AddisWalta - AW
45.4K subscribers
42K photos
205 videos
20 files
16.7K links
This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.

For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
Download Telegram
ምክትል ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ ባሕር ዳር ገቡ

ሚያዚያ 24/2016 (አዲስ ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ ባሕር ዳር ከተማ ገብተዋል።

የጣና ሐይቅ ፈርጧ፣ የበርካታ ደሴቶች መናኸሪያ፣ የጢስ ዓባይ ፏፏቴ መገኛ፣ የበርካታ ቱሪስቶች መዳረሻ እና የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መቀመጫ በሆነችው ውቢቷ ባሕር ዳር ከተማ ገብተናል ሲሊ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎቹ ባሕር ዳር ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና ካቢኒያቸው እንዲሁም የከተማዋ ከንቲባ እና ህዝብ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር የተሰሩ ስራዎች በቁጥር
#አዲስ_ዋልታ
የትንሳኤ በዓልን በአዲስ ዋልታ

የትንሣኤ ዕለት ይጠብቁን!

#ትንሣኤ_በዓል
የትዳር መፍረስ እና የሀብት ክፍፍል
#ሕግ_ይዳኘኝ

ጋብቻ ከሚያስከትላቸው ውጤቶች አንዱ የጋራ ሀብት ነው፡፡ ፍችን ተከትሎ ብዙ ጊዜ ከሚፈጠሩት አለመግባባቶች አንዱ የጋራ ሀብት ክፍፍል ነው፡፡ አንድ ሰው ወደ ጋብቻ ከመግባቱ በፊት የነበረው ሀብትና ንብረት ከሕጋዊ ጋብቻው መፍረስ በኋላ የማን ይሆናል የሚለው ጉዳይ የብዙዎች ጥያቄ ነው፡፡

በዛሬው “ሕግ ይዳኘኝ” መርኃ ግብራችን ትዳር ሲፈርስ ተፋችዎቹ ሀብታቸውን እንዴት እና በምን አግባብ ይከፋፈላሉ በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ትኩረት ይደረጋል።

በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 62 መሰረት ባልና ሚስት ከግል ጥረታቸውና ከግል ወይም ከጋራ ንብረታቸው የሚያገኟቸው ገቢዎች ሁሉ የጋራ ሀብቶቻቸው ይሆናሉ፡፡ በዚህ ሕግ በአንቀጽ 58(2) መሰረት የአንደኛው ተጋቢ የግል ሀብት ነው ካልተባለ በስተቀር ባልና ሚስት ከተጋቡ በኋላ በግብይት የሚያገኙት ንብረት ሁሉ የጋራ ሀብታቸው እንደሚሆንም ተደንግጓል፡፡ በፍች ወቅትም ይከፋፈላሉ።

በስጦታው ውል ወይም በኑዛዜው ቃል በሌላ አኳኋን ካልተመለከተ በስተቀር በስጦታ ወይም በኑዛዜ የተሰጧቸውም ንብረቶች የጋራ ሀብቶቻቸው ናቸው፡፡ አንደኛው ተጋቢ የግል ሀብቱ መሆኑን ካላስረዳ በስተቀር ማንኛውም ንብረት በአንደኛው ተጋቢ ስም ብቻ የተመዘገበ ቢሆንም እንኳን የጋራ ሀብት እንደሆነ ይቆጠራል ሲል ቤተሰብ ሕጉ በአንቀጽ 63 አስቀምጧል፡፡

ባልና ሚስቱ ከተጋቡ በኋላ አንዱ የግል ሀብቱ በሆነ ንብረት ለውጥ ያገኘው ወይም በግል ገንዘቡ የገዛቸው ወይም የግል ንብረቱን ሽጦ የሚያገኘው ገንዘብ የግል ይባልልኝ ብሎ ለፍርድ ቤት ጥያቄ አቅርቦ ፍርድ ቤቱ ያጸደቀው እንደሆነ የግል ሀብቱ እንደሚሆንም በአንቀጽ 58 ተደንግጓል፡፡
👇👇
https://shorturl.at/ehnL8
የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው

ሚያዝያ 25/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው።

በዓሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን፣ በካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን እና በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት በስግደት፣ በጾም፣ በጸሎት እና በዝማሬ እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዕለቱ ቀኑን የሚያወሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የሚነበቡ ሲሆን በዕለተ ስቅለት የተከናወኑ ተግባራት እየታሰበም የስግደት ስርዓት ይከናወናል።
የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከበረ

ሚያዝያ 25/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በልደታ ማሪያም ካቶሊክ ካቴድራል ቤተክርስቲያን በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነሥርዓት ተከበረ።

የቤተክርስቲያንቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል በሥነ ሥርዓቱ ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት ስቅለት ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ከኃጢአት ለማንፃት ሲል በመስቀል ላይ የተሰቀለበት ሁነት መሆኑን ተናግረዋል።

የዚህም መለኮታዊ መልዕክት ማሳያነቱ ከራስ ባለፈ ለሰው ልጆች ሁሉ ዋጋ መክፈልንና የመልካምነት ሁነኛ ማሳያ መሆኑን አስረድተዋል።

የትንሳኤ በዓልም አጠቃላይ የማካፈልና የመረዳዳት መሆኑን ገልጸው በዓሉን እርስ በእርስ በመተሳሰብ፣ በመደጋገፍ፣ መልካምን ሁሉ በማሰብና በማድረግ ጭምር ልናከብረው ይገባል ብለዋል።

በልደታ ማሪያም ካቶሊክ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ስቅለትን ያከበሩት የእምነቱ ተከታዮች በበኩላቸው ስቅለት አንዳችን ለሌላችን ዋጋ መክፈልን የሚያስተምር ነው ሲሉ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በመሆኑም የስቅለትን ብሎም የትንሳኤን በዓል ስናከብር ሁላችንም ከራሳችን አልፎ ለሌሎች ማሰብንና ማድረግን ዓላማ አድርገን መሆን አለበት ብለዋል፡፡
በየአካባቢው የቁም እንስሳት ቅርጫ ማረድ አለመከልከሉ ተገለጸ

ሚያዝያ 25/2016 (አዲስ ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ የትንሳኤ በዓል ህብረተሰቡ በየቤቱ እና በየአካባቢው የቁም እንስሳትን ቅርጫ ማረድ አለመከልከሉን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው ለትንሳኤ በዓል ህብረተሰቡ በየቤቱ እና በየአካባቢው የቁም እንስሳትን ቅርጫ ማረድ ተከልክሏል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን አስታውቋል።

በየአካባቢው በህገ ወጥ መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የሚገኙ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የከተማውን ነዋሪ ጤንነት ላይ ጉዳት ስለሚያደርስ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግም ቢሮው ባወጣው መረጃ አመላክቷል።

የከተማው ነዋሪ በዓላትን ሽፋን በማድረግ ጤንነቱ ያልተረጋገጠ እንስሳት አርዶ ማከፋፈል በጤና ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ግምት ውስጥ በማስገባት በህገወጥ እርድ የሚሰማሩ አካላት በሚደረገው ቁጥጥር ተባባሪ እንዲሆን አሳስቧል።
የስቅለት በዓል በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከበረ

ሚያዝያ 25/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከብሮ ዋለ።

በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በተከናወነው ሥነ ስርዓት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናትና ምዕመናን በተገኙበት በጸሎትና በስግደት ተከብሯል።

በትናንትናው እለት የጸሎተ ሐሙስ "ሕፅበተ እግር" ሥነ ስርዓት በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ መከበሩ ይታወቃል።

የፊታችን እሁድ ደግሞ የፋሲካ በዓል በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል።
እንኳን ለ2016 ዓ.ም የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
ለአጋሮቻችን፣ለአዲስ ዋልታ ቤተሰቦች እና ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ።

ለአብሮነታችሁ ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን። መልካም በዓል!!

ጋዜጠኛ መሀመድ ሀሰን የዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ
ኤፕሲዊች ታዉን ወደ ፕሪሚዬር ሊግ ማደጉን አረጋገጠ

ሚያዚያ 26/2016 (አዲስ ዋልታ) ኤፕስዊች ታዉን ከ22 ዓመታት በኋላ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ተመለሰ።

በቅፅል ስማቸው ዘትራክተር ቦይስ የሚባሉት ኤፕስዊቾች ዛሬ ከሃደርስፊልድ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፉቸውን ተከትሎ ወደ ታላቁ ፕሪሚዬር ሊግ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል።

የቡድኑ ማደግ አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ ባለፈው ዓመት ከሶስተኛ ዲቪዚዮን ወደ ሻምፒዮንሽፑ አድጎ ባመቱ ደግሞ ወደ ፕሪሚዬር ሊጉ መመለሱ ነው የተገለጸው።

ይህም ሳውዝሃምፕተን እ.ኤ.አ 2012 ካስመዘገበው ታሪክ ጋር እንዲጋራ አስችሎታል።

በሻምፒዮንሽፑ 24 ቡድኖች የሚሳተፉ ሲሆን በደረጃ ሰንጠረዥ አንደኛና ሁለተኛዎቹ ቡድኖች በቀጥታ ወደ ፕሪሚዬር ሊጉ ያድጋሉ። ሌስተር ሲቲ በኬራን ማኬና ከሚሰለጥነው ኤፕስዊች ታዉን ቀደም ብሎ ወደ ፕሪሚዬር ሊጉ መመለሱ ይታወሳል።

ቀጣዮቹ አራት ቡድኖች የደርሶ መልስ ጨዋታ አድርገው አንደኛ የወጣው ቡድን በሶስተኝነት ፕሪሚዬር ሊጉን ይቀላቀላል፡
የትንሳዔ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው

ሚያዝያ 27/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ (ፋሲካ) በዓል በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በዛሬው እለት በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት ዕለት የሚታሰብበት ነው።

በዓሉን በማስመልከት የተለያዩ የሀይማኖት መሪዎች ባስተላለፉት መልእክት፤ የትንሳኤ በዓል እግዚአብሄር አምላክ ለሰው ልጆች ያለውን ታላቅ ፍቅር በልጁ ሞትና ትንሳኤ የገለጠበት በመሆኑ ምእመናንም የተራቡትን በማብላትና የተቸገሩትን በመርዳት ሊያከብሩት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ምዕመናን በዓሉን ሲያከብሩ ስለ ሀገር ሰላም እና እድገት እንዲያስቡ እንዲሁም የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የሀይማኖት መሪዎቹ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለአረጋዊያን፣ እና ለአቅመ ደካሞች የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋርተዋል።