ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.5K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
#ዝም #ዝም

ሆድ ከሀገር ይሰፋል~ በሚሉባት ሀገር
አፍ ከአለም መስፋቱን ~ለማን እንናገር ?
ለማን እንናገር ~ እኮ ለማ እንማው
አፍ ባጋለው ሐገር~ምጣድ ነው
ሚሰማው
#ሰማ #ሰማ #ብለን
በቶሎ ተጋግረን ~ በጊዜ እንዳንወጣ
በሰማ ምጣድ ላይ ~ የሚያሰፋ መጣ
የሚያሰፋው መጣ ~ሊጡን አንጠልጥሎ
ማልዶ ሊማግድህ ~ ነፃ ላውጣህ ብሎ
ተናገር ይልሀል ~ አስከብር መብትህን
እንዳሻህ ተጠቀም ~ ሰብአዊነትህን
#እኔ ግን #እላለሁ
በንግግር ብቃት ~ እልፎች ቢጀግኑም
አንድ ሺህ ምላሶች ~አንድ ጆሮ አይሆኑም
በምላስ ተስቦ ~ ከሰነባበተ
ጆሮን ይከልላል ~ አፍ ከተከፈተ
#እኔ #ጠይቃለሁ
የወል ጥያቄህ ላይ
ያለ ሀሳብ ተኝተው ~ ሠው ለሚያንተርሱ
መናገር አይደል ወይ ~ ዝም ማለት ራሱ
#እኔ #ሞግታለሁ
ሐሳብን በመግለፅ ~ በመናገር አለም
ዝም የማለት መብቱን~የሚያስከብር የለም
#እኔ #እጠቁማለሁ
በነፃነት ጥላ ~ ግብሩ የተከለለ
በመናገር መብት ውስጥ~ዝም የማለት አለ
===||===
ከሙሉቀን ሰ•