ውሉደ ብርሀን ሰ/ት/ቤ/ት🙏(ጫንጮ)
766 subscribers
84 photos
4 files
98 links
ሰንበት ትምህርት ቤት የመልካም ወጣት የመልካም ትውልድ መፍለቂያ ናት! ትውልድን ለበጎ ነገር የምታበቃ ናት፡፡


የጫንጮ ከተማ ደ/ብ/ቅ/እግዚአብሔር አብ እና ደ/ሲ/ቅ/ ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ ው/ብ/ሰ/ት/ቤት ቻናል
ለሀሳብ እና አስታየት @weldebirhanbot @ty1921 ይጠቀሙ

ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ መልካም ነው፡፡
Download Telegram
ይቅርታ ምንድን ነው ?

የይቅርታ ጥጉስ እስከምን ነው ?

“ትርጉም የሌለው ይቅርታ ፈርዶ ከመግደል አይለይም” ዛሬ በህይወት ባይኖሩም ትምህርታቸው ግን ህያው ሆነው እንዲኖሩ አድርጓቸዋል ፡- ብጹዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ፡፡

ሰው የግጭት አካል ነው፡፡ ፍጹም ተሆኖ አይኖርም፣ አይቻልምም፡፡ የሰው ሰውነቱ የሚለካው በስሁትነቱ ነው፡፡ ጻድቅ ጻድቅነቱ ሰባት ጊዜ ወድቆ ሰባት ጊዜ መነሳቱ የጽድቁ ልኬቱ እንደሆነ ሁሉ ማለቴ ነው፡፡ ይቅርታን መጠየቅ መጸጸት ሲሆን ይቅርታን ማድረግ ግን ታላቅነት ነው፡፡ ማመን ቀላል ሲሆን መታመን ደግሞ እጅግ ከባድ ሸክም ነው፡፡ ማመን ኃላፊነት መወጣት ነው፣ መታመን ግን ኃላፊነትን መሸከም ነው፡፡ ይቅርታ በማድረግ ውስጥ “ፍጹምነት” ሊኖር ግድ ነው፡፡ ይቅርታን የምታደርጉ ሁሉ ሸክምን ይቅርታችሁን ጠይቋችሁ ለሰጣችሁት ሰው እንዳሸከማችሁት እመኑ፡፡ ቅርታን ስታደርጉ “እዳው በአንተ ላይ ይሁን” ማለታችሁ ነው፡፡ ስለሆነም ወደ ኋላ ከመመለስ ይልቅ እንደ ጳውሎስ በፊታችሁ ያለውን ለመያዝ ሩጡ እንጂ ያስተፋችሁትን ቆሻሻ መልሳችሁ ለመቁጠር ወደ ኋላ ለመመለስ ቁጥር አትጀምሩ፡፡

እግዚአብሔር መሐሪ ነው፡፡ ምን ድረስ ? ልጁን ኢየሱስን እስከመስጠት ድረስ፡፡ ይቅር የምንል ሁሉ ይቅርታ የተደረገልን ነን፡፡ በወንጌል ላይ እዳው ተሰርዞለት በደስታ ዘልሎ ሳይጨርስ እሱ ደግሞ እዳ ያለበትን ባለእዳውን ሲመለከት የተሰረዘለት እዳው ተረስቶት ባለእዳውን ያነቀውን ሰው አስቡት፡፡ የእሱ እዳ እንደተሰረዘለት እሱም የሌላውን እዳ መሰረዝ ሲኖርበት እሱ ግን ባለ እዳዬ ያለውን በማነቁ ወደ ወኅኒ መጣሉን አስታውሱ፡፡ ከክፋት ሁሉ የከፋ ክፋት የሰጠነውን ይቅርታ መልሰን ለመንጠቅ የምናደርገው ነው፡፡ ይቅርታ ያልነውንና . በደል እያነሳን ማቁሰል እግዚአብሔርን አለማወቅ ክፉ ቂመኝነትም ነው፡፡ የእኛ ድርሻ በይቅርታ ውስጥ የይቅርታን ጌታ አስታውሶ በንጹህ ኅሊና መኖር ነው፡፡ “ትቼልሃለው” ብሎ ትቶ መኖር እንዴት ያለ ክርስትና መሰላችሁ ! እዳን ለባለ እዳ ተዉለት እንጂ የእዳ ተሸካሚ አትሁኑ፡፡ ክርስቶስ እዳን ሰረዘ እንጂ አልቆጠረም፡፡ ታዲያ የሰረዝነውን እዳ መልሰን የምንቆጥር እኛ ከማን ተምረን ነው ? በማመን ወደፊት ሂዱ እንጂ በመጠራጠር ወደ ኋላ አትመለሱ፡፡ እግዚአብሔር ተቆጣጥሮልን እንጂ እኛ ተከታትለን የምናሸንፈው ነገር የለም፡፡

ይቅርታ ዋጋ አውጥቷል፡፡ ይቅርታ ዋጋ ያeወጣልም ፡፡ የምንወደውን ሰው ይቅር ለማለት ዋጋ እንከፍላለን፡፡ ዋጋው የቀደመውን ፍቅርና ለይቅርታ ራቁቱን የተሰቀለውን ማሰብ፡፡ በአንድ ወቅት ቅዱስ ጴጥሮስ ወደ ጌታ ቀርቦ “ጌታ ሆይ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት?” አለው፡፡ ጴጥሮስ ግን ለጠየቀው ጥያቄ መልስ ከመጠበቅ ይልቅ የውስጥ ደንዳናነቱ እንዲጸድቅለት በማሰብ ይመስላል በትንሽዋ አእምሮው ያለውን የራሱን አስተያየት ሰጠ፡፡ “እስከ ሰባት ጊዜ ነውን?” በዚያ የመስቀል ስቃይ ላይ ሆኖ የሰቀሉትን ይቅር ያለና ለሰቃዮቹ እንኳን የመዳንን ሀብት የሰጠ ጌታችን ግን እንዲህ አለ “እስከ 70 ጊዜ 7 እንጂ እስከ 7 ጊዜ አልልህም” ማቴ 18 ÷ 21-22 በሂሳብ ስሌት መሰረት በቀን 7 x 70 = 490 ጊዜ ይቅር ማለት ይጠበቅብናል፡፡ እውነተኛ ፍቅር ይህ ነው፡፡ እውነተኛ ፍቅር ይሰርዛል እንጂ አያከማችም፣ ኃጢአትን ያፈሳል እንጂ አይቋጥርም፣ ያቅፋል እንጂ አይወጋም፣ ያክማል እንጂ አያደማም፡፡ ይቅርታ ማድረግ ትክክለኛ ትርጉሙ “መተው” ወይንም “መርሳት” መሆኑን ክርስቶስ ተማሩ፡፡ ጠቢቡ እንዲህ ይላል “ሰውን ጠቢብ አእምሮው ከቁጣ ያዘገየዋል፣ በደለኛውንም ይቅር የሚል ክብር ይሆንለታል” ምሳ 19÷11

የይቅርታ ሰዎች የሆናችሁ የመንግስቱ ውራሾች ያድርገን አሜን መልካም ቀን
ውሉደ ብርሀን(የብርሀን ልጆች) ሰ/ት/ቤ/ት ጫንጮ ቅ/እግዚአብሔር አብ:
ሰላም የተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ🙏
@yeberhanljoche @yeberhanljoche
@yeberhanljoche @yeberhanljoche
Forwarded from ተዋህዶ
የመንፈሳዊ ስነ ፅሁፎች መገኛ ምርጥ ቻናል
join በማለቶ አይፀፀቱም በተለያዩ መንገዶች በግጥም ቢሉ በመነባነብ በጭውውት ቢሉ በእንካ ሰላምታ በብዙ መንገድ ስለ እምነቶ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሚያቁበት ለየት ያለ ቻናል።

ለመቀለቀል ከታች መርጠው ይጫኑ
👇
​​እንኳን ለታላቁ ገዳማዊ አባ ጳውሊ እና ለጻድቁ አባ ለንጊኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ታላቁ ቅዱስ ጳውሊ

††† በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ "ታላቁ /ዐቢይ/ THE GREAT" የሚል ስም የሚሰጣቸው አባቶች የተለዩ ናቸው። አንድም እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን የሠሩ ናቸው። በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ስም ከሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን እንለይበታለን።

ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው። በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል። ሕይወቱ በጐላ በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው።

ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል። በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም (በበርሃ) ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል።

ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለአርባ ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል፤ አስተምሯል። በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ (ኤሌዎን ዋሻ) በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት።

ከጌታ ዕርገት በኋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ። አኗኗራቸውም በቡድንም በነጠላም ሊሆን ይችላል። ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው። ይህም ሲያያዝ እስከ ሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ደረሰ። በዚህ ዘመን ግን አባ ጳውሊ የሚባል ንጹሕ ክርስቲያን ይህንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው። ለሰማንያ ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ "የባሕታውያን አባት" ተባለ። ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ።

ይህ ከሆነ ከሃያ ዓመታት በኋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት። በቅዱስ ሚካኤል አመንኳሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ። ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ።

እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል። ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል።

አንድ ቀን ቅዱስ እንጦንስ (የመነኮሳት ሁሉ አባት) እንዲህ ሲል አሰበ። "በውኑ በበርሃ ለበርካታ ዘመናት በመኖር ከእኔ የሚቀድም (የሚበልጥ) ሰው ይኖር ይሆን?" ይህንን ሃሳቡን ገና ሳይጨርሰው ቅዱስ ሚካኤል ወደ እርሱ ዘንድ ደረሰ።

"እንጦንስ ሆይ! ከእኔ የሚቀድም የበርሃ ሰው ይኖር ይሆን ብለህ አስበሃል። በእርግጥም ከአንተ ሃያ ዓመታትን ቀድሞ ወደ በርሃ የገባ፣ በቅድስናው ፈጣሪውን ያስደሰተ፣ ዓለም ከነ ክብሯ የእግሩን መረገጫ ያህል እንኳ የማትመጥነው በጸሎቱና በምልጇው ዓለም የምትጠበቅለት ሞገስን የተሞላ አንድ ሰው በበርሃ ስላለ ሒድና ተመልከተው።" ብሎት ተሠወረው።

ቅዱስ እንጦንስም ከሰማው ነገር የተነሳ እየተደነቀ ተነሳ። እርሱ ካለበት በርሃ በራቀ መንገድም ለቀናት ተጉዞ አንድ በዓት (ዋሻ) በር ላይ ደረሰ። በበሩ አካባቢ የሰውና የአራዊት ኮቴ ተመልክቶ በሩን ጸፋ (ቆፈቆፈ)። በውስጥ ያለው አረጋዊ ሰው ግን ትልቅ ድንጋይ ገልብጦ በሩን አጠበቀው። ለሰማንያ ዓመታት ሰውን አይቶ አያውቅምና ሰይጣን ሊያታልለኝ መጥቷል ብሎ አስቧል። ቅዱስ እንጦንስ ግን "ኃሠሥኩ እርከብ ጐድጐድኩ ይትረኃው ሊተ - ሽቻለሁና ላግኝ፤ ደጅ መትቻለሁና ይከፈትልኝ።" ሲል አሰምቶ ተናገረ።

ቅዱሱ ገዳማዊም ሰው መሆኑን ሲያውቅ በሩን ከፈተለትና ወደ ዋሻው አስገባው። መንፈሳዊ ሰላምታንም ተለዋወጡ። ሲመሽም ቅዱስ እንጦንስ ሽማግሌውን ገዳማዊ "ስምህ ማን ነው?" ቢለው "ስሜን ካላወክ ለምን መጣህ?" ሲል መለሰለት።

ያን ጊዜ ቅዱስ እንጦንስ ቀና ብሎ ሰማይን ሲመለከት ምሥጢር ተገለጠለትና "ቅዱስ ጳውሊ ሆይ! ከአንተ ጋር ያገናኘኝ ፈጣሪ ይክበር፤ ይመስገን።" ሲል ፈጣሪውን ባረከ። ቅዱስ ጳውሊም መልሶ (በጸጋ አውቆት) "አባ እንጦንስ ሆይ! እንኳን ደህና መጣህ።" አለው። ሁለቱም ደስ ብሏቸው ፈጣሪያቸውን እያመሰገኑ ተጨዋወቱ።

ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም ዓይነት የቅድስና ሕይወት የመጀመሪያ የምትላቸው አላት። ለምሳሌ፦
የመጀመሪያው ሐዋርያ ቅዱስ እንድርያስ፣ የመጀመሪያው ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ፣ የመጀመሪያው ባሕታዊ (ገዳማዊ) ቅዱስ ጳውሊ እና የመጀመሪያው መነኮስ ቅዱስ እንጦንስን ማንሳት እንችላለን።

ቅዱስ ጳውሊ የተወለደው በሰሜናዊ ግብጽ በእስክንድርያ ከተማ ሲሆን ዘመኑም ሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ነው። ወላጆቹ ባለጸጐች ነበሩ። ቅዱሱንና ታላቅ ወንድሙን አባ ጴጥሮስን ወልደዋል። ሁለቱ ክርስቲያን ወንድማማቾች ገና ወጣት ሳሉ ወላጆቻቸው ሞቱባቸው። ሃዘናቸውን ፈጽመው ሃብት ሲካፈሉ ግን መስማማት አልቻሉም።

ምክንያቱ ደግሞ ትልቁ ጴጥሮስ ደህና ደህናውን እቃ ወስዶ መናኛ መናኛውን ለትንሹ ለጳውሎስ (ጳውሊ) መስጠቱ ነበር። ስለዚህ ነገር ተካሰው ወደ ፍርድ ቤት ሲሔዱ ግን መንገድ ላይ አንድ ባለጸጋ ሙቶ ደረሱ።

ቆመው ሳሉም ቅዱስ መልአክ ሰው መስሎ ጳውሊን "ይህ ሰው ባለጸጋ ነው። በገንዘቡ የሰጠውን ፈጣሪ ሲበድልበት ኑሮ እነሆ ተሸኘ። በሰማይም አስጨናቂ ፍርድ ይጠብቀዋል።" ሲል ነገረው።

በዚያች ቅጽበት የወጣቱ ጳውሊ ሐሳብ ተለወጠ። ወደ ወንድሙ ተመልሶ "ወንድሜ ሆይ! ሁሉ ንብረት ያንተ ይሁን።" ብሎት ከአካባቢው ጠፋ። በመቃብር ሥፍራ ለሦስት ቀናት ያለ ምግብ ጸልዮ የእግዚአብሔር መልአክ ሰው ወደ ማይደርስበት በርሃ ወሰደው።

በዚያም ምንጭ ፈለቀችለት። እየጾመ ይጸልይ ይሰግድ ገባ። ሁሌ ማታ ግማሽ ሕብስት ከሰማይ እየወረደለት ቅዳሜና እሑድ መላእክት እያቆረቡት ለሰማንያ ዓመታት ኖረ። (አንዳንድ ምንጮች ግን ለዘጠና ዓመታት ይላሉ።) ከቅዱስ እንጦንስ ጋር የተገናኙትም ከዚህ በኋላ ነው።

ከቅዱስ እንጦንስ ጋር በነበራቸው የሁለት ቀናት ቆይታም ቅዱስ ጳውሊ ብዙ ትንቢቶችን ተናግሯል። በዚህች ቀን ሲያርፍም መቃብሩን አናብስቱ ቆፍረዋል። ቅዱስ እንጦንስም በክብር ቀብሮታል። ለሰማንያ ዓመታት የለበሳት የዘንባባ ልብሱም ሙት አስነስታለች።

ጻድቅ፣ ቡሩክ፣ ቀዳሚው ገዳማዊ፣ መላእክትን የመሰለና የባሕታውያን ሁሉ አባት ለተባለ ለቅዱስ ጳውሊ ክብር ይገባል!

ዝክረ ቅዱሳን
https://t.me/yeberhanljoche
​​ጾመ ሰብአ ነነዌ
በርእሰ ደብር ብርሃኑ አካል

ጾመ ነነዌ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዷ ስትኾን የምትጾመውም ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ይህቺ ጾም የምትጀመርበት ዕለትም ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አይለቅም፡፡ ጾሟ የምትጀመርበት ቀን ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር ፲፯ ቀን ድረስ ነው፡፡

ቀኑ ሲወጣ ወይም ወደ ፊት ሲገፋ ደግሞ እስከ የካቲት ፳፩ ቀን ይረዝማል፡፡ ጾመ ነነዌ በእነዚህ ፴፭ ቀናት ውስጥ ስትመላለስ (ከፍ እና ዝቅ ስትል) ትኖራለች፤ ከተጠቀሱት ዕለታት አትወርድም፤ አትወጣም፡፡ በዚህ ዓመትም የካቲት 7 ቀን ትጀመራለች፡፡

‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሚለው የጽሑፋችን ርእስ እንደሚያስረዳው ይህቺን የሦስት ቀን ጾም የጾሟት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪/ ፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የኾነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚሸፈን ነበር፡፡ በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶባት ነበር /ዮናስ ፬፥፲፩/፡፡

በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኀጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ሲል ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር መክሮ፣ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ላከው /ሉቃ.፲፩፥፴/፡፡

ዮናስ የስሙ ትርጕም ‹ርግብ› ማለት ነው፡፡ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይ ነው፡፡ ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፡፡ አባቱም አማቴ ይባላል፡፡ ኢዮርብዓም ሶርያውያንን አባሮ የእስራኤልን ድንበር እንዲመልስ ነቢዩ ዮናስ ትንቢትን ተናግሯል /፪ኛነገ.፲፬፥፳፭፤ ዮናስ ፩፥፩/፡፡

ነቢዩ ኤልያስ ያስነሣው የሰራጵታዋ መበለት ሕፃን ነቢዩ ዮናስ እንደ ኾነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል /፩ኛ ነገ.፲፯፥፲፱/፡፡ መድኀኒታችን ክርስቶስም የዮናስን ከዓሣ ኾድ መውጣት የራሱ ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎ ነግሮናል /ማቴ.፲፪፥፲፱-፵፪፤ ሉቃ.፲፩፥፴-፴፪/፡፡

እግዚአብሔር ‹‹ሔደህ በነነዌ ላይ ስበክ›› ባለው ጊዜ ነቢዩ ዮናስ ‹‹አንተ  መሐሪ ነህ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ››  ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡

እግዚአብሔርም ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩ ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ ጥፋቱን ተገንዝቦ ‹‹ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ ስለ ኾነ  ንብረታችሁን  ሳይኾን እኔን  ወደ ባሕር ጣሉኝ›› ብሎ ተማጸናቸው፡፡

እነርሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ፣ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳይደረግብን አይኾንም›› አሉ፡፡

ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ በተጣጣሉ ጊዜም ዕጣው በዮናስ ላይ ስለ ወጣ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ወደ ነነዌ አደረሰው፡፡

እግዚአብሔር የቅል ተክልን ምሳሌ በማድረግ ቅጠሉ በመድረቁ ዮናስ ባዘነ ጊዜ ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ ያሳዝኑኛል›› በማለት ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መኾኑን አስረድቶታል፡፡

ዮናስም ነነዌ መሬት ላይ መድረሱን ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ፤ የነነዌ ሰዎችንም ‹‹ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡ ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ኾኖ ከላይ ታይቶአል፡፡

የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል /ትንቢተ ዮናስን በሙሉ ይመልከቱ/፡፡ ታኅሣሥ ፭ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል  ‹‹ወበልዐ አሐደ ኀምለ›› በማለት ንስሐ ያልገቡ አንድ አገር ያህል ሰዎች በእሳቱ እንደ ጠፉ ይነግረናል፡፡

ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ናት፤ በሦስት ቀናት ጾምና ጸሎት ንስሐ የገቡ የነነዌ ሰዎች ከጥፋት እንደ ዳኑ ዅሉ፣ በብሉይ ኪዳን አስቴር ሦስት ቀን ጾማ፣ ጸልያ በእስራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች /አስ.፬፥፲፭-፲፮/፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ ሕፃኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት ቀን ፍለጋ በኋላ በቤተ መቅደስ አግኝታዋለች /ሉቃ.፪፥፵፮/፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ በሰጠው ምላሽ መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መኾኑን ገልጿል /ሉቃ.፲፫፥፴፪/፡፡

ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው፡፡ ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይኾን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡

በእርግጥ እግዚአብሔር ሌላ የሚልከው ነቢይ አጥቶም አይደለም፤ እርሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለ ፈለገ እንጂ፡፡ የነነዌ ሰዎች የተነሳሕያን ምሳሌ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን  ‹‹አንተ  ላልደከምክበት  እና በአንድ  ቀን በቅሎ  ላደገ ቅል  ስታዝን እነሆ  በታላቂቱ  ነነዌ ከተማ  ያሉ ከአንድ  መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ  የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ  ያሳዝኑኛል›› ያለው፡፡

ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ይህን እና ሌሎች አጽዋማትን እንድንጾም የወሰኑልን ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሕጉ የተዘጋጀልን እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም ጾመን፣ ጸልየን ከኀጢአታችን እንነጻ ዘንድ ነው፡፡ ዛሬ ዓለማችን በኀጢአት ማዕበል እየተናወጠች ባለችበት ወቅት እኛም እንደ ነነዌ ሰዎች ከበደላችን ብንመለስ እና ንስሐ ብንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለ ኾነ ‹‹ወደ እኔ  ተመለሱ፤  እኔም ይቅር  እላችኋለሁ፤›› ይለናል፡፡

ስለኾነም በነቢዩ ዮናስ ላይ የተደረጉ ተአምራትንና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመኾኑን በማስተዋል፣ ለነነዌ ሰዎች የወረደውን ምሕረት በመገንዘብ ለእግዚአብሔርም ኾነ ለሃይማኖት አባቶች እና ለወላጆቻችን መታዘዝ ይገባናል፡፡

ስንጾምም እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረት፣ ቍጣውን በትዕግሥት መልሶ በኀጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይልካል፡፡ በመጾማችን ራሳችን ከመዓትና ከመቅሠፍት ከመዳናችን ባሻገር በእኛ በደል ምክንያት አገራችን፣ ዕፀዋቱና እንስሳቱም ሳይቀር ከድርቅና ከቸነፈር ይተርፋሉና፡፡

✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
@yeberhanljoche
💠 #ኢየሱስ_ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። 💠

✧ በወንጌልም ሆነ በተለያዩ የሀዲስ ኪዳን የመልእክት ክፍሎች ውስጥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ተጠቅሶ ይገኛል። እንደውም ማንኛውም ክርስቲያን፥ ኢየሱስ እግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ማመን መቀበል እንዳለበት አጽንኦት ተሰጥቷል፡፡

✧ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቂሳርያ ሀዋርያቱን ሰብስቦ ሰዎች ማን እንደሚሉት በጠየቃቸው ጊዜ አንዳንዶች ኤልያስ ከነብያት አንዱ እንደሆነ እንደሚናገሩ ሲነግሩት እናንተ ማን እንደሆንኩ ትላላችሁ ብሎ ቢጠይቃቸው ክርስቶስ የህያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ቅዱስ ጴጥሮስ ተናግሯል ጌታችንም ቅዱስ ጴጥሮስን አመስግኖ ስጋና ደም እንዳልገለጠለት የሰማዩ አባቱ እንደገለጠለት በመናገር በዚህ በቅዱስ ጴጥሮስ ንግግር ቤተክርስቲያኑን እንደሚመሰርት ጌታ ተናግሯል ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው የሚለው የቅዱስ ጴጥሮስ ንግግር የቤተክርስቲያን መሰረት ነው። የጌታን ማንነት የሚገልጽ እምነታችን መሰረት ነው፡፡

✧ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ የማያምን እንዲሁም ብሎ የማይመሰክር ሰው ክርስቲያን ተብሎ ሊጠራ አይችልም ምክንያቱም የክርስትና መሰረት ይህ ስለሆነ ‹‹ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን። ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ። እርሱም፦ አንዳንዱ #መጥምቁ_ዮሐንስ ፥ ሌሎችም #ኤልያስ ፥ ሌሎችም #ኤርምያስ ወይም #ከነቢያት_አንዱ ነው ይላሉ አሉት።
እርሱም፦ #እናንተስ #እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው።
ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ #አንተ #ክርስቶስ_የሕያው_እግዚአብሔር_ልጅ ነህ አለ። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ #በሰማያት ያለው #አባቴ እንጂ #ሥጋና #ደም ይህን #አልገለጠልህምና #ብፁዕ ነህ። እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።››ማቴ 16፡13-19

ቅዱስ ገብርኤልም እመቤታችንን ለማብሰር በተላከ ጊዜ ከእርሷ የሚወለደው <<ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ>> እንደሚባል ነግሯታል እሷም ይህንን በእምነት ተቀብላ ስግው ቃል/ሰው የሆነ አምላክ/ እግዚአብሄርን በስጋ ወልዳዋለች ስለዚህም ወላዲተ አምላክ ብለን እንጠራታለን፡፡ የሉቃስ ወንጌል 1፡35 ‹‹መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።››

✧ በተለያየም ቦታ አጋንንት እኳን ሳይቀሩ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ መስክረዋል፡፡ ማቴ 8፡29 አይሁድም የእምነታችን መሰረት የሆነውን የእግዚአብሔር ልጅነቱን አልተቀበሉም ነበር፡፡ማቴ 26፡63 ይዘብቱበትም ነበር ማቴ 27፡43 ፡፡ ቅዱስ ማርቆስም ወንጌሉን ሲጀምር እግዚአብሔር ልጅነቱን መስክሮ ነው ማር1፡1፡፡ በተለያየ የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ክፍል ውስጥ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ ተጠቅሷል ይህንንም እናመን ዘንድ ወንጌል እንደተፃፈ ይነግረናል ዮሐ 1፡34 ፤1፡50 ፤6፡69 ፤ 10፡36 ፤11፡4 ፤11፡27 ፤ 19፡7 ፤ 20፡31፡፡

✧ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ይህንን አምኖ እንደተጠመቀ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል ሐዋ 8፡37፡፡ቅዱስ ዮሐንስ በመልእክቱም ኢሱስ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነ ተናግሯል ‹‹ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።››1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፡15፡፡

እንግዲህ ከላይ እንደተመለከትነው መጽሀፍቅዱስ አፅንኦት ሰጥቶ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ በእግዚአብሔር ልጅነቱም ማመን እንዳለብን ይናገራል...

??? ለመሆኑ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ሲባል ምን ማለት ነው ???

✧ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ሲባል መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን እግዚአብሔር ነው ማለት ነው። እኛ የሰው ልጆች ሰዎች እንደምንባል ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ኢየሱስም እግዚአብሔር ተብሎ ይጠራል፡፡ ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው ሲባል አብን በመልክ የሚመስለው በባህሪ የሚስተካከለው ማለታችን ነው ዮሐ 1፡1-3 ፤ ዮሐ 10 ፡30 ፤ዮሐ 14፡8-10 ‹‹እኔና አብ አንድ ነን እኔን ያየ አብን አይቷል››፡፡ ልጅነቱም የባህሪ ልጅነት ነው ማለትም ከማንም ያልተቀበለው ማንም የማይወስድበት ዘላለማዊ ልጅነት ነው፡፡

✧ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአብ ልጅ እንደሆነ ከአብ ጋር አንድ እንደሆነ እና አብ የሚያደርገውን ሁሉ እንደሚያደርግ ለአይሁድ ሲነግራቸው ድንጋይ አንስተው ሊወግሩት በማሰባቸው ጌታችን ስለምን ትወግሩኛላቻሁ ባላቸው ጊዜ ስለመልካም ስራህ አንወግርህም ስለስድብህ ነው ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለማድረግህ ነው ማለታቸው በወንጌል ተመዝግቧል እንግዲህ አይሁድ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ማለቱ አምላክ ነኝ ማለቱ እንደሆነ ገብቷቸዋል ማለት ነው ዮሐ 10፡25-38

✧ ከዚህ ጥቅስ እንደምንረዳው ጌታችን ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ ብሎ መጥራቱ አምላክ ነኝ ማለቱ እንደሆነ ነው/ ሙሉውን የአይሁድ እና የጌታን ንግግር አንብቡት/፡፡በሌላም ቦታ አይሁድ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ብሎ ራሱን መጥራቱን ተቃውመው ሊገሉት እንደነበር የእግዚአብሄር ልጅ ነኝ ማለቱ ደግሞ እግዚአብሔር ነኝ ማለቱ እንደሆነ ተረድተውት ሊገሉት እንደሚፈልጉ ተገልጧል ‹‹እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ደግሞ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ <<
እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር።››ዮሐ 5፡18

✧ ስናጠቃልለው ኢየሱስ እግዚአብሔር ልጅ ተብሎ መጠራቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተመለከትነው አምላክ/እግዚአብሔር መሆኑን የሚገልጥልን ልጅነቱም ከማንም ያልተቀበለው ባህሪ ልጅነት እንደሆነ እግዚአብሄርንም የሚስተካከልበት ልጅነት በመልክ ሚመስልበት ልጅነት እንደሆነ ልንረዳ ያስፈልጋል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ሰላም የተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ🙏

ከዛሬ ጀምሮ በአዲሱ ቻናላችን ስለ ሰ/ት/ቤቱ መረጃዎች እንዲሁም ስለተዋህዶ ሀይማኖት እየፃፍን እናቀርባለን።
ጎደኛዎትን ለመጋበዝ ከፈለጉ ከታች የለዉን ሰማያዊ ሊንክ ሼር በማድረግ አባልነቶን ያሳዩን።

@yeberhanljoche @yeberhanljoche
@yeberhanljoche @yeberhanljoche
"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🙏

🙏 እንኳን ለዐቢይ ጾም ለመጀመርያ ሳምንት ለዘወረደ (ለጾመ ሕርቃል) በሰላም አደረሰን።

+ + +
የዘወረደ መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ "ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ ባኡ ቅድሜሁ በተጋንዮ ወውስተ አዕፃዲሁ በስብሐት እመንዎ፤ እ፣ ንጹም ጾም ወናፍቅር ቢጸነ ወንትፋቀር በበይናቲነ፤ እ፣ አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ እስመ ሰንበትሰ በእንተ ሰብእ ተፈጥረት፤ እ፣ ምሕረተ ወፍትሐ አሐሊ ለከ እዜምር ወእሌቡ ፍኖተ ንጹሐ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ አባግዐ መርዔቱ። ትርጉም፦ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፣ ለእርሱም መገዛት ደስ ይበላችሁ። እግዚአብሔር ቸር ምሕረቱም ለዘላለም፣ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነውና። እኛስ ሕዝቡ የማሰማሪያው በጎች ነን፤ ወደ ደጁ በመገዛት፣ ወደ አደባባዮችም በምስጋና ግቡ፤ ጾምን እንጹም፤ ጓደኞቻችንን እናፍቅር፤ እርስ በርሳችንም እንፋቀር። ሰንበት ስለሰው ተሠርታለችና ሰንበትን እናክብር። እውነትንም እንሥራ፤ አቤቱ ምሕረትንና ፍርድን እቀኝልሃለሁ፤ እዘምራለሁ፤ ንጹሕ መንገድንም አስተውላለሁ። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው ላይ።

+ + +
ዘወረደ፦ የ0ቢይ ጾም የመጀመሪያው እሁድ (ሳምንት) ዘወረደ ይባላል።

ጌታችን እኛን ለማዳን ከሰማይ መውረዱን የሚነገርበት ሳምንት በመሆኑ ዘወረደ ተብሏል።

ከሰማይ ወረደ ማለት እርሱ የሌለበት ኖሮ ካለበት ወደዚህ መጣ ማለት አይደለም እርሱስ ጽርሐ አርያም ምጥቀቱ በርባኖስ ጥልቀቱ ፥ አድማስ ናጌብ ስፋቱ ተብሎ የማይነገርበት በዓለም ሙሉዕ ነውና ዓለማትን ቢወስን እንጂ ዓለማት እርሱን አይወስኑትም ።

የፀሐይ ብርሃን ከክበቡ ሳይለይ ከ0ይናችን ብሌን ጋር እንደሚዋሓድ ወልደም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ በምልዓቱ መወሰን ሳይኖርበት በሥጋ ማርያም መገለጹን ሰው መሆኑን ያስረዳል ::

ከሰማይ ወረደ ሲባል ስንሰማ "ሰማይ" ያለው ዕበዩን፣ ክብሩን ፣ ልዕልናውን ፣ ጌትነቱን፣ መንግሥቱን ፣ ርቀቱን .... ነው :: ስለዚህ ከሰማይ ወረደ ማለት የባሪያውን መልክ ይዞ ሰው መሆኑን ለመግለጽ ነው። ፊል 2፥6-8

ሰው ሆኖ መፈጠር ታላቅ ክብር ነው ለአምላክ ግን ሰው መሆኑ ተዋርዶ ነውና ይልቁንም እኛን ለማዳን በለበሰው ሥጋ መራብ መጠማቱ ፣ መገረፍ መታመሙ ... እንኳን ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ይቅርና ከመላእክት እንኳን ያነሰበት ነው መላእክት በባህሪያቸው መራብ መጠማት፣ መታመም የለባቸውምና " ከመላእክት እንኳን አሳነስከው" ያለውም ስለዚህ ነው ። መዝ 8፥5፣ ዕብ 2፥7

ይህ ማለት ግን ወልድ ሰው መሆኑ አምላክነቱን አጥቶ በዚህም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ አነሰ ማለት አይደለም ጌታችንም "አብ ይበልጠኛል" ያለው በለበሰው ሥጋ ባገኘው መራብ መጠማት አነሰ ለማለት ነው አብ እና መንፈስ ቅዱስ ሰው ሆነው መራብ መጠማት ... ያላገኛቸው መሆኑን ለመግለጽ ነው። ዮሐ.14፥28

ቅዱስ ያሬድ ጾመ ድጓውን ሲጀምር ሃሌ ሃሌ ሉያ "ዘወረደ እም ላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ ወሚመ ኢያእመሩ እግዚአ ኩሉ ዘየሃዩ በቃሉ"። ትርጉም፦ ከሰማየ ሰማያት የወረደ አይሁድ የሰቀሉት ሁሉን በቃሉ እንደሚያድን አይሁድ ያላወቁት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በማለት ሰው ሆኖ በአይሁድ ተዋርዶ ያገኘው መሆኑን የዚህን ሳምንት ጠቅላላ ሀሣብ ይገልጻል። ምንጭ፦ ከአምኃ ሥላሴ (መኩሪያ ተስፋዬ) ፔጅ የተወሰደ።

+ + +
የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሌላ ስሙ ጾመ ሕርቃል፦ ሕርቃል ማን ነው? ለምንስ በስሙ ተሰየመ? በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡

ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲየኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፡፡

እርሱም "ሐዋርያት ሰውን የገደለ ዕድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው?" አላቸው እኛ "የአንተን ዕድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን" ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉን ያለበትን አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቊስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡

የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ ይህን ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪም በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን እንጾመዋለን፡፡

በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ ሱባኤ ይዞለታል፡፡

ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያን ያደረግነውን በማሰብ እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡

የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡ ምንጭ፦ የመጋቢት 10 ስንክሳር እና ከፌስቡክ ከማኅበረ ጎዶልያስ ዘ ዑራኤል የተወሰደ።


+ + +
የዘወረደ አራራይ ዜማ፦ ሃሌሉያ "መሐረነ ንጉሠ ስብሐት ተሣሀለነ እግዚአ ለሰንበት አቡሃ ለምሕረት ወሀበነ ጾመ ለንስሐ በዘይሰረይ ኃጢአት። ትርጉም፦ የምስጋና አምላክ ማረን የምሕረት አባት የሰንበት ጌታ ይቅር በለን ጾምን ለንስሐ ስጠን ኃጢአታችን ይሰረይ ዘንድ፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው ላይ።

+ + +
የዕለቱ ምስባክ፦ "ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት። ወተኀሠዩ ሎቱ በረዓድ። አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዐዕ እግዚአብሔር"። መዝ 2፥11-12። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 13፥7-16፣ ያዕ 4፥6-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 25፥13-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 3፥10-25። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅበላ በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
@yeberhanljoche
@yeberhanljoche
@yeberhanljoche
​​ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ

- በፊት ስማቸው አባ ዘሊባኖስ ፈንታ የሚባሉት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ፣ በጎንደር ክፍለ ሀገር በደብረ ታቦር አውራጃ በአለታ ወረዳ አረጊት ኪዳነ ምሕረት በተባለችው ገዳም ሰበካ፣ ልዩ ስሙ ማር ምድር በ1930 ዓ.ም.፣ ከብላታ ፈንታ ተሰማና ከወ/ሮ ለምለም ገሰሰ ተወለዱ፡፡

- ማዕርገ ምንኵስናን በጣና ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስ በመግባትከመምህር ኃይለ ማርያም(በኋላ የባሕር ዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ መልአከ ገነት) በ1961 ዓ.ም. የተቀበሉ ሲሆን፣ በዚሁ ዓመት ማዕርገ ቅስናን፣ ከጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ተቀብለዋል፡፡

- ባላቸው በቂ የቤተ ክርስቲያን ዕውቀትና ባሳዩትም የመንፈሳዊ አገልግሎትና የሥራ ወዳድነት፣ ቤተ ክርስቲያኗ ጥር 13 ቀን 1971 ዓ.ም. ባደረገችው የ13 ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ፣ በካህናትና በምእመናን በከፍተኛ ድምፅ ተመርጠው የኦጋዴን አውራጃ ኤጲስ ቆጶስ ኾነው ተሾመዋል፡፡

- ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስ፣ በ1971 ዓ.ም. ወደ ጎንደር ሀገረ ስብከት ተዛውረዋል፡፡

- ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ 4ኛ ፓትርያርክ ኾነው የተሾሙት፣ ነሐሴ 29 ቀን 1980 ዓ.ም. ሲኾን፣ በፖሊቲካዊ ግፊትና ጫና መንበራቸውን ለቀው ከሀገር ከመውጣታቸው በፊት እስከ ነሐሴ 28 ቀን 1983 ዓ.ም. ድረስ ለቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ አመራር ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡

- ከ26 ዓመታት ስደት በኋላ፣ ሐምሌ 25 ቀን 2010 ዓ.ም.፣ በስሙ በተሠየሙበት በሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ክብረ በዓል ወደ ቅድስት ሀገራቸው ኢትዮጵያ መመለሳቸውን፣ ይታወቃል፡፡

- አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከቀናት በፊት ህመም አጋጥሟቸው በሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን ዛሬ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ተነግሯል።
ቅዱስ ሲኖዶስ በጠራው አስቸኳይ ጉባኤ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ስርአተ ቀብር እሁድ የካቲት 27/06/2014 በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንዲፈፀም ወስኗል።
ብፁህ አባታችን አቡነ መርቆርዮስ ባረፉ በሁለተኛው ቀን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አረጋዊ አቡነ ኤፍሬም ከዚህ አለም ድካም አርፈዋል በረከታቸው ይደርብን
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የካቲት ሃያ ሰባት በዚችም ዕለት የመድኃኒታችን የስቅለቱ መታሰቢያ ነው::

የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የስቅለቱን መታሰቢያ ስናስብ እርሱ ካለምንም ነገር ምንም ሳይኖረን እኛን መውደዱን ነው የምናስበው::

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ድኅነትን ለመስጠት ምን ምክንያት ነበረው? ብለን ብንጠይቅ መልሳችን ከፍቅር ሌላ ምንም የለም የሚል ይሆናል::

በምድራዊ ፍቅርና በእግዚአብሔር ፍቅር መካከል ለንፅፅር የሚከብድ ትልቅ ልዩነት አለ::

ሰዎች ሲወዱ መነሻ ይፈልጋሉ:: ያለመነሻ ማንም ማንንም ወዶ አያውቅም:: ሰው ሰውን የሚወድባቸው መነሻዎች አሉ:: ሀብት÷ ውበት÷ ጉልበት÷ ዝና::

የእግዚአብሔር ፍቅር ግን ከዚህ ሁሉ የጸዳ ያለ ማንጠልጠያ ያለ መነሻ የሆነ ፍቅር ነው::
"እንዲሁ ኑና የሕይወትን ውኃ ጠጡ" ኢሳ 56
"እግዚአብሔር ዓለሙን እንዲሁ ወደደው" ዮሐ.3÷16
"መንፈሱና ሙሽራይቱም ና ይላሉ:: የሚሰማም ና ይበል:: የተጠማም ይምጣ; የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይወሰድ የሕይወትን ውኃ እንዲሁ ጠጡ::" ራእ.22÷17

እንዲሁ ያለመነሻ መውደድ የእግዚአብሔር ብቻ ነው:: እግዚአብሔር ሰውን በመውደዱ የሚጨመርለት ነገር የለም::

ንጉሥነት እንዳይጨመርለት ዓለም ሳይፈጠር ንጉሥ ነበር:: እኛ ያለ እግዚአብሔር መኖሮ አንችልም:: እርሱ ግን ነበረ አለ ይኖራል::

እኛ ስንወድ ስንቀርብ በምክንያት ነው:: እርሱ ግን እየራቅነው ያቀረበን÷ እየጠላነው የወደደን÷ እየወረድን ከፍ ያደረገን አባት ነው:: ምንም የማይጠቅምን ሰውን መውደድ አስደናቂ ፍቅር ነው::

እስኪ እንደዚ እስከ ሞት ድረስ የወደደንን አምላክ እንውደደው:: ስንወደው ሕጉን እንጠብቃለን ስንጠብቅ ሕጉን እኛ ነን የምንጠቀመው::

በይቅርታውና ቸርነቱ የወደደን ምሕረትና ቸርነቱን ያበዛልን መድኃኒያለም ክብር ይገባዋል በእውነት ለዘላለሙ አሜን::
@yeberhanljoche
@yeberhanljoche
@yeberhanljoche
አቢይ ፆም ግን መቼ ነው የሚገባ ?

መቼም ይህ ነገር ስል ምን እያወራ ነው ትሉኝ ይሆናል ወይም ምን ነካው ? አሁን ኮ ዘወረደ ፤ቅድስት ብለን ፤ሙክራብ ልንል ተቃርበናል የት ሄዶ ነው እስከ ዛሬ? ወይስ ምን አስቦ ነው ? ትሉኝ ይሆናል ።

እኔ የማውቃት አቢይ ፆም የበገና መዝሙር የሚሰማባት ፤ እጅግ በርካታ ምዕመናን የፆሙ ጅማሬ ላይ ቤተክርስቲያን የሚጥለቀለቁባት ፤ እዚህም እዛም ነጠላ ለባሽ የሚታይባት ደስ የምትል የአቢይ ፆም ነበር የማውቃት።

ድሮ ኮ በአቢይ ፆም ከቤታችን ቴሌቪዥን እንኳን አይከፈትም ነበር የሚተኛውም አልጋ ላይ ሳይሆን መሬት አንጥፈን ነበር ከት ብሎ መሳቅ ጮክ ብሎ ማውራት ሁሉ አይቻልም ነበር ሀዘን ላይ ነበርን።

ያውምኮ እንደ ዛሬ ችግር አልነበረም ሰው አይታረድ ንብረት ሳይወድም ፤ሴቶች አይደፈሩ፤ ጦርነት አልነበረ ፤ኮሮና አይታወቅ ሰው ሲሞት ለምን ሞተ እንጂ ስንት ሰው ሞተ ብለን በማንናገርበት ዘመን አቢይ ፆም ጥብቅ ነበር።

ችግር ብርቃችን ፤ሞት ብርቃችን ፤ በሽታ ብርቃችን በሆነበት ባለፈው ዘመናችን አቢይ ፆም ሁሉም ይፆመው ነበር አሁን ግን ግራ የሚያጋባ ሆኗል በየመንገዱ ፤በስልካችን እዚህም እዛም የበገና መዝሙሮች ሳይሆን የሚሰሙት ሌላ ነገር ሆነዋል ።

እንኳን በመንገድ እንኳን ከቤታችን ይቅርና በቤተክርስቲያን አጥር ስር የሚወራው ወሬ እንኳን አቢይ ፆምን የሚዘክር ሳይሆን የኑሮ ውድነት ፓለቲካ ፤ቧልትና አሉባልታ ብቻ ሆኗል፤ ሰው ነጠላ ለብሶ ሊፀልይ ሳይሆን ሊያወራ የሚሄድ ነው የሚመስለው ወሬው እንደ ጉድ ሲወራ ይሁላል።

በቤተ መቅደስ ውስጥ ዞር ዞር ብላችሁ ስታዩ አበክሮ የሚፀልይ አብዝቶ የሚሰግድ እንብዛም አታዩም ሰው ሁሉ አካሉ እንጂ አሳቡ ብዙ ጉዳዮች ላይ ተጠምዷል በደመ ነፍስ የቆመ ፍጥረት መስሏል።

ዲያብሎስ ቤተክርስቲያን ላይ የከፈተው ጦርነት እጅግ በጣም አደገኛ ሲሆን አሳቡም የተሟላለት ይመስለኛል አስቀድሞ ከካህን አጣልቶ ፤ከንስሀ አባት አለያይቶ ፤በጳጳሳት ውግዘት ጠፍሮ አሰረን ከዛ ከቅዳሴ ፤ከኪዳኑ ፤ከቤተክርስቲያን ህብረት አወጥቶ ከቤታችን ወሸቀን ፤በውዳሴ ከንቱ ልባችንን ሞልቶ በግል ፀሎት እንድንጠመድ አደረገን።

ፆምን ና ራስን ማስራብን ለይተን እንዳናውቅ አድርጎ ጥሬ እያስቆረጠመ በርሃብ አለጋ እየገረፈ ፤በምድራዊ አሳብ በምድራዊም ንጉስ ወስኖ ከዳኑት ወገን እንደተደመርን አድርጎ ጠልፎ በጥበብ ጣለን ማንም ሊነቃበት አልቻለም ጭራሽ ለጥበባዊ ተንኮሉ ጠበቃ ተሳዳቢ አድርጎ በአራት ሚስማር ከርችሞ አስቀረን።

አሁን የአቢይ ፆም ድባቡ ጠፍቷል ኪዳን የሚሄደው የሚያስቀድሰው የሰው ቁጥሩ እጅግ በጣም ቀንሷል የኑሮ ውድነት በሽታው ፤ጦርነቱ ስጋት ሆኖበት ማንም የሚነዳው ስነ ልቦናው የተጎዳ ፤በፍርሃት ውስጥ የሚኖር ፤ደንባሪ ጊዜው ስላደረገው ተረጋግቶ አምልኮቱን ለመፈፀም ሕዝቡ ተቸግሯል።

መንግስታዊ መዋቅር ፤የአገሪቱ ፓለቲካ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ከድጡ ወደ ማጡ ሆኖባታል መከራዋ እየባሰ መጣ እንጂ ከለውጡ የተለወጠ ነገር አላገኘችም ምዕመናኑን እንኳን በአግባቡ ሰብስባ ለማስተማር ጊዜ ያጣች ተዋካቢ አድርገዋታል።

ሕዝቡ አቢይ ፆምን እንዴት እየፆመ እንደሆነ አልገባኝም መቼም ቀኑን ሳይበሉ መዋል ብቻ ርሃብ እንጂ ፆም አይባልም ፀሎት ያስፈልገዋል ወይ ከኪዳኑ አልያም ከቅዳሴው ካልሆነም በሰርኩ ፀሎት መካፈልም ይገባል።

እና ተወዳጆች የፆም ማዕዛ አልሸት ቢለኝ አቢይ ፆም መቼ ነው የሚገባው አስብሎኛል በእውነት መቼ ነው ግን የሚገባው ?
@yeberhanljoche
@yeberhanljoche
@yeberhanljoche
ማሰብና ማድረግ እኩል ናቸው?

በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዘመን የኖሩ እጅግ ለእምነታቸው የሚቀኑ ጽኑዕ ክርስቲያኖች ነበሩ። ታዲያ በአንድ ወቅት ኃጢአትን በማሰብ እና በማድረግ መካከል ስላለው ልዩነት አንሥተው ይከራከሩ ጀመር። ብዙዎቹም "ማሰብና ማድረግ ምንም ልዩነት የላቸውም" የሚል የሚል አቋም ነበራቸው። በስተመጨረሻም ይህን ጥያቄ እንዲመልስላቸው ወደ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይዘው ቀረቡ። ቅዱሱ በምሳሌ ሊያስተምራቸው ስለ ፈለገ አንድ ቀን ሙሉ ምንም ምግብ ሳይቀምሱ ቆይተው ማታ ለእራት እርሱ ዘንድ እንዲመጡ ጠራቸው። በቤቱም ለዓይን ያማረ ለመብላት ደስ የሚያሰኝ ፈታኝ ማዕድ እንዲያዘጋጁ ለአርድእቱ ተናገረ። እነርሱም እንዳላቸው አዘጋጁ።

እንግዶቹም በመጡ ጊዜ በየቦታቸው ተቀመጡ። የተዘጋጀውም መዓድ ከፊት ቀረበ። የምግቡ መዓዛ የምግብ ፍላጎት የሚከፍት ብቻ ሳይሆን የሰዎቹን ረሃብ የሚያባብስም ጭምር ነበር። ከዚያም ቅዱስ ዮሐንስ በቤቱ የሚያገለግለውን ዲያቆን ከመዝሙራት እያወጣ እንዲያነብ አዘዘው። ዲያቆኑም ረዘም ላሉ ሰዓታት ማንበቡን ቀጠለ። እንግዶቹ ግን ከመጎምዠት ብዛት በአፎቻቸው ምራቅ ሞላ። ጸሎቱ አልቆ እስኪመገቡ መቆየት ጣር ሆነባቸው።

አሁን ጸሎቱ ተጠናቋል። ይሁን እንጂ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ግን እንግዶቹን ለመዓዱ እንዲቀመጡ በመጋበዝ ፈንታ "በቃ ወደየቤታችሁ በሰላም ግቡ" ብሎ አሰናበታቸው። ወደ ቤቱ ተጠርተው የመጡት እንግዶችም ደነገጡ። ይህን ያየው ቅዱሱ "ምነው ግራ የገባችሁ ትመስላላችሁ? ምግቡን በደንብ አላያችሁትም? ልትበሉስ እጅግ ተመኝታችሁ አልነበረም?" ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም "አዎን" አሉት። አፈወርቅም "ጥሩ፤ እንግዲያውስ እንደ በላችሁ ይቆጠራላ" ቢላቸው ሁሉም ፈገግ አሉ። በዚህ ጨዋታ መካከል የእነዚያ ክርስቲያኖች ጥያቄ በሚገባ ተመለሰላቸው።

ክፉን ነገር በማሰብና በማድረግ መካከል ያለው ልዩነት ምን እንደ ሆነ በዚህ ታሪክ ውስጥ ግልጽ ሆኖ ይታያል። ክርስትና ሐሳብ እና ሥራን መቀደስ ነው። ነገር ግን የሐሳብ ንጽሕና ባይኖርህ "ማሰብ ከማድረግ ጋር እኩል አይደል!" ብለህ በኅሊናህ የቋጠርከውን ክፋት ለማድረግ ራስህን አታደፋፍር። ያሰብከውን እስካልፈጸምህ ድረስ አሁንም ከኃጢአት ወጥመድ የማምለጥ እድሉ በእጅህ ነው።

"ኃጢአት በደጅ ታደባለች፤ ፈቃድዋም ወደ አንተ ነው፥ አንተ ግን በእርስዋ ንገሥባት" ዘፍ 4፥7
@yeberhanljoche
ቅዱሳን መጽሐፍት ምን ይላሉ?:
🌾‹‹ኑ እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር›› (ኢሳ. ፩፥፲፰)🌾

መምህር ጳውሎስ መልክዐሥለሴ

በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ተጎሳቁለው ለእግዚአብሔር ባልተመቻቸ ስፍራ በመቆማቸው ምክንያት የደረሰባቸውን በደል መቋቋም ላቃታቸው እስራኤላውያን ከኃጢአት የሚያነጻው፥ የሚያጠራው እና ከሰይጣን ባርነት ነጻ የሚያወጣው እግዚአብሔር እንደሆነ ነቢዩ ኢሳያስ ነገራቸው፡፡ ለደረሰባቸው የጸጋ መገፈፍ እና የሕይወት መጎስቆል ሁሉ መፍትሔያቸው እግዚአብሔር መሆኑንም አሳወቃቸው፡፡  (ኢሳ. ፩፥፲፰)

ብዙ ጊዜ በሕይወት በሚገጥመን ፈተናና ችግር ምክንያት ራሳችንን በመመርመር እግዚአብሔርን መማጸንን የመሰለ መፍትሔ ወይም የድኅነት መንገድ የለም፡፡ እስራኤል ከእግዚአብሔር ርቀው፤ ወደ ቃሉ መጠጋት በአቃታቸው ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ  የመጣባቸው መቅሠፍት የኃጢአታቸው ውጤት ስለነበረ እግዚአብሔር አጥቦ ቅዱሳን ልጆቹ ሊያደርጋቸው የተዘጋጀ አባት በመሆኑ ‹‹ኑ እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር›› አላቸው፡፡ (ኢሳ. ፩፥፲፰)

የሰው ልጅ በሕይወት ጎዳና ውስጥ ከፍተኛ የኃጢአት አዘቅት እና ተስፋ መቁረጥ ውስጥ የሚወድቀው  እግዚአብሔር ቸር መሆኑን ሳይረዳ ሲቀር ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቸርነት የተረዳ ሰው ኃጢአት ቢሠራ እንኳን እርሱ መሓሪ መሆኑን አውቆ ለንስሓ ወደ ፈጣሪው ይጠጋል፡፡ እስራኤል ግን ይህን ስላልተረዱ ሸሹ፤ እነርሱንም ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ አላቸው፤ ‹‹ኑ እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደአለላ ብትሆን እንደአመዳይ ትጸዳለች፤ እንደደምም ብትቀላ እንደባዘቶ ትጠራለች፤›› በደጅ ለሚንከራተቱት እና ጎዳና በመከራ ለሚንከላወሱት አባት ሊሆናቸው እነርሱም ልጆች ይሆኑት ዘንድ እግዚአብሔር እንደጠራቸው አሳወቃቸው፤ እግዚአብሔር ያነጻው እና ያጠበው ብቻ ይነጻልና፡፡ (ኢሳ. ፩፥፲፰)

የሰው ልጅ ለመንፈሳዊ ንጽሕና በእግዚአብሔር ሊታጠብ ያስፈልጋል፤  እግዚአብሔር ካላጠበው ሰው ሕይወት የለውም፡፡ በዮሐንስ ወንጌል እንደተጻፈው ጌታ በሐዲስ ኪዳን የደቀ መዛሙርቱን እግር ሲያጥብ ቅዱስ ጴጥሮስ ግን ስለ ትሕትናው ‹‹ጌታ ሆይ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን?›› አለው፤ ጌታ ግን መልሶ ካላጠብህሁ፥ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም›› ብሎ መለሰለት፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ‹‹ጌታ ሆይ፥ እጄንና ራሴን ደግሞ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም፤›› አለው፡፡ (ዮሐ. ፲፫፥፮-፱)

ቅዱስ ዳዊት በኃጢአት ጎስቁሎና አድፎ ‹‹በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነጻማለሁ፤ እጠበኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ›› ብሎ እንደጸለየው በኃጢአት ያደፍን ወገኖች ሁሉ እግዚአብሔር እንዲያጠራን ራሳችንን ያለመፍራት ወደ እርሱ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ እስራኤል ከእነ እድፋቸው ሲመላለሱ ኃጢአት አለብኝ ብለው መሸሽ ትክክል እንዳልሆነ፤ እግዚአብሔርም ከኃጢአት እንዲያነጻቸው ይቀርቡት ዘንድ አስተማራቸው፡፡ ሰዎች በኃጢአታቸው ተጸጽተው ከተመለሱ ወደ አምላካቸው መቅረብ እንጂ መሸሽ የለባቸው፡፡ እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላችሁ ብሏቸዋል፡፡ (መዝ. ፶፥፯፤ኢሳ. ፩፥፲፱)

የሰው ልጅ የመንፈሳዊ ሕይወት ስኬት ለእግዚአብሔር፣ ለሕጉም ከመታዘዝ  ይጀምራል፡፡ እሺ ማለት፣ መታዘዝ እና ራስን ለእግዚአብሔር አሳልፎ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር በግዴታ ሳይሆን በፈቃደኝነት የሚገዛን ቸር አምላክ ነው፤ የፍቅር አባት በመሆኑ እርሱ ሲገዛን ጥሩ ልጆች እንሆናለን፤ እግዚብአሔር ሲመራን በእውነት መንገድ እንጓዛለን፡፡ እራሳችንን ለእርሱም የምናስገዛው እግዚአብሔርን ስናውቀው ነው፤ ክርስቲያኖች ፈጣሪያችንን ማወቅ አለብን፡፡ ክርስትናም ማመን፣ መታዘዝ፣ መገዛትና መጽደቅ፣ ለሰማያዊ ርስት፣ ለማያልፍ፣ ለማያልቅ፣ ለማያረጅ እና ለልጅነት በረከት መዘጋጀት ነው፡፡ ልባችን ለእግዚአብሔር የምናስገዛው ሁለንተናችን በፍቅር ሲነካ ነው፡፡ እግዚአብሔር ከሕይወት ጽልመት፣ ከኑሮ ጭጋግ እና ከሰብእና ውድቀት ሊጠብቀን ሲሻ ‹‹ልጄ ሆይ÷ ልብህን ስጠኝ÷ ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ፤›› አለን፡፡ ልብ የሰውነታችን መሪ፤ ከአካል ክፍላችን ሁሉ በላይ ነውና፡፡ ሰው ዓይኑ ቢጠፋ በሕይወቱ ይኖራል፤ የልባችን መሥራት ካቆመ ግን ይሞታል፡፡  (ምሳ. ፳፫፥፳፮)

‹‹ልባችሁን ስጡኝ›› እንጂ ዓይናችሁን፣ እጃችሁን፣ እግራችሁን ወይንም ሌላ አካላችሁን ስጡኝ›› አላለም፡፡ ዋናውን አካላችንን እንድንሰጠው እና እርሱ ኃይል እንደሚሆነን ነገረን፤ እስራኤላውያን በተመሰቃቀለ መንገድ ላይ በመሆናቸው ሳቢያ በመቅሠፍት መመታታቸው ልባቸውን ስላልሰጡት እንደሆነ ነገራቸው፡፡ በችግር መደቆሳቸው፣ ጦርነት እና በሽታም ያጠቃቸው ልባቸውን ለእርሱ ባለመስጠታቸው መሆኑን አስረዳቸው፡፡

ዛሬም ሀገር በሰላም የምትተዳደረው ሰዎች ልባቸውን ለእግዚአብሔር ሲሰጡ ነው፡፡ ከትንሽ እስከ ትልቅ፤ ከልሒቅ እስከ ደቂቅ ያለው ሰው ሁለንተናውን ሊሰጥ ይገባል፤ የሰው ልጅ ሕይወቱን ለፈጣሪው ሲሰጥ ድኅነትን ያገኛል፤ ይባረካልም፡፡ ካላንበት የኑሮ አዘቅት ውስጥ ስቦ የሚያወጣን እግዚአብሔር ልባችንን ስንሰጠው እንደሆነ ነግሮናል፡፡ ፈጣሪያችን ሲመራን አንሰናከልም፤ አንሰበርም፤ አንታመምም፡፡  በእርሱ ዘንድ የማይጨልምበት ጌታ በድቅድቅ ጨለማ ወስጥ ብርሃን ይሆነናል፤ እግዚአብሔርን የምትወድ ነፍስ በብርሃን ትጓዛለች፡፡ ‹‹እግዚአብሔርም ሁል ጊዜ ከአንተ ጋር ይኖራል፤ እንደ ነፍስህም ፍላጎት ያጠግብሃል፤ አጥንትህንም ያለመልማል፡፡ አንተም እንደሚጠጣ ገነት÷ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ›› እንዲል፡፡ (ኢሳ. ፶፰፥፲፩)

እግዚአብሔር የሚመራን ከሆነ ሀገር በበረከት ሕዝብ በታዛዥነት ይጓዛል፤ ከመሪ ጀምሮ እስከ ተመሪ ለፈጣሪ መገዛት ያስፈልጋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን በቤታችን ሀብት ብናገኝም ጤና እናጣለን፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የለምና፤ በሰላም ውለን የምናድረው እርሱ ሲፈቅድ ነው፡፡ ካልሆነ ግን ሀብቱ ቅዠት፤ ዕውቀቱ እብደት፤ ንግዳችን ኪሳራ ይሆናል፡፡

እግዚአብሔር የለም ብለው የሚያምኑ ሰዎችንም እንደ ምሁር መቁጠር ጀምረናል፤ ‹‹እርሱ እኮ ወጣ ያለነው እንላለን፤›› በእርግጥ የወጣ ነው፤ ከሕይወት ጎዳና የወጣ፣ ወደ ሞት ቁልቁለት የወረደ ማለት ነው፡፡ የክሕደት መርዛቸውን እየረጩ ብዙ ተማሪዎችን ሳይጨርሱ እንዲወድቁ ያደረጉ መምህራን አሉ፡፡ ዕውቀትና እድገት ይገኝበታል የተባሉ ትምህርት ቤቶች ዛሬ የዝሙት፣ የሴሰኝነት እና የርኩሰት መናኀሪያዎች ሆነዋል፡፡ ክፋት የሌለባቸውን ሕፃናት ከአቅማቸው በላይ ለሆነ ሐሳብ እየዳረግናቸው እንገኛለን፡፡

ከሕፃንነት ጀምሮ የመራንን አባት በእምነት እንከተለው፤ ጌታ ሆይ ከአማልክት መካከል እንዳንተ ያለ ማነው፤ አንተ ፈጠርከን፤ ስለወደድከን አሳደከን፤ ልጅህ አድርገህ አከበርከን፤ በመንፈስ ቅዱስ የምትመራን አንተ ነህ፤ ኑሮአችን፣ ሥራአችን፣ ትዳራችን በአንተ ይሁን፤ እንቅስቃሴያችን፣ ንግግራችን፣ ልባችንና ሁለንተናዊ ማንነታችን ለአንተ ይሁን፤ አንተን የሚመስል የለም እንበለው፡፡

በማጣት፣ በማግኘት፣ በመራብም፣ በመጥገብም፣ በማትረፍም፣ በመክሰርም፣ በመሾምም፣ በመሻርም፣ ክርስቲያን ተመስገን ማለት አለበት፡፡ምድራዊ ሕይወታችን የምንማርበት እንጂ የምናማርርበት ሊሆን አይገባም፤ ‹‹እግዚአብሔር ሊያስተምረኝ ፈልጎ ነው›› ብለን ተመስገን ማለት አለብን፡፡