ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.49K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
••●◉ ሀገሬ ምግብ ናት◉●••
•════••• •••════•
ኢትዮጵያ በመባል ስሟን የምናውቃት
ሀገሬ በርገር🍔 ናት ሁሉም የሚገምጣት
ኢትዮጵያ እያልን ስሟን የምንጠራት
ሁሌ በሙዚቃ የምናወድሳት
ገጣሚው በግጥም ሰአሊው በስእል የሚያሸበረቃት
እላይላዩን እንጂ ፈፅሞ የማናውቃት
ሀገሬ ውስኪ ናት ሀብታም የሚጠጣት
ደሃ ከዳር ሆኖ የሚመለከታት

ሀገሬ ዶሮ ናት🐓
ሀብታም በየቀኑ ደሃው የበዓል ቀን አርደው የሚበሏት
በቃ ምን አለፋህ ሀገሬ ምግብ🍝 ናት
የተራበ ሁሉ ቆርሶ የሚበላት
የተጠማ ሁሉ አንስቶ የሚጠጣት
••●◉
ብሎ የሚል ግጥም ለመፃፍ አስቤ
ስጋት ገባው ልቤ...
ሀሳቤን ቀይሬ ብእሬን አነሳው
ከዛ በመቀጠል ይሔንን አወሳው።
••●◉
ሀገሬ ሚስት ናት
ሁሉም ሰው በፍቅር በስስት የሚያያት
ሀገሬ እናት ናት
ሁሉም በሰቀቀን በፍቅር የሚወዳት
ሀገሬ እህት ናት
ሁሉም የሚያከብራት
:
ሀገር ማለት ሰው ነው ሊያውም ወዳጅ ዘመድ
በስስት የሚታይ ሁሌም የሚወደድ
እያልን በግጥም ከምናወድሳት
እጅ ተያይዘን ባንድነት እናልማት።
•════••• •••════•
🎼••●◉ ገጣሚ፡ ተካበ ግርማ 👍
#ሠናይ_ውሎ

@Simetin_Begitim
በምድጃዬ
.........
በዓይኔ ምድጃ ውስጥ-
ፍም እሳት ይዣለሁ
ፍቅር ይሞቀኛል
በዓይኔ ምድጃ ውስጥ-
በረዶ ይዤ አድራለሁ
ሀዘን ይበርደኛል
ዓይኔ ላይ ድስት አለ -
ነገር ላብስል ብዬ
እሳት አነድዳለሁ
ሆድ የባሰኝ እንደሁ-
በፈላው ዕንባዬ
ተስፋን ጥጄ አድራለሁ፡፡

© ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ


#ሠናይ_ምሽት
#ወይኩን_ፍቃድከ

በወዝጋባ ዕለት ውዝግብግብዋ ዕኔ
ግራ በሆነ ሀሳብ መልኩ በወየበ
እንባ ያነፈረው ዕርጥብ ጉንጬን ይዜ
ከእግዜር ደጃፍ ቆምኩኝ እለምነው ብዬ።

ልቤ ከህሊናዬ መንታ ሀሳብ ይዞ
ቅጭም ፈካ ይላል መልኬ ተበርዞ።

ጸሎቴ ውል አጣ
ምኞት አናወዘኝ
ሁለት ሀሳብ ናጠኝ።

እጄን አመሳቀልኩ
መላ አካሌን ባረኩ
ወደኩ ;ተንበረከኩ
መጽናናትን ናፈኩ።

ያሳብ ማዕበል አይምታኝ
ያሠብኩትን ሳይሆን
ያንተን ፍቃድ ስጠኝ።

ህሌና
#ሠናይ ውሎ
‹‹ነገ ሌላ ቀን ነው››
--------------------
ከዕለታት በዚች ቀን፣
በልዩ አጋጣሚ፤
እንድትሆኝ ጋበዝሁሽ፣
የቤቴ ታዳሚ።

አንቺ ግን ሰበባም፣
ምክንያት ደርድረሽ፣
ግብዣዬን አቃለሽ፣
እምቢ ብለሽ ቀረሽ።

በይ ከእንግዲህ ወዲያ፣
አንቺ ከኔ ጋራ፤
ፈፅሞ እንዳያምርሽ፣
ጊዜ እንድንጋራ።

እርሱ በፈቃዱ፣
ቢመርጥም ባይመርጥም፤
ዛሬዬን ለናቀ፣
ነገዬን አልሰጥም።

አየሽ በኔ ዓለም፣
ዛሬ ልዩ ቀን ነች፤
ነገ የማትመጣ፣
ትናንት ያልነበረች።

ጊዜን ትርጉም ሰጥቶ፣
ተግባር ለሚከውን፤
ቀን ማለት ዛሬ ነው፣
ጊዜ ማለት አሁን።

‹‹ነገ ሌላ ቀን ነው››
ትርጉሙ ይሄው ነው።
--------------------------
መላኩ አላምረው
📙 ነፍጠኛ ስንኞች

#ሠናይ ምሽት
#ውብ ለሊት
#ጥንቃቄ ማድረግ አይዘንጉ ለእርስዎ ለቤተሰብዎ ደህነንት ሲሉ
“ብትችል ብረር፤ መብረር ካልቻልክ ሩጥ፣ መሮጥ
ካልቻልክ ተራመድ፣ መራመድ ካልቻልክ ተንፏቀቅ ግን ምንም
ቢሆን መሄድህን አታቁም”
ማርቲን ሉተር ኪንግ

#ሠናይ ቀን ከሙሉ ጤና ጋር
ድሮ ተማሪዎች ሆነን፡ ከሚያዝናኑኝ ነገሮች አንዱ ቅጣታችን
ነበር።
" አየለ! "
" አቤት ቲቸር "
" ና ውጣ! "
" ምን አጠፋው? ቲቸርዬ "
" እሁድ በሰፈራችሁ ሳልፍ በሴት ድምጽ ' ጊሽጣው ' ብለኸኛል
"
" ኧረ....እኔ "......
ቲቸር ማሩ ባገኙት ነገር ነው የሚማቱት። ጊዜ አይሰጡም!
ቷቷ ጧጧ ግው ጭው ድው...ካደረጉ በኋላ አራግፈን ስንነሳ ለኛ
ብለው እየመከሩን እንደሆነ ይነግሩናል።
አየለ ዘለግ ስለሚል በዱላ ነው የሚስተናገደው
ዧዧ...ጀርባውን
እውነቱን ለመናገር አየለ እንዳይገረፍ ጸሎታችን ነው
በተዠለጠ ቁጥር፡ ከጃኬቱ የሚነሳው አቧራ ተዉት!
" አንት ጅምር አህያ! " እያንከባለሉ...አባሱት ጭራሽ!
°°°°°°°°°°
አንድ ቀን የቲቸር ምስራቅ ወንበር ላይ የሞተ እንቁራሪት
ያስቀመጠውን መጠቆም ስላልቻልን በመደዳ እንድንገረፍ
መምህርቷ ሃሳብ አቀረቡ
በ75 ተቃውሞና በሳቸው ድጋፍ ጸደቀ!
" ማነው ስምህ? "
" ፍቅሬ "
" መምህር ሙላቱ ጋር ሂድና 4ኛ C ዎችን ልገርፍ ስለሆነ
ከቢልልኝ ጋር ሆናችሁ አግዙኝ ብላችኋለች ምስራቅ "
በላቸው!......እኔንኮነው የሚልኩት!
እሺ ብዬ ሄድኩ
" ቲቸር! " አልኳቸው መምህር ሙላቱን
" ምንድነው? "
" አይ፡ ቲቸር ምስራቅን እንዲያግዟቸው ነው "
" ምን እየሰራች? !
" ሊገርፉን ስለሆነ አግዙኝ ብለዋል "
ቲቸር ሙላቱ ሳቅ አፈናቸው
" ጥሩ!..... አለንጋ ብቻ ነው ያላት ማቴሪያል? "
.....ሙያ አደረጉትንዴ?......
" ለማንኛውም ያንን ጉማሬ አለንጋ ያዝ "
አሉና ትላልቅ አጣና ይዘው ተከተሉኝ።
አረማመዳችንና የተሸከምነውን ለሚያይ ገራፊና ተገራፊ
አንመስልም።
ለክፍላችን መገረፊያ የተሸከምኩትን ጭነት ክፍላችን አመጣነው።
ስንደርስ ቢልልኝ የተባለው ጥበቃ ቀድሞ ደርሶ፡ አዳሜን
ሰባብሯታል።
ክፍላችን የሰልስት ለቅሶ አይነት በስሱ ሲለቀስባት ሰማሁ፡፡
ለካ ዱላው ሲበዛ እኔ በሌለሁበት፡ በኔ ላይ ተደፍድፏል!
" ሙላቱ እንዳትለቀው! እራሱ ነው! ያዝ! "
.......ተበላሸሽ ፍቅርሻ!..........
እንደሮኬት ተወነጨፍኩ!
ዞር ስል ቲቸር ሙላቱ በንዴት አጣናውን እንደያዙ ያባርሩኛል
" ሙላቱ አጣናውን ጣል! " ይላል ቢልልኝ በጩኸት
ቲቸር ሙላቱ ገዋናቸው በንፋስ ወደኋላ እየተወጠረ ዞሬ ሳያቸው
ሳቄ መጣ።
" ሌባ ! ሌባ! ሌባ! ".....ሲሉ ደነገጥኩ!
ጥበቃዎቹ ከያሉበት እንደ ግሪሳ ከበው እላዬ ላይ!....
" አለንጋ ከአስተማሪ ይሰረቃል? "
እጄ ላይ ነበር!
Fikre Z Bhere Ethiopia

#ሠናይ ውሎ ውብ ቅዳሜ ተመኘንላችሁ

#StaySafe
የፖለቲካ ቋንቋችን
(በእውቀቱ ስዩም)
እጄን በሳሙና ከመታጠብ በተረፈኝ ጊዜ ለንጀራ የሚሆን ስራ
እሰራለሁ፤ ማታ ማታ ደግሞ አፌ ላይ ነጭ ሽንኩርት፤ ትከሻየ ላይ
ነጭ ጋቢ ጣል አድርጌ ዩቲውብ ላይ እጣዳለሁ፤
ከፊልሙም ከዘፈኑም ቀማምሼ ያገሬን ቃለመጠይቅ ወይም
ውይይት መመልከት እጀምራለሁ:: አልናደድም፤ አላዝንም፤
እንቅልፍ ደርሶ ከነዚህ ስሜቶች ይገላግለኛል : :
አይበልብንና በእለት ተእለት ውሉዋችን በፖለቲካ አማርኛ
የምንግባባ ቢሆን ህይወት እንዴት እጅ እጅ ይል ነበር? ሳስበው
ራሱ ዘገነነኝ! ነገሩን በንፅፅር ለማየት የሚከተለውን ከፍቅር
እስከመቃብር የተቀነጨበ ውብ ስነፅሁፍ አንብቡልኝ፤
“ ሰብለ ወንጌል የገብሬን አንዲር እንዲህ በሩቁ በሰማች መጠን
ያፏ ምሬት እየጣፈጠ፤ ጠቅላላ ስሜቷ ካዘን ወደ ደስታ
እየተለወጠ ሄደች፤ የእንባ ጎርፍ ያበላሸው ፊቷ እንደገና ውበትና
ደም ግባት ትንሽ በትንሽ መቀባት ጀመረ፤”
( ፍቅር እስከ መቃብር፤ ሀዲስ አለማየሁ ገፅ 96)
ይሄንን አንቀፅ አንድ የዘመናችን ፖለቲከኛ ቢፅፈው እንዲህ
ሊያደርገው ይችላል፤
“ በአማራ ክልል ፤ ምስራቅ ጎጃም ዞን ነዋሪ የሆነችው ፤ሰብለ
ወንጌል ከአርብቶ አደርነቱ ጎንለጎን ባህላዊ የሙዚቃ መሳርያ
በመጫወት ህብረተሰቡን የሚያገለግለውን የገብሬን ዋሽንት
ከፍተኛ ትኩረት መከታተል ጀመረች፤ በከባድ ቀውስ ውስጥ
ተዘፍቆ የቆየው ገፅታዋ ተሻሻለ ፤ ቀደም ብሎ የነበረው እና ዛሬ
ድረስ እየተንከባለለ የመጣው ሀዘኗ ባስቸኳይ ተቀረፈ! መስቀልኛ
መንገድ ላይ የነበረ ውበቷ ቀስ በቀስ ወደ ትክክለኛ መስመር
መመለስ ጀመረ! ለረጅም ጊዜ ተራርቀው የነበሩት ፊቷና ደም
ግባቷ ተቀራርበው መነጋገር ጀመሩ! "
( የፀጥታ ችግር እስከ መቃብር፤ አንቀፅ 96)

#ሠናይ ውሎ
#Staysafe
በመንቃት ላይ ባሉ ፍጡራን መካከል
ሕይወት የምንለው እንደጥሬ እህል
በኑሮ ምጣድ ላይ ቢቆላ ቢማሰል
የበሰለው ያራል ጥሬው እስኪበስል ።
ኃይሉ ገብረዮሐንስ
(ገሞራው)

#ሠናይ ውሎ ውብ ቀን!!
የሁለተኛ ክፍል በሮች
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
" ይሄ ክፍል መረጨት አለበት!....ሰላቢ በዛ! "
" ምነው መምህር? "
" ለሽንት ወጥቼ ስመለስ ጭር ይልብኛል "
ከዋናው መንገድ የሚዋሰነው የክፍላችን ግድግዳ ቆርቆሮ ነበር።
ከኋላ ጥግ ያለችውን ቆርቆሮ፡ ሚስማሮቿን አርቆ አሳቢ
ፎራፊዎች አላልተውት በ shortcut ይፎርፋሉ!
" 4 X 3 = ? ስለው ያለቀሰው ልጅ የት ሄደ? "
" አላየነውም ቲቸር "
" ቅድም ሲነፋረቅኮ ቁጥሮቹ የሞቱበት መስሎኝ "
እንስቃለን
" አስታወሳችሁት? "
" አዎ "
" አሁን ወጣ ከማለቴ፡ የት ሄደ? "
" አላየነውም "
" ተባይ ሁላ!! "
ያሬዶ እሳቸው ወጣ ሲሉ፡ ሚስማር የሚያላላ ኮሚቴ ተዋቅሮለት፡
ሾልኮ ሄዷል!
*
በጣም የሚደነግጡት ግን መንገደኞች ነበሩ!
" ሰሃሊትነ!..." አሉ አንዲት ጠና ያሉ ሴት፡ ማሞ ድንገት
ፍልቅ ሲልባቸው ከክፍሉ።
" ምነው ልጄ? በስኳሬ ላይ? ".......
ማሞ እድለ ቢስ ነበር። የደረጃ ተማሪ ቢሆንም፡ አባቱ ግን
ውጤቱን አይቀበሉትም ነበር
ሰኔ ሰላሳ ማሞ ሲገረፍ፡-
" እንዴት 2 ብቻ ታመጣለህ!? "....እየዠለጡ
" አባዬ ላስረዳህ ቆይ! "
" መምህርህን አስረዳ! "
" ኧረ አባዬ! "
" ዝምበል! የአጉኔ ልጅ 71 ሲያመጣ አንተ ሁለት? "
" ኧረ ደረጃችን ነው አባዬ? "
" የምን ደረጃ? "
" እኔ ሁለተኛ ነው የወጣሁትኮ! "
" ምን ያንቀዠቅዥሃል? ረጋ ብትል 71ዱን ትዘግን ነበር! "
**
አንድ ቀን ግን ያቺ መፎረፊያ ተባነነች
ደምሴን ለመስወጣት በተደረገው ኦፕሬሽን የላሉት ሚስማሮች
ወልቀው ጠፉ!..ዝም ብለን አስደገፍናት!
ቲቸር ግስላ ዳኒን ለመኮርኮም ሲንጠራሩ፡ የውጪው ንፋስ
በሃይል ገፍትሯት አናታቸው ላይ ተኛች!
...ሙሴ የተማራችሁ አስታውሱ!.....
መንገደኞች በተከፈተው በኩል እያሰገጉ ቲቸርን በንቀት እያዩ
" አስተማሪም ይፎርፋል?? "

Fikre Z Bhere Ethiopia

#ሠናይ ቀን ከሙሉ ጤና ጋር ተመኘንላችሁ
#Staysafe