ውሉደ ብርሀን ሰ/ት/ቤ/ት🙏(ጫንጮ)
773 subscribers
84 photos
4 files
98 links
ሰንበት ትምህርት ቤት የመልካም ወጣት የመልካም ትውልድ መፍለቂያ ናት! ትውልድን ለበጎ ነገር የምታበቃ ናት፡፡


የጫንጮ ከተማ ደ/ብ/ቅ/እግዚአብሔር አብ እና ደ/ሲ/ቅ/ ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ ው/ብ/ሰ/ት/ቤት ቻናል
ለሀሳብ እና አስታየት @weldebirhanbot @ty1921 ይጠቀሙ

ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ መልካም ነው፡፡
Download Telegram
#ሰበር_ዜና

ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው እለት በአካሔደው ምርጫ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን የቅዱስ ዋና ጸሐፊ በማድረግ ሾሟል።

የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከእነሱ ጋራ ይኹን!
@yeberhanljoche
✔️ዕርገት እንኳን አደረሰን

⛪️ዐረገ እግዚአብሔር በይባቤ ፤ወእግዚእነ በቃለ ቀርን፤ ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ።///" አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ። ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ፤ ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ።"

✝️" ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።" ማር ፲፮፥፲፱

✍️"እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ። እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ# ኃይል #እስክትለብሱ ድረስ #በኢየሩሳሌም #ከተማ ቆዩ። እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ #ሰማይም #ዐረገ። እነርሱም፤ ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ።" ፳፬፥፵፰-፶፫

"ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ኢየሱስ የመረጣቸውን ሐዋርያትን በመንፈስ ቅዱስ ካዘዛቸው በኋላ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ፥ ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ ስለ ጀመረው ሁሉ መጀመሪያውን ነገር ጻፍሁ፤ ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው። ከእነርሱም ጋር አብሮ ሳለ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው፥ ነገር ግን። ከእኔ የሰማችሁትን አብ የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቁ፤ ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፥ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኃላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ አለ። ሐዋ ሥራ ፩፥፩-፭


በችግር ላይ ያሉትን እሱ በምህረቱ ይዳብስልን
https://t.me/yeberhanljoche
ኦርቶዶክሱ ቅዱሳንህን እወቅ

አቡነ ዜና ማርቆስ

ቀድሰው ሕዝቡን ሁሉ ሲያቆርቡ ቢመሽባቸው ፀሐይን እንደ ኢያሱ ገዝተው ያቆሟት እና 8 እንጀራን አበርክተው 8ሺህ ሕዝብ በመመገብ ጌታችንን የመሰሉት ታላቁ ጻድቅ አቡነ ዜና ማርቆስ

አቡነ ዜና ማርቆስ፡- አባታችን ዜና ማርቆስ ሀገራቸው ጽላልሽ አውራጃ ምድረ ዞረሬ ስትሆን ትውልዳቸው ከነገደ ሌዊና ከእስራኤል ነገሥት ወገን ነው፡፡ ወላጆቻቸው ልጅ በማጣት ሲያዝኑ አንድ ዕለት ሐዋርያውና ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ወደ እናታቸው ማርያም ዘመዳ ሌሊት መጥቶ ገድሉና ትሩፋቱ በዓለም ሁሉ የመላ ጻዲቅ ልጅ እንደምትወልድ ነገራት፡፡ ለአባቱ ለቀሲስ ዮሐንስም እንዲሁ ተገልጦለት ‹‹ሚስትህ ማርያም ዘመዳ የካቲት 24 ፀንሳ ኅዳር 24 ቀን ይኸውም በካህናተ ሰማይ በዓል ቀን ትወልዳለች፣ ስሙም ዜና ማርቆስ ይባላል›› በማለት ብስራቱን ነግሮታል፡፡

በወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ብሥራት መሠረት አባታችን በተወለዱም ዕለት ቅዱስ ዑራኤልና ቅዱስ ሩፋኤል የብርሃን ልብስ አልብሰው በክንፋቸው ሲጋርዱአቸው ለሰዎችም ሁሉ ታይቷል በወቅቱም የአባ ሳሙኤል ዘወገግ አባት እንድርያስና የአቡነ ተክለሃይማኖት አባት ቅዱስ ጸጋ ዘአብ እስኪደነቁ ድረስ ይህን በዓይናቸው ተመልክተዋል፡፡ ሁለቱ መላእክትም ከእናታቸው ዕቅፍ ወስደው ወደ ሐዋርያው ማርቆስ መቃብር ወስደው ለማርቆስና ለቅዱሳን ጳጳሳት አስባርከዋቸው መልሰው ለእናቱ ሰጧቸው፣ እናቱ ግን ይህን አታውቅም ነበርአቡነ ዜና ማርቆስም በተወለዱ በሦስተኛው ቀን በእግራቸው ቆመው ‹‹አንድ አምላክ ለሆኑ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለሁ›› ብለው ሦስት ጊዜ አምላካቸውን አመስግነው ሰግደዋል፡፡ በ40 ቀኑ ሲጠመቅ የሚያጠምቀው ካህን የአባቱ ወንድም እንድርያስ ውኃው ሲፈላ አይቶ ሸሽቷል፡፡ መልአኩም እንዳይፈራ ነግሮት ለእርሱም ተአምር እንደሚደረግለት አስረዳው እንድርያስም ዕድሜው 72 ነበርና ራሰ በራ ስለነበር በውኃውም ራሱን ቢታጠብበት ጸጉር አብቅሏል፡፡ ሕዝቡም ሁሉ ይህን አይቶ አደነቀያችም ውኃ ሌሎች በጣም ብዙ ተአምራትን አደረገች፡፡

አንድ ዓመት በሆነውም ጊዜ ቤተክርስቲያን ውስጥ እየዳኸ ሲሄድ መልአክ በክንፎቹ አቅፎ ወስዶ ጌታችንና እመቤታችን ጋር አቅርቦት አስባርኮታል፡፡ እንዲሁም የ15ቱን ነቢያት፣ የ12ቱን ሐዋርያት የ72ቱን አርድእት፣ ሃይማኖታቸው የቀና የ318ቱን ሊቃውንት፣ የጻድቃንን፣ የሰማዕታትን የእነዚህን ሁሉ በረከት እንዲቀበል ካደረገው በኋላ ወደዚያች ቤተክርስቲያን መለሰው፡፡ ከጳጳሱ ከአቡነ ጌርሎስ ድቁናን ተቀብሎ ከአባቱ ጋር ወደ ሀገሩ ሲመለስ ዘራፊዎች ደብድበው በትራቸውንም ሳያስቀሩ ዘረፏቸውአቡነ ዜና ማርቆስም ወደ ፈጣሪው በጸለየ ጊዜ በትራቸው እባብ ሆና ነድፋ ገደለቻቸው፡፡ በኋላም ወደ አምላካቸው ጸልየው ከሞት እንዲነሱ በማድረግ በአካባቢውም ያሉ ሰዎች ሁሉ በእርሱ አምላክ እንዲያምኑ አድርጓቸዋል

‹አቤቱ ጠላቶቹን እስከደመሰሰና ለእስራኤል ልጆች ርስታቸውን እስካካፈለ ድረስ ለኢያሱ ፀሐይን በገባዖን ያቆምክ አንተ ነህ፤ ዛሬም ቅዱስ ሥጋህን ክቡር ደምህን ለእነዚህ ባሮችህ ቅዱሳን መነኮሳትና ለሕዝቦችህ እስከማቀብላቸው ድረስ እንዲሁ በቸርነትህ ብዛት ፀሐይን አቁማት› ብሎ በጸለየ ጊዜ ፀሐይዋ ወዲያውኑ ቆመች፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዳሴውን ጨርሶ ሕዝቡን ሁሉ አቆረባቸው፡፡››

ቅዱስ አባታችን በምሁር ኢየሱስ ገዳም ከሬብ በሚባል ዋሻ ውስጥ 40 ዓመት ዘግተው ተጋድለዋል፡፡ በዚህም ሳሉ መልአክ የዕረፍታቸውን ዕለት ታኅሣሥ ሦስት ቀን እንደሚሆን ስለነገራቸው ታኅሣሥ አንድ ቀን ወደ ገዳማቸው በመሄድ ቀድሰው ሕዝቡን ሁሉ ሲያቆርቡ ቢመሽባቸው ፀሐይን ለሁለተኛ ጊዜ እንደ ኢያሱ ገዝተው አቁመዋታልአባታችን ዜና ማርቆስ የዕረፍታቸውን ዕለት ከመልአኩ ከተረዱ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አሏቸው፡- ‹‹ከዚህ ዓለም የምለይበት ጊዜ ደርሷልና ወደ ፈጣሩዬ እሄዳለሁ፣ እኔ ሽማግሌ አባታችሁ የምመክራችሁን ስሙ፣ ከበጎ ሥራ ሁሉ አስቀድማችሁ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ፣ ፍቅር ሰማያዊ መንግሥትን ለማግኘት በባለሟልነት ወደ እግዚአብሔር ፊት ያደርሳልና›› ብለው መከሯቸው፡፡ ዳግመኛም ጾመኛ ነኝ አትበሉ አሏቸው፡፡ ‹‹ስለ ነፍሳችሁ ድኅነት፣ ከመከራና ከጥፋትም ሁሉ ለማምለጥ በምትጾሙ ጊዜ እንዲህ እየጾማችሁ ሳላችሁ ስለምትሹትግብር ወደ ዓለም ሰዎች ብትደርሱና በጾም ቀን ሲበሉና ሲጠጡ ብታዩአቸው መብልና መጠጥን በሚወዱ ሰዎች ፊት በውጭ በአደባባይ ‹ዛሬ የጾም ቀን ስለሆነ እኛ እንጾማለን› አትበሉ፡፡ ስለ እናንተ መጾምና ስለ እነርሱም አለመጾም አንዳች አትናገሩ፣ ባለመጾማቸውም አትንቀፏቸው፡፡ ስለ ሌላ ሥራ ወደማይጾሙ ሰዎች ብትደርሱ ግን በጾም ዕለት ወንድሞቻችን ‹ኑ አብረን እንብላ› ቢሏችሁ እኛ እንጾማለን አትበሉ፣ እንዲህ በሉ እንጂ፡- ‹ወደ እናንተ ከመምጣታችን በፊት ከቤት በልተናል፣ ጠግበናል› ስትሏቸው እናንተ እንደምትጾሙ ያውቃሉ፡፡›››

ከዚህም በኋላ አቡነ ዜና ማርቆስ ታኅሣሥ ሁለት ቀን የደቀ መዛሙርቶቻቸውን እግር ሲያጥቡ ውለው አስቀድሞ መልአኩ እንደነገራቸው ታኅሣሥ ሦስት ቀን በ140 ዓመታቸው ነቢይም፣ ሐዋርያም፣ ካህንም፣ ባለራእይም፣ የሀገራችንም ብርሃን የሆኑት ጻዲቁ አባታችን በክብር ዐርፈዋል ጌታ ለአባታችን ብዙ ቃልኪዳን የገባላቸው ሲሆን ከቃልኪዳናቸው ውስጥ እሚገርመኝ አንዱ ይህ ነው ማንም 1 ጧፍ ወደ ገዳምህ ይዞ መጥቶ የሰጠ ሰው ቢኖር ከአገሩ ከወጣ ወደ ሀገሩ ሳልመልሰው እና ንስሀ ገብቶ ሳይቆርብ አይሞትም የሚል ነው እንዲሁም በስምህ ቢለምነኝ ስለ ወዳጄ ስለ አንተ ስል ከ160 ዓመት ወይም ከ140 ወይም ከ120 ወይም 80 ዓመቱ በፊት በሞት አልወስደውም። እነዚህን ዕድሜ እንዲያይ አደርሰዋለው፤ እነዚህንም ዓመታት እየጨመርኩኝ ዘመኑን በመልካም እንዲፈፅም
እጠብቀዋለው።
የአቡነ ዜና ማርቆስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
https://t.me/yeberhanljoche
✟የዕለት እንጀራችንን ስንቀበል የአደራውንም መስጠት አንዘንጋ✟

በጸሎት ኃይል የሚያምን አንድ ጽኑዕ ክርስቲያን ነበር፡፡ ይህም ክርስቲያን ጥሪት የሌለው ደሃ፣ የሚበላ የሚቸግረው ረሃብተኛ፣ ልብሱ በላዩ ላይ አልቆ የታረዘ ምስኪን ነው፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በጸሎት ሕይወቱ የነበረውን ትጋት በቅርበት ያውቅ የነበረው አንድ ወዳጁ እየተቆጣ ‹ቢያንስ ለረሃብህ ማስታገሻ ቁራሽ ዳቦ እንኳን ማሰጠት ካልቻለ የአንተ ጸሎት ፋይዳው ምንድር ነው? ይቅርብህ በቃ! ፈጣሪህ አይሰማህም ማለት ነው› ሲል ተስፋ በሚያስቆርጥ ቃል ተናገረው፡፡ ያም ምስኪን ክርስቲያን እንዲህ ሲል መለሰለት :- ‹እግዚአብሔርማ አልረሳኝም። ለአንዱ ሰው ከዕለት እንጀራው የበለጠ አትርፎ በመስጠት ለእኔ እንዲያካፍለኝ መልእክተኛ አድርጎት ነበር፡፡ነገር ግን ይህን አደራ የተቀበለው ሰው ዘነጋኝ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ሳይሆን አድራሹ ሰው ረስቶኛል!›

መጻሕፍት እንደሚያስተምሩን "የዕለት እንጀራችንን ስጠን" የሚለው ጸሎት ለመነኮሳት ሲሆን "ለዕለት"፣ በዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ሲሆን ደግሞ "ለዓመት" የሚሆን እንጀራ ስጠን ማለት ነው። ታዲያ ለምን አንዳንዶች ከዓመት የሚተርፍ ብዙ እንጀራ ሲያገኙ፣ ሌሎች ደግሞ ለዕለት እንኳን የሚሆን ቁራሽ ያጣሉ ? መቼም ‹ለሰው ፊት የማያዳላ› እግዚአብሔር "አድልዎ ቢኖርበት ነው" ብለን የድፍረት ቃል በእርሱ ላይ አንናገርም።(ሐዋ 10፥34) ይህ የሆነው እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት አትርፈው ያገኙ ሰዎች ምንም የሌላቸውን እንዲረዱ እና መግቦት የባሕርይው የሆነውን አምላካቸውን በጸጋ እንዲመስሉት ነው። በዚሁም ላይ በፈጠራቸው ሰዎች መካከል ያለውን የመተዛዘንና የፍቅር ትስስር የበለጠ ለማጠናከር ነው፡፡

‹የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ› ብለን የለመንነው አምላክ ከዓመት እንጀራችን በላይ አትርፎ የሚሰጠን፣ የሚበቃንን ያህል ተመግበን በቀረው ለሌሎች አድራሽ መልእክተኞች እንድንሆን ነው። ስለዚህ ይህን የተጣለብንን አምላካዊ አደራ ባለመወጣት ድሆችን አንበድል፤ ተማርረው ከፈጣሪያቸውም ጋር እንዲጣሉ አናድርጋቸው።
@yeberhanljoche
እንኳን ደስ አለክ መምህራችን ያስተማርከንን በተግባር አሳየከን
ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡ በሌላ አገላለጽ ብነግራችኁ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡ እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ጾመ ሐዋርያት (ሰኔ ጸም) ሰኔ 6/2014 ዓ.ም
(JUNE 13/2022 G.C) ይገባል፡፡
@yeberhanljoche
ናፍቆናል መቅደስህ !!!


ያ የሚያምረው መቅደስ የታቦት ማደሪያው፣
የሕይወት እንጀራ ቃሉን መመገቢያው
የነፍስ መድኃኒት ቁርባን መቀበያው፣
የጥምቀት የተክሊል ምሥጢር መፈጸሚያው፣
የቀዳሽ ያስቀዳሽ ጸሎት ማሳረጊያው፣
የሰው ያለህ ይላል ጭር ብሎ ቤቱ፣
ምስጋና የሚያቀርቡት ቀርተው ሕፃናቱ ፡ሴት ወይዛዝርቶቹ ደግሞም አዛውንቱ ፣
ወጣቶች ጎልማሶች እንዲሁም መኳንንቱ ፡
ሁለት ወር ሆናቸው ከቀሩ ከቤቱ ፡ወንበሩ ባዶውን አቤት ማስፈራቱ
ዘንድሮስ ሞተናል በሕይወት የለንም
በደላችን በዝቶ ያውም በዓብይ ጾም
ቤቱ ዎና ሆነ ምዕመናኑ የሉም
ካህናት ዲያቆናት ተሟልተው አይታዩም።
አወይ ማሳዘኑ አወይ ማስለቀሱ በታላላቅ በዓላት ጭር ብሎ መቅደሱ
የምናከብራቸው በዓላቱ በሙሉ ሆኖ የማያውቀውን ዘንድሮ ታጎሉ
የትንሣኤው ደስታ ክብሩ ቢቀርብን በተደበቅንበት በቤታችን ሆነን
አባቶች በመቅደስ ሲላቀሱ እያየን ጡት እንዳስጣሉት ልጅ እኛም አለቀስን
መንበረ ጸባዖት ይድረስ ጩኸታችን
እንደወጣን አንቅር ከቤትህ መልሰን
ናፍቆናል መቅደስህ ዳግም ዕድል ስጠን
ይቅር በለንና በቤትህ ሰብስበን
ግድ ሆኖብን እንጅ ወደነው አይደለም
እንዲህ ያለ አምልኰት ልንለምደው አንችልም
በሞዐብ ምድር ላይ ሙሴ እንዳንቀላፋው፣
ምድሪቷን ሳይረግጣት ሳይገባ ከተስፋው፣
በሩቅ በዓይኑ እያየ መግባት ተመኝቶ፣
ሳይገባባት ቀርቷል ያቺን ምድር ከቶ።
አሁንም አባት ሆይ ሳንገባ ከመቅደስ፣
እንደ ወጣን ቀርተን ዳግም ሳንመለስ፣
ብርቱ ኀዘን እንዳይሆን እንደቸርነትህ
በይቅርታህና በምሕረት ደግፈህ
ከመአት ከመቅሰፍቱ ከክፉ ጠብቀህ፣
ለመቅደስህ አብቃን እንደ አባትነትህ ኤልሻዳዩ ንጉሥ አንተ ይቅር ባይ ነህ። አሜን
@yeberhanljoche
ወጣትነት
ወጣትነት ከሁሉም የእድሜ ክልል በሁሉም ነገር የሚበልጥ ኃይል የምናገኝበት ጊዜ ነው። አካላዊም ሆነ አዕምሯዊ አቅማችን ብርቱ የሚሆንበት ጊዜ ነው። ይህንን ጊዜያችንን ብንጠቀምበት ብዙ ነገር ለክርስቶስ ማድረግ እንችላለን። ዛሬ ያለን ኃይልም ሆነ ዛሬ ያለን ጊዜ ነገ ወደ ስራ ዓለም ስንገባ፣ ነገ ወደትዳር ዓለም ስንገባ እናጣዋለን። ስለዚህ ዛሬ ላይ ወጣትነታችንን ለክርስቶስ እንስጥ። እግሮቻችን ብርቱ ሳሉ ወደቤቱ ዘወትር እንገስግስ፣ አእምሯችን በሳል ሳለ ክርስቶስን እናገልግል፣ ወደ አገልግሎት እንግባ፣ የጭንቀት ቀን ሳይመጣ ፈጣሪን እናስብ፣ ይህን በማህበራዊ ሚዲያ የምናጠፋውን ጊዜ ነገ ወደሥራና ትዳር ዓለም ስንገባ አናገኘውም። ስለዚህ በከንቱ ምንም ጥቅም በማይገኝበት ወሬ ብቻ ጊዜያችንን ከምናሳልፍ አይተናቸው የማናውቃቸውን ቁጥራቸው የተከመረውን መንፈሳዊ ገጾች እንመልከት፣ መንፈሳዊ ትምህርቶችን እናዳምጥ፣ ጽሁፎችን እናንብብ፣ ሰይጣን ይህን የሚጠቅመንን ነገር አሰልችቶን በማይጠቅም ከንቱ ነገር ጊዜያችንን እያስባከነ እንደሆነ ይግባን። ወጣትነታችንን ለክርስቶስ ኢየሱስ እንስጥ፣ ይህን ዕንቁ ጊዜያችንን በከንቱ አናባክን።
@yeberhanljoche
ሥርዓተ ማኅሌት ዘሰኔ ሚካኤል
"ሰኔ ፲፪"

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለጒርኤክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ: ብኡላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ: እመትትኃየዩኒሰ ኢትኅድጉኒ ጽኑሰ: ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ስጋየ ጌሠ: ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ።

ዚቅ
ኢይጽሕቅ ዘይመክሮ ወኢየኀሥሥ ዘይመክሮ: አልቦቱ ጥንት ወኢተፍጻሜት: ኢየኀልቅ መንግሥቱ ወአልቦ ዘይክል መዊዓ ኀይሉ: ወአልቦ ኁልቊ ለሠራዊተ መላእክት እለ ይትለአክዎ: አንተ ውእቱ አቡሃ ለጥበብ: ገባሬ ኲሉ ፍጥረት ወገባሪሃ ለሕግ።

ነግሥ
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሳሕል: እንበለ ባህቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል።

ዚቅ
አመ ይነፍህ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ: አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን: ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ: በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት።

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ: ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ፀሃፈ: ሶበ እጼውእ ስመከ ከሢትየ አፈ: ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ: ለረዲኦትየ ነዓ ሠፊሐከ ክንፈ።

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ዓቢተነ በመድኃኒትከ: ጸግወነ ንጸውዕ ስመከ: ኖላዊነ ኄር ትጉሕ ዘኢትነውም ሰላመከ ሀበነ።

ወረብ
ሀበነ ሰላመከ ንጸውዕ ስመከ/፪/
ዘኢትነውም ትጉሕ "ኖላዊነ ኄር"/፪//፪/

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለልሳንከ በነቢበ ጽርፈት ዘኢተኃበለ: በእንተ ስጋሁ ለሙሴ አመ ምስለ ሰይጣን ተበኃለ: ሚካኤል ክብርከ እምክብረ መላእክት ተልዕለ: ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ: በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ።

ወረብ
ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ/፪/
"በብሂለ ኦሆ"/፪/ ፍጡነ አስምአኒ ቃለ/፪/

ዚቅ
አመ ይነፍሕ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ: አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን: ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ: በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት።

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ዕብል ለአስናኒከ ዘመንፈስ: ዘኢይረክቦን ጥረስ: ሚካኤል ረዳኢ ለእለ ውስተ ባሕር ወየብስ: እስመ ረሰይከ ካህነ ምሥዋኡ ክርስቶስ: መፍትው ሊተ ትተንብል ቀሲስ።

ዚቅ
ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ ምስሌሁ: ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ: ዮም ሰማያዊ በምድር አስተርአየ።

ወረብ
ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ/፪/
ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ ስዕንኩ/፪/

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለእስትንፋስከ ቁሱላነ ነፍስ ለአጥዕዮ: ዘይነፍሕ ፄና አንህዮ: ሚካኤል ነዓ ኲናተከ በተረስዮ: ለገቢር ከመ ቀዳሚ ለአርዌ አመፃ ደርብዮ: እስመ ኢኃደገ እንከ ዘትካት እከዮ።

ዚቅ
ወከሢቶ ረከበ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ: ወእከስተ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን: ወእፈውስ ሎሙ ለቁሱላነ ልብ: ወእሰምዮ ለባሕራን ኅሩየ: ዝኬ ዘተነግረ በመዋዕለ ትካት: ለ፳ኤል ኅብስተ መና ዘአውረደ በገዳም: ወርእየቱ ከመ ተቅጻ ወከመ አያያተ መዓር ጥዑም ፈድፋደ።

ወረብ
"ወከሢቶ ረከበ"/፪/ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ/፪/
ወእስብክ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን ወእስምዮ ለባሕራን ኅሩየ/፪/

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለአጻብኢከ መጽሐፈ እለ ለክዑ: ዕጒለ አባግዕ እምኖሎት በጊዜ ተመልዑ: ሚካኤል አንተ ለንጉሠ ነገሥት ካህነ ምሥዋኡ: አሣዕነ መድኃኒት ለእገርየ አጻብኢከ ይቅጽዑ: ከመ በፍናውየ የኀዝ ለሰላም ቅብዑ።

ዚቅ
ቅዱሳት አጻብኢከ ለጽሒፈ መጽሐፍ እለ ተቀንያ: ወብጹዓት አዕይንቲከ ምስጢረ መለኮት ዘርእያ: ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ።

ወረብ
ምስጢረ መለኮት ዘርእያ አዕይንቲከ/፪/
ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ "ሚካኤል መልአክ"/፪//፪/

መልክዐ ሚካኤል
አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክዕከ ኲሉ: ለለአሐዱ አሐዱ ዘበበክፍሉ: ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ: ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኃ ሰማያት ዘላዕሉ: ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ።

ዚቅ
መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል: ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ: አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዓቢይ።

ወረብ
መልአከ ሰላምነ/፬/
ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሰአል በእንቲአነ/፪/

ምልጣን
አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ: ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ: ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ: ወሪዶ እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ።

አመላለስ
ወሪዶ እመስቀሉ/፪/
እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ/፬/

ወረብ
አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ/፪/
ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ/፪/

እስመ ለዓለም
እምድኅረ ተንሥአ እሙታን ዓርገ ውስተ ሰማያት በስብሐት አምላከ ምሕረት: ወተቀብልዎ አዕላፋ አዕላፋት: ወሚካኤል ሊቀ መላእክት በንፍሐተ ቀርን እምኀበ እግዚአብሔር: ስብኩ ትንሣኤ ውስተ ኲሉ ምድር።

ዓዲ (ወይም)
እስመ ለዓለም
ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ: አዓርግ ሰማየ አቡየ ወአቡክሙ: ኀበ አምላኪየ ወአምላክክሙ: ዘንተ ይቤሎሙ ዓርገ ውስተ ሰማያት: ካዕበ ይመጽእ በዘዚአሁ ስብሐት: ሠርጎሙ ለሐዋርያት ብርሃኖሙ ለእለ ውስተ ጽልመት: መድኃኔ ነገሥት ክብሮሙ ለመላእክት ኖላዊሆሙ።

አመላለስ
በንፍሐተ ቀርን እምኀበ እግዚአብሔር/፪/
ስብኩ ትንሣኤ ውስተ ኲሉ ምድር/፪/
ኦ አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ዕቀብ ሕይወተነ ወሥረይ ኀጢአተነ፤
አድኀነነ ወባልሐነ ከመ ኢይርከብ ኃይለ ላዕሌነ ዝንቱ ደዌ ዘኮነ በመዋዕሊነ፡፡
ክፍለነ እምበረከትከ ቅድስት፡ በጸሎተ ኲሎሙ ቅዱሳን እለ አሥመሩከ እምፍጥረተ ዓለም፡፡
@yeberhanljoche
#ቅዱስ_ላሊበላ

📖ሰኔ ፲፪
https://t.me/yeberhanljoche

ቅዱስ ላሊበላ የተወለደው በላስታ ሮሃ ቤተመንግሥት በዋሻ እልፍኝት ውስጥ ታህሳስ ፳፱ በ፲፩፻ወ፩ ዓ/ም ሲሆን በዛሬው ዕለት ጻድቁ ንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ ያረፈበት ነው።
ይህ ቅዱስ ጌታችን የጠጣውን መራራ ሐሞት እያሰበ ዓርብ ዓርብ ኮሶ ይጠጣ ነበር፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ኢየሩሳሌም ወስዶ ቅዱሳን መካናትን፤ ወደ ሰማይም ወስዶ የቤተ መቅደሶቹን አሠራር አሳይቶታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የሚሠራበትን እግዚአብሔር እንዲገልጥለት ሱባኤ ቢገባ ቤተ ማርያም ከተፈለፈለችበት ቦታ የብርሃን ዐምድ ተተክሎ አይቷል።
ቅዱስ ላሊበላ ጎጃም በመሔድ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን ተምሯል። ላሊበላ ከወንድሙ ቀጥሎ እንደሚነግሥ ትንቢት ተነግሮ ስለነበር ንጉሡ ሊገድለው ምክንያት ይፈልግበት ነበር፡፡ በእናትም በአባትም እኅት የምትሆነው፣ ለላሊበላ ግን በአባት ብቻ እኅት የሆነችው ላሊበላን ለመግደል አጋጣሚ ትጠብቅ ነበር፡፡ ቅዱስ ላሊበላ ጌታችን መራራ ሐሞት መጠጣቱን እያሰበ ዓርብ ዓርብ ከጾመ በኋላ ኮሶ ይጠጣ ነበርና እኅቱ አጋጣሚውን በመጠቀም መርዝ ጨምራ ሰጠችው።
ለቅዱስ ላሊበላ መርዝ ጨምራ የሰጠችውን እርሱ ከመጠጣቱ በፊት ያገለግለው የነበረ ዲያቆን ሲቀምሰው ወዲያው ሞተ፡፡ ዲያቆኑ ያስመለሰውን የጠጣው ውሻም ወዲያው ሞተ፡፡ ቅዱስ ላሊበላም አገልጋዩ ለእሱ የተዘጋጀውን መርዝ ጠጥቶ እንደሞተ ባየ ጊዜ መርዙን ጠጣው፡፡ የጠጣው መርዝም ከሆዱ ውስጥ ሆኖ ያሰቃየው የነበረውን አውሬ አወጣለት። እሱም በተአምር ተረፈ።
በዚህ ምክንያት ቅዱስ ላሊበላ ለሦስት ቀናት አያይም አይሰማም ነበር። በዚህ ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ሰማይ ወስዶ ሰባቱን ሰማያት አሳየው። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በመጀመሪያ አክሱም ከዚያም ኢየሩሳሌም ወስዶ በዚያ የነበሩትን ቅዱሳት መካናት አሳየው። ኢትዮጵያውያን ወደ ኢየሩሳሌም መንፈሳዊ ጉዞ ሲያደርጉ ይደርስባቸው የነበረውን መከራ እያሰበ ያዝን ነበርና በሮሐ ዐሥራ አንድ አብያተ ክርስቲያናትን ፈለፈለ።
ቅዱሱ አባት በሃይማኖት ብቻ ሳይሆን በድፕሎማሲም የተዋጣለት ስለነበር በቱርኮች ተይዞ የነበረውና በኢየሩሳሌም የሚገኘው ዴር ሡልጣን ገዳማችን እንዲመለስልን አድርጓል። ከውቅር አብያተ ክርስቲያናት በተጨማሪ በርካታ ቤተ ክርስቲያኖችንም ሠርቷል፣ ንግሥናን ከክህነት፣ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አስተባብሮ የያዘው ቅዱስ ላሊበላ በዚች ሰኔ ፲፪ ቀን አርፏል።
🙏የቅዱሱ አባት የቅዱስ ላሊበላ ረድኤት በረከት ይደርብን አሜን!!🙏

ለሌሎች መረጃዎች👇
https://t.me/@yeberhanljoche
“እንደ እባብ ልባሞች ኹኑ” /ማቴ.10፡16/

እባብ ራሱን (ጭንቅላቱን) ለማዳን ሲል ሌላው ሰውነቱን ለአደጋ እንደሚያጋልጥ ኹሉ አንተም እንዲህ አድርግ፡፡ ሃይማኖትህን ለመጠበቅ ስትል ሀብትህን ወይም ሰውነትህን ወይም የዚህ ዓለም ሕይወትህን ወይም ያለህን ኹሉ እንኳን መስጠት ካለብህ ይህን በማድረግህ በፍጹም አትዘን! አንተ ሃይማኖትህን ይዘህ ወደ ወዲያኛው ዓለም ስትሔድ እግዚአብሔር ደግሞ ኹሉም ነገር እጅግ ውብ አድርጎ ይመልስልሃል፤ ሰውነትህን በታላቅ ክብር ያስነሣልሃል፤ ከሀብት ከንብረት ይልቅም ከመግለጽ ኃይል በላይ የኾኑ በጎ በጎ ነገሮችን ይሰጥሃል፡፡ ኢዮብ ዕራቁቱን ኾኖ በአመድ ላይ ከሞት እልፍ ጊዜ የሚከፋ ሕይወትን እየመራ የተቀመጠ አይደለምን? ነገር ግን ሃይማኖቱን ስላልጣለ አስቀድሞ የነበረው ኹሉ እጅግ በዝቶ ተመልሶለታል፤ ጤናውና ውብ የኾነ ሰውነቱ፣ ልጆችን፣ ሀብቱን፣ ከዚህ ኹሉ የሚበልጥ ደግሞ አክሊለ ትዕግሥትን አግኝቷል፡፡
@yeberhanljoche
ሁለት ሰዎች በአንድ ጉዳይ አብረው ይጸልያሉ። አንደኛው ጸሎቱ ተመለሰለት፣ አንደኛው ሳይመለስለት ቀረ። በዚህ ጊዜ ጸሎቱ ያልተመለሰለት፡- “ጌታ ሆይ ሁለታችንም እኩል ጸለይን ለእርሱ ሰጥተኸው ለእኔ የከለከልከኝ ለምንድን ነው?” አለው። እግዚአብሔርም፡- “ለእርሱ ባልሰጠው ይጠፋል፣ ላንተ ከሰጠሁህ ትጠፋለህ” አለው።

እግዚአብሔር ከራሳችን በላይ እኛን ያውቀናል። ለአንዳችን በመስጠት፣ አንዳችንን በመከልከል ዕድሜያችንን ያረዝመዋል። መስጠቱም መንሣቱም ሁለቱም ለፍቅር ነውና ስለሆነልን ስለሚሆንልንና ስላልሆነልን ነገር ሁሉ ተመስገን ማለትን አንርሳ፡፡
@yeberhanljoche
ከቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ውድ ቃላት ውስጥ

"ሁሉን ነገር በኢየሱስ ክርስቶስ ታደርጋለህ"(Epistle Of Ephesians Chapter 8)

"ክርስትና የዝምታ ነገር ብቻ አይደለም ነገርግን ታላቅነት የሚገለጥበት ነው"
(Epistle Of Romans Chapter 3)

"የዓለም ተድላዎች ሁሉ እና የዚህች ምድር መንጎስታት ሁሉ ምንም አይጠቅመኝም በዓለም ዳርቻ ሁሉ ከመገዛት ይልቅ ለኢየሱስ ክርስቶስ መሞቴ ለእኔ ይሻላል"
(Epistle Of Romans Chapter 6)

"የእግዚአብሔርን እንጀራ፣የሰማይን እንጀራ፣የሕይወትን እንጀራ እፈልጋለሁ እርሱም ከዳዊት እና ከአብርሃም ዘር በኋላ የተገኘው የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ስጋ ነው እና የማይጠፋ ፍቅር እና የዘለዓለም ሕይወት የሆነውን የእግዚአብሔር መጠጥ ማለትም ደሙን እፈልጋለሁ"
(Epistle Of Romans Chapter 7)

"ክርስቶስን አለማመን ከባድ ነው የሐዋርያትን ስብከት ውድቅ ማድረግ ከባድ ነው"
(Epistle Of Philadelphia Chapter 8)

"አንድ ክርስቲያን በራሱ ላይ ስልጣን የለውም ነገርግን ሁልጊዜ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ዝግጁ መሆን አለበት"
(Epistle Of Polycarp Chapter 7)

ይህ ቅዱስ እንዳውም ቴዎፎሮስ(ክርስቶስ የተሸከመው)ተብሎ የሚጠራ እና
ለክርስቶስ ሲል በሮም አደባባይ በትራጃን አማካኝነት ለአንበሶች የተጣለ እና በአንበሶች ተበልቶ ሰማዕትነቱን የፈፀመ ነው።

ወንጌሉንም በተግባር የኖረ ነው በሰባት መልዕክቶቹም በብዛት ለካህናተ ቤተክርስቲያን እንድንታዘዝ እና የካህናትን ክብር እንዲሁም ከተለያዩ የስህተት አስተምህሮዎች ስለመጠበቅ አስተምሮናል ባጠቃላይ ሐዋርያት ያፀኗት በክርስቶስ ኢየሱስ ራስነት የተመሰረተችው ቤተክርስቲያን በሐዋርያነ አበው ዘመን የነበራትን አቋም በመልዕክቶቹ ውስጥ መገንዘብ እንችላለን እንማራለን።

ይህ ቅዱስ ታሪኩ አስተማሪ ነው ደግሞም ታሪኩን ስናጠና ቤተክርስቲያን ስንት ፈተና አሳልፋ ለዚህ ጊዜ መድረሷን እና በዛ ጊዜ የነበረውን ማለትም የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ክርስትና ሒወት እናይበታለን።

ይህ ቅዱስ በሀገራችን ውስጥ ከጓደኛው ከቅዱስ ፖሊካርፐስ ጋር ሰላሌ ኦሮሚያ ውስጥ ቤተክርስቲያን አለው።
ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ሰማዕት የሆነበትም ቀን ሐምሌ ፯ ቀን በ፻፯ዓ/ም ነው።
በረከቱ ይድረሰን

ይህ ቅዱስ ለጓደኛው ለቅዱስ ፖሊካርፐስም ጭምር መልዕክት የፃፈ ሲሆን የፃፋቸው መልዕክታትም
፩ወደ ኤፌሶን ክርስቲያኖች
፪ወደ ማግኔዥያ ክርስቲያኖች (አሁን በዚህ ስም ለምትጠራው አገር ሳይሆን ጥንት የክርስቲያኖች መኖሪያ ለነበረችው እና ዛሬ በቱርክ ውስጥ ለምትገኝ ቦታ ነው)
፫ወደ ሮም ክርስቲያኖች
፬ወደ ትራሊያ ክርስቲያኖች
፭ወደ ፊላዴልፊያ ክርስቲያኖች
፮ወደ ሰርመኔስ ክርስቲያኖች
፯ወደ ጓደኛው ቅዱስ ፖሊካርፐስ ነው።
@yeberhanljoche
@yeberhanljoche
@yeberhanljoche
#አንተ_አንቺ_ማለት ...

ፀሀይዋን ተመልከታት አታምርም ? ጨረቃዋስ ከዋክብቱስ ዛፎቹ ወንዙና ተራራውስ አያምሩም ? ያምራሉ እኚ ሁሉ ግን ያልፉሉ አንተ ግን በሞት ከዚህ አለም ብትለይ እንኳን በሰማይ ለዘላለም ትኖራለህ ፈጣሪ ፍጥረታትንን ሁሉ በቃሉ በመናገር እና በሀሳብ (በሀልዮ) ሲፈጥር አንተን ግን በእጁ አሽሞንሙኖ ፈጥሮሀል አንተ ማለት ክርስቶስ እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለው ማንም ሚከፍትልኝ ቢኖር ገብቼ እራቴን ከእርሱ ጋር እበላለው ብሎ የተናገረልህ ነህ ፈጣሪ አለምን ከፈጠረበት ጥበብ ይልቅ አለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል ተብሎ የተነገረልህ ዋጋ የከፈለልህ የመንግስቱ ወራሽ ውድ ልጁ ነህ ምን አልባት ዛሬ በተለያየ ሱስ ተይዘህ ይሆናል ምን አልባት ስራ በማጣት ፍቅረኛ በማጣት ትሰቃይ ይሆናል ምን አልባት ቤተሰብህ ወገንህ ተስፉ ቆርጦብህ ይሆናል ምን አልባት ሞትህን እየተመኘህ ይሆናል ግን አይዞህ ፈጣሪ በአንተ የጀመረውን ስራ ሳይጨርስ አትሞትም

ሰው ተስፉ ቢቆርጥብህ እራስህም ተስፉ ብትቆርጥ የፈጠረህ በአንተ ላይ ተስፉ አይቆርጥብህምና አይዞህ 1 ጠጠር አንስተህ ተራራ ላይ ብትወረውር ተራራው ምንም አይሆንም ጠጠሩ ተንከባሎ እግሩ ስር ይሆናል ያን ጠጠር አንስተህ መስታወት ላይ ብትወረውረው ግን መስታወቱ ይሰባበራል ጠጠሩን በችግር እንመስለውና ችግር ወዳንተ ሲመጣ እንደ መስታወቱ አትሰባበር እንደ ተራራው በቁጥጥር ስር አውለው 1 የተለኮሰ የክብሪት እንጨት ጭድ ላይ ብትጥለው ይቀጣጠላል ውሀ ላይ ብትጥለው ግን ውሀው ያጠፉዋል የሚያቃጥሉ ነገሮች በህይወትህ ውስጥ ሲከሰቱ እንደ ጭድ አትቀጣጠል እንደ ውሃው አጥፉቸው

እህቴ ምን አልባት ለስራ ጉዳይ በተለያየ ሀገር ውስጥ ሆነሽ ይሆናል ያለሽው መፈጠርሽ ሴትነትሽም አስጠልቶሽ ይሆናል። ግን ክርስቶስ ወደ አለም ሲመጣ ምድራዊ እናት እንጂ አባት አላስፈለገውም የሴት ልጅ ተብሎ እስኪጠራ ድረስ ማርያም ብቻዋን ነው ያሳደገችው። በኛ ቤተክርስቲያን ህንፃ ቤተክርስቲያኑ ተሰርቶ አለቀ የሚባለው ጉልላቱ ተሰርቶ ሲያልቅ ነው ። ፈጣሪም ፍጥረትን ሁሉ ፈጥሮ ሲጨርስ አዳምን ፈጠረ በመጨረሻም ከጎኑ ሄዋንን ወይም አንቺን የስነ ፍጥረት ጉልላት አርጎ ፈጠረሽ ስለዚህ እህቴ ክብርት ፍጥረት ነሽና ደስ ይበልሽ
@yeberhanljoche