AddisWalta - AW
45.2K subscribers
41.8K photos
204 videos
20 files
16.6K links
This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.

For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
Download Telegram
መንግሥት በየቀኑ 10 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ እያስገባ መሆኑ ተጠቆመ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) መንግሥት በየቀኑ በአማካይ 10 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ እያስገባ መሆኑን የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ገለጸ።

ባለስልጣኑ በሐምሌ ወር በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ይኖራል በሚል ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት የምጣኔ ሃብት አሻጥር የሚፈጥሩ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድም አሳስቧል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሳህረላ አብዱላሂ እንዳሉት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከባለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ የተከሰተው የነዳጅ እጥረት መንስኤ አቅርቦት ሳይሆን በሥርጭት ላይ በሚፈጸሙ ችግሮች እንደሆነ ተረጋግጧል።

ቀደም ሲል በየወሩ መጨረሻ ቤንዚን ላይ እጥረት ይከሰት እንደነበር ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት ባልተለመደ ሁኔታ በናፍጣ ላይ የተከሰተው እጥረት የሀገርን ሃብት ለግል ጥቅም ለማዋል የተደረገ አሻጥር መሆኑን ተናግረዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ በባለፉት ሦስት ወራት መረጃ መሰረት ከጂቡቲ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው የነዳጅ አቅርቦት በየወሩ እየጨመረ ነው ብለዋል።

በዚህም መንግሥት በአሁኑ ወቅት በየቀኑ በአማካይ 10 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ እያስገባ መሆኑን ገልጸዋል።

https://www.facebook.com/489211707826282/posts/pfbid02AadnFUKyhwFg9i3v2wFHfNfrpeLb61zCbidK7Pb3fCWRaygYg4qB8HwutWmA4Tv3l/?app=fbl
39ኛው የኢጋድ ልዩ የመሪዎች ጉባኤ በናይሮቢ እየተካሄደ ነው

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) 39ኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ልዩ የመሪዎች ጉባኤ በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው መሪዎቹ በአካባቢው ሀገራት የሚከሰተውን ድርቅ ማሸነፍ በሚቻልበት ሁኔታ፣ በሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የኢጋድ አባል አገራት መሪዎች በጉባኤው ተገኝተዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
የሱዳኑ ወታደራዊ መሪ ሥልጣን ለመልቀቅ ፈቃደኛ መሆናቸውን ገለጹ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) የሱዳን ጦር ኃይል አገሪቱ ወደ ሲቪል አስተዳደር እንድትመለስ ለማድረግ ቦታውን እንደሚለቅ ወታደራዊው መሪ ጄኔራል አብዱል ፋታህ አል-ቡርሃን ተናገሩ።

የአገሪቱ ጦር ኃይል ሱዳን ወደ ዴሞክራሲ ለምታደርገው ሽግግር እንቅፋት እንደማይሆንና ምርጫ እንዲደረግ ወስኖ እየሠራ እንደሆነ ገልጸዋል።

ጄኔራል አል-ቡርሃን ጨምረውም በአገሪቱ ያለውን ፖለቲካዊ ቀውስ ለማብቃት ከሲቪል ቡድኖች ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ ጦር ሠራዊቱ የሚያደርገውን ተሳትፎ እንደሚያቋርጥ አሳውቀዋል።

ነገር ግን አገሪቱ ውስጥ ምርጫ ስለሚደረግበት እንዲሁም ጦር ኃይሉ ሥልጣን ስለሚያስረክብበት ሂደት የጊዜ ሰሌዳ ምንም አለማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በሱዳን ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲመሰረት የሚጠይቁት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ሠራዊቱ ከፖለቲካው እንዲወጣ በመጠየቅ ለወራት የዘለቀ ተቃውሞ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል።
አዲሱን የነዳጅ ድጎማ ተግባራዊ ለማድረግ መንግሥት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) አዲሱ የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተግባራዊ ለማድረግ መንግሥት እየሰራ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተግባራዊነት በሚመለከት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር እና የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን በዛሬው ዕለት በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገ/መስቀል ጫላ የነዳጅ ድጎማ ለመተግበር በተዘረጋው ሥርዓት መሰረት በየሦስት ወሩ መንግሥት ለነዳጅ የሚያደርገውን ድጎማ 25 በመቶ እያነሳ እንደሚሄድ ገልጸዋል።

ድጎማ የሚደረግላቸው የሕዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ድጎማ ደግሞ በቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ እንደሚነሳ ገልጸዋል።

በዚህም መንግሥት በየስድስት ወሩ ተፈፃሚ በሚያደርገው ሥርዓት መሰረት 10 በመቶ ድጎማን እያነሳ የሚሄድ ሲሆን በቀጣይ 5 ዓመታት ውስጥ በድጎማ የሚደገፋ የሕዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ከድጎማ የሚወጡ ይሆናል ተብሏል።

በሰለሞን በየነ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ከባንክ እንደተደወለ በማስመሰል የማጭበርበር ሙከራዎች እየተደረገ በመሆኑ ኅብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ ማሳሰቢያ ተሰጠ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) አጭበርባሪዎች ከባንክ እንደደወሉ በማስመሰል ገንዘብ ለማጭበርበር ሙከራዎችን እያደረጉ በመሆኑ ኅብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ጥሪ አቀረበ።

አገልግሎቱ አጭበርባሪዎች የግለሰቦች ስልክ ላይ በመደወል እና ከባንክ እንደደወሉ በማስመሰል ሽልማት ደርሷችኋል፣ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎታችሁን አስተካክሉ እና ሌሎች መሰል መልእክቶችን በማስተላለፍ ገንዘብ ለማጭበርበር ሙከራዎችን እያደረጉ እንደሆነ ጥቆማዎች ደርሰውኛል ብሏል።

ግለሰቦች እንደዚህ ዓይነት መልእክቶች በሚደርሳቸው ወቅት አቅራቢያቸው በሚገኝ የባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ከማረጋገጣቸው በፊት ምንም ዓይነት እርምጃ ከመውሰድ በመጠንቀቅ ራሳቸውን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቁ አሳስቧል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ሕዳሴ ግድብ ለአፍሪካ የግጭት መንስኤ ሳይሆን የልማት ጉዳይ መሆን ነበረበት!
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አገልግሎቶች የሀገራቱን ሕዝቦች ወዳጅነት ማዕከል ማድረግ እንዳለባቸው ተጠቆመ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የሚሰጡ የቆንስላ አገልግሎቶች የሁለቱን ሀገራት ሕዝቦች ወዳጅነት ማዕከል ማድረግ እንዳለባቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ገለጹ፡፡

ሚኒስትር ዴኤታዋ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የአሜሪካ ኤምባሲ ለዜጎች የሚሰጡትን አገልግሎት ቀልጣፋ ለማድረግ ስለሚችሉበት ሁኔታ ዝርዝር ነጥቦች ተነሥተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን በሚኒስቴሩ የሚሰጡ የተለያዩ የአገልግሎት ዓይነቶች ጊዜ እና ሁኔታን ከግምት በማስገባት ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ እና ለሰብዓዊ ዕርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች እየቀረቡ መሆኑን አስረድተዋል።

በኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ለደንበኞች የሚቀርቡ የቪዛ አሰጣጥ ሂደቶችን ቀልጣፋ እና ዘመናዊ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ገልጸው በሽግግር ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ጉድለቶችም በቅርቡ ይወገዳሉ ብለዋል።

በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የሚሰጡ የቆንስላ አገልግሎቶች የሁለቱን ሕዝቦች ወዳጅነት ማዕከል ማድረግ እንዳለባቸው ጠይቀዋል።

ሌሎች የሁለትዮሽ እና ወቅታዊ ጉዳዮችን በሚመለከትም ሐሳብ በመለዋወጥ በቀጣይም ተባብሮ መሥራት ለመንግሥታቱ እና ለሁለቱ አገራት ሕዝቦች ያለው ፋይዳ ትልቅ መሆኑን መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
39ኛው የኢጋድ ጉባኤ ተጠናቀቀ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) በኬንያ ናይሮቢ የተካሄደው 39ኛው የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) አባል ሀገራት ርዕሳነ ብሔራት እና መሪዎች ጉባኤ ተጠናቀቀ፡፡

ጉባኤው ልዩ ልዩ የጋራ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግለጫ በማውጣት መጠናቀቁን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
ኢጋድ መንግሥት የሰሜኑን ግጭት ለመፍታት ሁሉን ዐቀፍ ውይይት ለማድረግ መወሰኑን ደገፈ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሁሉን ዐቀፍ ውይይት ለማድረግ የወሰደውን አዎንታዊ እርምጃ እንደሚደግፍ አስታወቀ፡፡

መንግሥት በሰብአዊ አቅርቦት ዙሪያ እየሰራ ያለውንም ሥራ ማድነቁን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኬንያ ናይሮቢ የተካሄደው 39ኛው የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) አባል ሀገራት ርዕሳነ ብሔራት እና መሪዎች ጉባኤ ልዩ ልዩ የጋራ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ዋልታ ምሽት በቀጥታ ሰኔ 28/2014
https://fb.watch/e46sS-YmXG/
"አፍሮ ኒውስ" የተሰኘ አዲስ የዋልታ የቴሌቪዥን ቻናል የሙከራ ስርጭቱን ጀመረ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) የዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት "አፍሮ ኒውስ" የተሰኘ አዲስ የቴሌቪዥን ቻናል የሙከራ ስርጭቱን ጀመረ፡፡

አዲሱ የቴሌቪዥን ቻናል በዋነኛነት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስርጭት የሚያደርግ ሲሆን በተጨማሪም ለውስን ሰዓታት በአረቢኛና በኪስዋሂሊ ቋንቋዎችም ለአድማጭ ተመልካቾች ተደራሽ ይሆናል።

የዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ንጉሴ መሸሻ (ፒኤችዲ) አፍሪካ ገፅታዋን ለዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ በትክክለኛው መነፅር የሚያሳይ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚተላለፍ የቴሌቪዥን ቻናል ያስፈልጋታል ብለዋል፡፡

አዲሱን ቻናል በNSS12 ሳተላይት በ11 ሺሕ 605 ፍሪኩዌንሲ፣ ሲምቦል ሬት 45 ሺሕ ፖለራይዜሽን ሆሪዞንታል ብለው ያገኙታል፡፡

ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት በቅርቡ በሐረሪ ክልል የመጀመሪያውን የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በመክፈት ወደ ሥራ ገብቷል፡፡

በቀጣይም ሁለተኛና ሦስተኛ ቅርንጫፎቹን በአፋርና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የሚከፍት ይሆናል፡፡

ከአንድ ዓመት ወዲህ ደግሞ ከቴሌቪዥን መስኮት በተጨማሪ "በዋልታ ኤፍ ኤም 105.3" ሬዲዮ ሞገድም ለአድማጮች መድረስ ጀምሯል፡፡

1986 ዓ.ም ላይ ምስረታውን ያደረገው ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል መጋቢት 24/2009 ዓ.ም ላይ ወደ ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ራሱን በማሳደግና አድማሱን በማስፋት በራሱ የቴሌቪዥን ቻናል ወደ ተመልካቾች መድረስ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

በሳሙኤል ሓጎስ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ሚኒስቴሩ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ አደረገ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ጭማሪ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታኅሣሥ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታና የትርፍ ህዳግ አሰራር እና የመሸጫ ዋጋ ማስተካከያና የታለመ ድጎማ አፈጻጸም ውሳኔ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ሥራ ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረት፡-
ቤንዚን - 47 ነጥብ 83 በሊትር
ነጭ ናፍጣ - 49 ነጥብ 02 በሊትር
ኬሮሲን - 49 ነጥብ 02 በሊትር

ቀላል ጥቁር ናፍጣ - 53 ነጥብ 10 በሊትር
ከባድ ጥቁር ናፍጣ - 52 ነጥብ 37 በሊትር
የአውሮፕላን ነዳጅ - 98 ነጥብ 83 በሊትር መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አስታውቋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW