅነት ማዕከል ማድረግ እንዳለባቸው ጠይቀዋል።

ሌሎች የሁለትዮሽ እና ወቅታዊ ጉዳዮችን በሚመለከትም ሐሳብ በመለዋወጥ በቀጣይም ተባብሮ መሥራት ለመንግሥታቱ እና ለሁለቱ አገራት ሕዝቦች ያለው ፋይዳ ትልቅ መሆኑን መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW