AddisWalta - AW
45.3K subscribers
41.9K photos
204 videos
20 files
16.7K links
This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.

For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
Download Telegram
39ኛው የኢጋድ ጉባኤ ተጠናቀቀ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) በኬንያ ናይሮቢ የተካሄደው 39ኛው የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) አባል ሀገራት ርዕሳነ ብሔራት እና መሪዎች ጉባኤ ተጠናቀቀ፡፡

ጉባኤው ልዩ ልዩ የጋራ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግለጫ በማውጣት መጠናቀቁን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
ኢጋድ መንግሥት የሰሜኑን ግጭት ለመፍታት ሁሉን ዐቀፍ ውይይት ለማድረግ መወሰኑን ደገፈ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሁሉን ዐቀፍ ውይይት ለማድረግ የወሰደውን አዎንታዊ እርምጃ እንደሚደግፍ አስታወቀ፡፡

መንግሥት በሰብአዊ አቅርቦት ዙሪያ እየሰራ ያለውንም ሥራ ማድነቁን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኬንያ ናይሮቢ የተካሄደው 39ኛው የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) አባል ሀገራት ርዕሳነ ብሔራት እና መሪዎች ጉባኤ ልዩ ልዩ የጋራ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ዋልታ ምሽት በቀጥታ ሰኔ 28/2014
https://fb.watch/e46sS-YmXG/
"አፍሮ ኒውስ" የተሰኘ አዲስ የዋልታ የቴሌቪዥን ቻናል የሙከራ ስርጭቱን ጀመረ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) የዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት "አፍሮ ኒውስ" የተሰኘ አዲስ የቴሌቪዥን ቻናል የሙከራ ስርጭቱን ጀመረ፡፡

አዲሱ የቴሌቪዥን ቻናል በዋነኛነት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስርጭት የሚያደርግ ሲሆን በተጨማሪም ለውስን ሰዓታት በአረቢኛና በኪስዋሂሊ ቋንቋዎችም ለአድማጭ ተመልካቾች ተደራሽ ይሆናል።

የዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ንጉሴ መሸሻ (ፒኤችዲ) አፍሪካ ገፅታዋን ለዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ በትክክለኛው መነፅር የሚያሳይ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚተላለፍ የቴሌቪዥን ቻናል ያስፈልጋታል ብለዋል፡፡

አዲሱን ቻናል በNSS12 ሳተላይት በ11 ሺሕ 605 ፍሪኩዌንሲ፣ ሲምቦል ሬት 45 ሺሕ ፖለራይዜሽን ሆሪዞንታል ብለው ያገኙታል፡፡

ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት በቅርቡ በሐረሪ ክልል የመጀመሪያውን የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በመክፈት ወደ ሥራ ገብቷል፡፡

በቀጣይም ሁለተኛና ሦስተኛ ቅርንጫፎቹን በአፋርና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የሚከፍት ይሆናል፡፡

ከአንድ ዓመት ወዲህ ደግሞ ከቴሌቪዥን መስኮት በተጨማሪ "በዋልታ ኤፍ ኤም 105.3" ሬዲዮ ሞገድም ለአድማጮች መድረስ ጀምሯል፡፡

1986 ዓ.ም ላይ ምስረታውን ያደረገው ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል መጋቢት 24/2009 ዓ.ም ላይ ወደ ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ራሱን በማሳደግና አድማሱን በማስፋት በራሱ የቴሌቪዥን ቻናል ወደ ተመልካቾች መድረስ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

በሳሙኤል ሓጎስ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ሚኒስቴሩ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ አደረገ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ጭማሪ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታኅሣሥ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታና የትርፍ ህዳግ አሰራር እና የመሸጫ ዋጋ ማስተካከያና የታለመ ድጎማ አፈጻጸም ውሳኔ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ሥራ ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረት፡-
ቤንዚን - 47 ነጥብ 83 በሊትር
ነጭ ናፍጣ - 49 ነጥብ 02 በሊትር
ኬሮሲን - 49 ነጥብ 02 በሊትር

ቀላል ጥቁር ናፍጣ - 53 ነጥብ 10 በሊትር
ከባድ ጥቁር ናፍጣ - 52 ነጥብ 37 በሊትር
የአውሮፕላን ነዳጅ - 98 ነጥብ 83 በሊትር መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አስታውቋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተግባራዊ መሆን ጀመረ

ሰኔ 29/2014 (ዋልታ) የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎችን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርገው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ከዛሬ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከ160 ሺሕ በላይ ተሽከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ መሆን መጀመሩን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሸከርካሪዎች የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ ለመሆን አስፈላጊ መረጃዎችን በመስጠት በኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት በኩል ምዝገባ ማድረጋቸውን ሚኒስቴሩ አስታውሷል።

የብሔራዊ የታለመለከት የነዳጅ ድጎማን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል መተግበሪያ በልፅጎ አስተማማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።

በዚህም መሠረት በቴሌ ብር በኩል አገልግሎቱን ለማግኘት የተመዘገቡ ከ160 ሺሕ በላይ ተሸከርካሪዎች ከዛሬ ጀምሮ መተግበሪያውን በመጠቀም ይስተናገዳሉ ተብሏል።

የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ዓመታዊ የነዳጅ ፍጆታ ተቀራራቢ የሊትር መጠን ግምት በጥናት መለየቱና እያንዳንዱ ተሸከርካሪ የሚጠቀመውን የነዳጅ መጠን ያገናዘበ ስሌት በመቀመጡ ተሽከርካሪዎቹ ያለብክነት የታለመ የነዳጅ ድጎማን ጥቅም ላይ እንዲያውሉ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም መሰረት
- ባለሦስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) በቀን 7 ሊትር
- መለስተኛ የከተማ ታክሲ (ላዳ) በቀን 25 ሊትር
- ሚኒባስ ታክሲ በቀን 65 ሊትር
- መለስተኛ አውቶብስ በቀን 94 ሊትር
- የከተማ አውቶብስ በቀን 102 ሊትር
- የሕዝብ አውቶብስ በቀን 25 ሊትር
- ሀገር አቋራጭ አውቶብስ በቀን 65 ሊትር ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።
እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያ ከዋልታ ቴቪ ሰኔ 29/2014
https://fb.watch/e4TJ-lf1Zr/
በክልሉ ግንባታቸው ባልተጠናቀቁ ማደያዎች በህገወጥ መንገድ የተከማቸ ነዳጅ ተያዘ

ሰኔ 29/2014 (ዋልታ) በአማራ ክልል እንጅባራ ከተማ አስተዳደርና ሰሜን ሜጫ ወረዳ ግንባታቸው ባልተጠናቀቁ ማደያዎች በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸ ነዳጅ መያዙን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ መሠረታዊ ዕቃዎች ጉዳይ ዳይሬክተር ታፈረ ይመር ለኢዜአ እንደገለጹት ነዳጁ ሊያዝ የቻለው ከቢሮው፣ ከዞን፣ ከወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በተዋቀረ ቡድን በተደረገ ክትትል ነው።

በእንጅባራ ከተማ አስተዳደር በተደረገ ክትትል ግንባታው ባልተጠናቀቀ ማደያ 184 ሺሕ ሊትር ነዳጅ መገኘቱን ገልጸው ከነዳጁ ውስጥ 46 ሺሕ ሊትር የሚሆነው ቤንዚን ሲሆን ቀሪው ናፍጣ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በተመሳሳይ በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ ልዩ ቦታው ጉንጫ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በአራት ቦቴ የተገለበጠ ነዳጅ በህገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ መገኘቱን አመልክተዋል።

በሁለቱም ቦታዎች ተደብቆ የተገኘው ነዳጅ በአንድ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የቀረበና ግንባታቸው ባልተጠናቀቁ ሁለት ማደያዎች እንደተገኘ አብራርተዋል።

“ማደያዎቹ ከክልል ጀምሮ ከዞን፣ ከወረዳና ከከተማ አስተዳደር ከተሰጣቸው የግንባታ ፈቃድ ውጭ ገና ህጋዊ ዕውቅና ያላገኙና የማጠራቀሚያ ታንከር ብቻ የተቀበረባቸው መስፈርቱን ያላሟሉ ናቸው” ብለዋል።

ነዳጁ የስርጭት አግባቡን ያልተከተለ፣ ባልተጠናቀቀ ማደያ ያለዕውቅና የተከማቸና ለአደጋ በሚያጋልጥ መልኩ የተቀመጠ መሆኑን አስረድተዋል።
https://www.facebook.com/489211707826282/posts/pfbid0iwQt61dJr4DsCU4KY4kF5m9UkBnsWgETbTMft47Zz8DA9bbSRbSk5p5eVh2BX9iGl/?app=fbl
በከተማዋ ከ190 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተሰሩ ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ነው

ሰኔ 29/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል ባቱ ከተማ ከ190 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተሰሩ ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ነው።

በኦሮሚያ ክልል ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ ቶሎሳ ገደፋ የተመራ ልዑክ በባቱ ከተማ በበጀት ዓመቱ ሲሰሩ የነበሩትን የተለያዩ ፕሮጀክቶች እያስመረቀ ይገኛል።

በባቱ ከተማ አስተዳደር በበጀት ዓመቱ ከ190 ሚሊየን በላይ ወጪ ከተሰሩ ፕሮጀክቶች መካከል 70 ፕሮጀክቶች ተጠናቀው በዛሬው እለት እየተመረቁ እንደሚገኙ ነው የተገለጸው።

ተሰርተው በመጠናቀቅ እየተመረቁ ካሉ ፕሮጀክቶች መካከልም 35 ሚሊየን በሚጠጋ ወጪ የተሰሩ የ2ኛ ደረጃ ኢፈ ቦሩና ቡዑረ ቦሩ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ 13 ነጥብ 8 ኪ.ሜ የኮብል ሰቶን መንገድ፣ 3 ነጥብ 6 ኪ.ሜ የሚረዝምና 5 ሚሊየን ብር በሚጠጋ ወጪ የተሰሩ የመንገድ መብራት ማስፋፍያም ዋነኞቹ ናቸው።

በባቱ ከተማ እየተካሄደ ባለው የፕሮጀክት ምርቃት ላይ ከክልል የተወጣጡ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮችን ጨምሮ የባቱ ከተማ ማኅበረሰብም እየተሳተፉበት ይገኛል።

ታምራት ደለሊ (ከባቱ)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
31 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

ሰኔ 29/2014 (ዋልታ) ኮይካ ባደረገው የገንዘብ ድጋፍ በዩኒሴፍ የተገዙ 31 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የእናቶችና የጨቅላ ህፃናት ሞት ለመቀነስ እና ጤናቸው ለማሻሻል የሚያግዙ የህክምና መርጃ ቁሳቁስ ለጤና ሚኒስቴር ድጋፍ ተድርጓል።

መድሃኒት ፣ አልጋና ሞተርሳይክልን ጨምሮ 33 ዓይነት የህክምና ቁሳቁሶች ናቸው ድጋፍ የተደርጉት።

የህክምና ቁሳቁሶቹ ለአፋርና ቤንሻንጉል ክልሎች ይሰራጫሉም ተብሏል።

ድጋፉን የተቀበሉት የጤና ሚንስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ድጋፉ የእናቶችና ህፃናት ሞትን ለመቀነስ እና ጤናቸውን ለማሸሻል ያግዘናል ብለዋል።

በትእግስት ዘላለም