ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.49K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ ገፅ የተወሰደ
© #አዳም_ረታ

ጥናት ከሌለ ዕውቀት የለም፡፡
ዕውቀት ከሌለ መለወጥ የለም፡፡
ልበሙሉነት ብቻውን ያለ
ትክክለኛ መረጃ ምንም ነው፡፡
ሳታውቅ 'አውቀሃል' ካለህ አገልግሎትህ መስዋዕት መሆን ብቻ ነው፡፡
ማወቅ ሲገባህ ካላወቅህ ደደብ
ነህ፡፡ ዕውቀት ስሜትን መቆጣጠር አለበት፡፡
ስሜት እውቀትን መያዝ ወይም ማሰር የለበትም፡፡ የለውጥ ስሜትህን አይተው ፣
እሱንም ከዕውቀት አምታተው ሳታውቅ አውቀሃል ካሉህ፣ ጠላቶችህ ናቸው፡፡ሹራቡ ላይ 'ጠላትህ ነኝ' ብሎ ፅፎ እንዲመጣ ትጠብቃለህ?'

ከ አዳም ረታ #መረቅ ከተሰኘው መፅሐፍ ላይ የተቀነጨበ

~ "ማስተዋልን ካዳበርን ሰው የማይናገረውን የመስማት ደረጃ ላይ እንደርሳለን።"
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ሀገረ ፀጉር ቤት
××××××××××××
በፀጉር ቤት ስርዓት በፀጉር ቤት ህግ
ሀገር ማለት ሰው ነው ፀጉሩን ’ሚያሳድግ
ብዬ የነገርኩሽ እውነት ነው ፍቅሬ
ላረጋግጥ ብዬ ይሄውልሽ ዛሬ
ፀጉር ቤት ብሄድ ባላደገው ፀጉሬ
ከንፈር መጠጠልኝ እድምተኛው ሁላ
በደሃው ፀጉሬ አንጀቱ ተበላ
ለካስ በፀጉር ቤት ስርዓት
በስልጣን ወንበር ላይ ወጥቶ ለመቀመጥ
ፀጉር ያስፈልጋል ከራስ የሚመለጥ
ሀብተ ፀጉርን ካላደለሽ ጌታ
ጥረሽ ካላፈራሽ የፀጉር ክምርታ
በፀጉር ቤት ሀገር አታገኝም ቦታ
እናም
እንደ ፀጉር ቤት ስርዓት እንደ ፀጉር ቤት ህግ
ሀገር ማለት ሰው ነው ፀጉሩን ’ሚያሳድግ
የሀብቱን ርዝራዥ በማሽን ቀንሶ
ራሱን ሚያሳምር መሬት ላይ አፍሶ
ለድሃው ወገኑ ቅንጣት ’ማይሳሳ
በዙፋን ልብሱ ሌላውን የረሳ
ብዬ የነገርኩሽ እውነት ነው ፍቅሬ
ካላመንሽ ጠይቂው
ይነግርሻል መስታውቱ እሱት ምስክሬ

© ዳንኤል ከበደ
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
Forwarded from ቅንጭብጭብ
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ፓርኪንግ
አሜሪካን ሀገር ወደሚኖሩ ወዳጆቼ ቤት ሄጄ ነበር፡፡ ከተጋቡ ሁለት ዓመት ሆኗቸዋል፡፡ ቤታቸው ስገባ የቤቱም ዕቃ የቤቱም ሰዎች ዝምታ ውጧቸዋል፡፡ አባ አጋቶን ቤት የገባሁ ነው የመሰለኝ፡፡ እርሱ ክፉ ላለመናገር ሰባት ዓመት ድንጋይ በአፉ ጎርሶ በአርምሞ ተቀምጧል፡፡ ነገር ዓለሙ አላምር ሲለኝ ‹ምነው ያለ ወትሯችሁ ዝምታ ዋጣችሁ› ብዬ ተነፈስኩ፡፡ እዚህ ቤት የነበረውን ሳቅና ጨዋታ ስለማውቀው፡፡ ‹ሳቅና ጨዋታ ዝና ካማራችሁ› ሲባል አልሰማችሁም፡፡
የመለሰልኝም የለ፡፡
@kinchebchabi
በኋላ ነገሩን ሳጠናው ሁለቱም ተኳርፈዋል ለካ፡፡ ‹‹ለመሆኑ እንዲህ ሳትነጋገሩ ስንት ጊዜ ተቀመጣችሁ› ብዬ ስጠይቅ ስድስት ወር ሆኗቸዋል፡፡ ሁሉም በየሥራው ይውላል፤ ማታ ይመጣል፤ ኪችን ገብቶ ያበስላል፤ በልቶ ቴሌ ቭዥን ያያል፤ ከዚያም ይተኛል፡፡ ቢል ሲመጣ ይህንን እኔ ከፍያለሁ ብሎ አንዱ ወረቀት ጽፎ ይሄዳል፤ ሌላው በተራው ይከፍላል፡፡ ይቺ ናት ትዳር፡፡
ድሮ የሰማሁትን ቀልድ ነበር ትዝ ያሰኙኝ፤ ባልና ሚስቱ ተኳርፋው አይነጋገሩም አሉ፡፡ ቤቱ እንደ መቃብር በጸጥታ ተውጦ ከርሟል፡፡ አንድ ቀን ባል ሌሊት አሥር ሰዓት የሚነሣበት ጉዳይ ገጠመው፡፡ ከተኛ መነሣት የሚከብደው ቢጤ ነበርና የመቀስቀሻውን ሰዓት ሊሞላ ሲስበው ተበላሽቷል፡፡ አዘነም፤ ተናደደም፡፡ ምን ያድርግ፡፡ ባለቤቱ ገና ከሥራ አልገባችም፡፡ ‹የወደዱትን ሲያጡ የጠሉትን ይመርጡ› ነውና፡፡ በቁራጭ ወረቀት ላይ ‹አሥር ሰዓት ላይ ቀስቅሽኝ› ብሎ ጽፎ በራስጌው ባለው ኮመዲኖ ላይ አስቀመጠና ተኛ፡፡
ሚስቱ ስትመጣ አየችውና ስቃ ተኛች፡፡ ልክ ከሌሊቱ አሥር ሰዓት ነቃችና በዚያው በቁራጭ ወረቀት ላይ ‹አሥር ሰዓት ሆኗልና ተነሣ› ብላ ጽፋለት ተኛች፡፡ እርሱ ዕንቅልፉን ለጥጦ ለጥጦ ሲነሣ ነግቷል፡፡ ተናደደ፤ ግን እንዳይናገራት ለካስ ተኳርፈዋል፡፡ እዚያው ወረቀት ላይ ‹በጣም ታሳዥኛለሽ› ብሎ ጻፈላት፡፡
እነዚህ ወዳጆቼ ይህን ነበር ያስታወሱኝ፡፡ አሁን እንዲህ ያለው ኑሮ ምን ዓይነት ኑሮ ይባላል? ብዬ ስም ፍለጋ ብዙ ጊዜ አሰብኩ፡፡
👉 @kinchebchabi
ይህን እያሰብኩ እያለ አንድ ዕቃ ለመግዛት ‹ካስኮ› ወደሚባለው አሜሪካ ውስጥ ካሉት ታላላቅ መደብሮች ወደ አንዱ ከእነዚሁ ወዳጆቼ ጋር ተጓዝን፡፡ እዚያ መኪናችን ለማቆም አራት የፓርኪንግ ፎቆችን መውጣትና እንደ አዲስ አበባ ስታዲዮም የተለጠጠውን ሰፊ የማቆሚያ ሜዳ ማካለል ነበረብን፡፡ ለዓይን እስኪያታክት ድረስ መኪኖቻ ተኮልኩለውበታል፡፡ በዓይነት ባይነታቸው፡፡ ረዥም፣ አጭር፣ ሽንጣም፣ ቁመታም፤ ያበጠ፣ የከሳ፣ ግልጽ፣ ድፍን፣ ነጭ፣ ቀይ፣ ቢጫ፣ አረንጓዴ፣ ሰማያዊ፣ ወይን ጠጅ፣ ምኑ ቅጡ፤ ተደርድረዋል፡፡ ጎን ለጎን፣ ፊትና ኋላ፤ በኋላ መመልከቻቸው ሊነካኩ እስኪደርሱ ድረስ ተደርድረዋል፡፡
የሚገርመው ግን አንዱ ከሌላው ጋር አያወሩም፣ አይጫወቱም፣ ኧረ እንዲያውም አይተዋወቁም፤ አንድ ያደረጋቸው በአንድ የፓርኪንግ ሜዳ መቆማቸው፣ ጎን ለጎን መሆናቸው፣ በአንድ ጣራ ሥር ውሎ ማደራቸው ብቻ ነው፡፡ የዚያኛውን ጠባይ፣ ሥሪት፣ ዓላማና፣ የኑሮ ጓዳ ይህኛው አያውቅም፤ እንዴው በአንድ ፓርኪንግ ቦታ ብቻ አብሮ ቆሞ ማደር፡፡ እነርሱምኮ ‹ቢል› አለባቸው፡፡ የፓርኪንግ ቢል፡፡
ያኔ ስም አገኘሁለትና እነዚህን ወዳጆቼን ‹የእናንተ ኑሮኮ ፓርኪንግ ነው› አልኳቸው፡፡ ሁለቱም ወደ እኔ ዞሩ፡፡ ‹እስኪ እነዚህን መኪኖች እዩዋቸው፤ አይፋቀሩ፣ አይጣሉ፣ አያወሩ፣ አይጫወቱ፣ አይወያዩ፣ አብረው አይሠሩ፣ አብረው መከራ አይካፈሉ፣ አብረው አይደሰቱ፤ ግን በአንድ የፓርኪንግ ቦታ ቆመዋል፡፡ ሁሉም በየራሱ መጥቶ ቆመ፡፡ ሁሉም በየራሱ ተነሥቶ ይሄዳል፡፡ የእናንተስ ከዚህ በምን ተለየ፡፡ ሁለታችሁም በየራሳችሁ ትውላላችሁ፤ ማታ ስትመጡ ቤታችሁ ውስጥ ፓርክ ታደርጋላችሁ፤ በቃ›
ከልባቸው ነበር የሳቁት፡፡ ፍርስ እስኪሉ፡፡
ለሰው አንድ ቦታ መሥራት፣ አንድ ቦታ መኖር፣ አንድ አልጋ መተኛት፣ በአንድ ቢሮ መዋል፣ አንድ ሕንፃ ላይ መኖር ብቻውን ከሰው ጋር መኖር አያሰኘውም፡፡ ይኼንንማ መኪኖችም ይኖሩታልኮ፡፡ ያውም ሰላማዊ በሆነና ማንም ማንንም ሳይነካ፣ ማንም በማንም ቦታ ላይ ሳይደርስ፤ ግን ይህ ፓርኪንግ እንጂ ኑሮ አይደለም፡፡ ኑሮ ያፋቅራልም ያጣላልም፤ ያገናኛልም፣ ያወያያልም፤ ኑሮ መስተጋብር አለው፡፡ አንደኛው በሌላው ውስጥ ቦታ ሊኖረው ይገባልኮ፡፡
ወዳጅነትኮ አብሮ ከመዋልና ከመኖር፣ ከመሥራትም በላይ ነው፡፡ አንቺ ባልሽ ሳይደውል ሲቀር ሲጠፋ፣ ያስለመደሽ ነገር ሲቀር፣ አንዳንድ ነገሩ ሲለወጥ ቅር የማይልሽና ምንም የማይሰማሽ ካልሆነ ድሮም ትዳር ሳይሆን ፓርኪንግ ነበር የመሠረታችሁት፡፡ እስኪ ያንን መኪና ተመልከቱት ተነሥቶ ሄደ፤ ከጎኑ ያለው መኪና ምን ተሰማው? ምንም፡፡ ሌላው ደግሞ መጣ፤ አያችሁ ፓርኪንግ ሲሆን እንደዚህ ነው፡፡ ወዳጅህ ቢኖር ባይኖር፤ ሰላም ቢልህ ባይልህ፣ ቢመጣ ባይመጣ፣ ካንተ ቢለይ፣ ባይለይ ምንም ካልመሰለህ ይህ ፓርኪንግ እንጂ ወዳጅነት አይደለም፡፡
ለአንዳንድ ሰዎች ወዳጅነት ማለት በፈለጉበት ጊዜ መጥተው ሊያቆሙበት የሚችሉ ፓርኪንግ ይመስላቸዋል፡፡ አይደለም፡፡ ወዳጅነት ጎን ለጎን አይሆንም፡፡ ወዳጅነት አንዱ በሌላው ውስጥ ቦታ ሲኖረው ነው፡፡ ለዚህ ነው ያ ወዳጅህ ሲቀር ክፍተት የሚሰማህ፡፡ ‹ሰው ቢሄድ ሰው ይመጣል› እያሉ የሚዘፍኑ አሉ፡፡ እነዚህ ፓርኪንግ እንጂ ወዳጅነት የማያውቁ ናቸው፡፡ በወዳጅነት ውስጥ ‹ሰው ቢሄድ ሰው ይመጣል› የሚባል መፈክር ተይዞ ሲቀበሉና ሲሸኙ መኖር አይቻልም፡፡ ዘላቂ ወዳጅ የሌለው ፓርኪንግ ብቻ ነው፡፡ እርሱም እንኳን አንዳንዴ ለአንድ ሰው ተመድቦ ይሰጣል፡፡
አሁን አሁንማ በኛም ሀገር የፓርኪንግ ኑሮ እየተለመደ ነው፡፡ ጎረቤቱን የማያውቅ መንደርተኛ፣ ግድግዳ የሚጋራውን የማያውቅ ባለ ኮንዶሚኒየም፣ አብሮ ነዋሪውን የማያውቅ ደባል እየመጣ ነው፡፡ በአንድ ሕንፃ ላይ እየሠሩ ፈጽሞ የማይተዋወቁ ሰዎች እየተፈጠሩ ነው፡፡
እንዲያውም አንድ ወዳጄ ለአንድ የሥራ ጉዳይ አንድ ባለሞያ ይፈልግ ነበርና አንድ ወዳጁ ስልክ ይሰጠዋል፡፡ ጎበዝ ባለሞያ ነው በዚያውም ተዋወቀው ይለዋል፡፡ ስልኩን ተቀብሎ ይደውልለትና ስለ ሥራው ይነጋገራሉ፡፡ ይግባባሉ፡፡ እጅግ የተሻለው ነገር በአካል መነጋገሩ ነበርና ‹ቢሮህ የት ነው› ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ አድራሻውን ሲነግረው እዚያ እርሱ ያለበት ሕንፃ ላይ ነው፡፡ የቢሮ ቁጥሩን ይጠይቀዋል፡፡ እጅግ የሚገርመው ነገር የዚያ ባለሞያ ቢሮ ከእርሱ ቢሮ ጎን ነበረ፡፡ ሦስት ዓመት ሠርተዋል አይተዋወቁም፡፡
አያችሁ ፓርኪንግ እንዲህ ያደርጋል፡፡ 👇
የአድዋ አዋጅ እና እምዬ ምንሊክ ብልሀት

#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

"የዳግማዊ ምኒልክ የክተት አዋጅ ከወራሪዎቹ እንቅስቃሴ አንፃር ከተጠበቀበት ወቅት ዘግይቷል፡፡ ይህም በአፍሪካና አውሮፓ ሀገሮች አይን ምንሊክን እንደ ፈሪ እንዲታዩ አድርጎ ነበር ይላል" ራይሞን ጆንስ የአድዋ ጦርነት በሚለው መፅሀፉ፡፡ ፀሀፊው ሲቀጥል "የመሪ ብልህነት የሚለካው ቸኩሎ በመወሰኑ ሳይሆንበወቅቱ ያሉትን አመቺ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ሲያሳልፍ ነው ይላል፡፡
የክተት አዋጁ በራሱ በወቅቱ ኢትዮጵያ የነበረችበትን የፈተና ጊዜ ማለፍንና የመረጋጋት ዘመን መምጣቱን ገላጭ ከመሆኑም በላይ፤ ህዝቡ ከሃይማኖት፣ ከዘርና ግዛት ማስፋፋት ፍጭት በመውጣት ስለ አንድ ሀገሩ ደህንነት በጋራ የሚቆም እንደነበረ ያረጋግጣል።

" እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ፣ አገር አስፍቶ አኖረኝ" ሲሉ ከአድዋ በፊት ጠንካራ የውጭ ጠላት አልነበረምና ጦርነት በሌለበት ሀገር እርጋታ ላይ ሆና አስተዳደሯን እያደረጀች እንደነበረ ይነግረናል።

" አሁንም አገር የሚያጠፋ፥ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን ባህር አልፎ መጥቷል። እኔም ያገሬን ከብት ማለቅ የሰውንም መድከም አይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር።"

ይህ ንግርት በወቅቱ ኢትዮጵያ የነበረችበትን የመከራ ዘመን "ክፉ ቀን" ደግመን እንድንመረምር ያደርገናል። በከ1881 ዓ.ም ጀምሮ የነበረው በኢጣሊያኖች አማካኝነት ወደ ሀገር የገባው የከብት በሽታ ለአራት አመታት ህዝቡን ከብቱን ጎድቶ ነበር። ረሀብ በመፅናቱ እናት ልጀቿን የበላችበት ክፉ ዘመን ነበር። እናም የዓድዋ ጦርነት ለምን ዘገየ ሲባል ራሱ አዋጁ ይነግረናል " የሰውን መድከም የከብቱን ማለቅ አይቼ እስካሁን ዝም ብለው" ይህ ሀሳብ ከላይ ራይሞን ጆንስ ከጠቀሰው ጋር የሚስማማ ነው፡፡

እምዬ በጥሪያቸው " ማርያምን አልምርህም! ለዚህ አማላጅ የለኝም " ብለዋል። ግን ሀገሬው በሙሉ ሃይማኖቱን አስቀድሞ በእምነቴ አልተጠራሁም ብሎ ሀገሩን ከመታደግ አልቀረም። ንጉሱን ተከትሎ ከንጉሱ ጋር ተዋደቀ እንጂ።

ለዛ ነው እምዬ ከምንም በላይ ሀገር እንደሚቀድም አሳይተው በአንድነት የመምራት ብቃት ነበራቸው የሚያሰኘው።

ክብር ይሁን!

#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia

@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
©#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

በትግል የተገኘ ውበት
(በላይ በቀለ ወያኔ)

ባሩድ ባሩድ የሚል ፣ የገላሽ መአዛ
ዜና ዜና ሚሸት ፣ ያንደበትሽ ለዛ
እንደ እግረኛ ጦር...
የተደረደረው ፣ የሚማርክ ጥርስሽ
እንደ ሻብያ ጦር...
የሚንቀጠቀጠው ፣ ዳሌሽ እና ጡትሽ
ስልጣን ስልጣን የሚል ...
ቢስሙት ማይሰለች ፣ የስስ ከንፈርሽ ጣ'ም
ይህ ሁሉ ውበትሽ ፣ ሚናፍቀው በጣም
በፅኑ ትግል እንጂ ፣ በተፈጥሮ አልመጣም

#ፍትህ_ለሰበታ_በሬዎች 😁
@Simetin_Begitim
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
ዕንባህን ባረገኝ

© ሰሊና

ከውስጥ ስሜትህ ከልብህ ፈልቄ
የአጉል ኩራትህን ሽፋኑን ፈልቅቄ
የዐይኖችህን ብሌን በዕንባ ሞልቼ
ቅል ባሳክላቸው በዕንባ አሳብጬ
ደም ባስመስላቸው ስሜትህን ገልጬ
ሲቃ ብሆንብህ ድምፅህን ዘግቼ
ጉንጮችህን ባርስ በመንታ ወርጄ
ከዛም...
ይህን ሁላ ሄጄ ሁሉን አቋርጬ
ብገኝ እመርጣለሁ ከንፈርህ ላይ ሞቼ

#መልካም_ቀን
ውብ ውሎ ከሙሉ ጤና ጋር ተመኘንላችሁ!!
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

፬ እርምጃ
°°°°°°°°°°
[ናዝሬት]

ከቦሌ እስከ ማርያም አራት እርምጃ ነው
ስሰክር ስሰክር ወይ ሲለኝ ድንግር ግር
እኔ የምራመደው።
እህ በይኝ እና ልንገርሽ አንቺዬ ስሚኝ ባዛኝቱ
ባይጥምም አይመርም ያፍቃሪ እውነቱ
የናፍቆት ዝለቱ
እህ በይ እህ በይ እህ በይ በማርያም ሰሚው እውነታዬን
ስሰክር ስከፋ የምረግጠውን ሃቅ የውነት እርምጃዬን

በጎዳናው መሃል በድንጋዩ ንጣፉ ካብታሞቹ ሰፈር
ስኔድ ትዝ ካለሽ ወሬ ስንረሳ ወሬ ስንጀምር
ምነዋ አንቺዬ
እንደውም ፍጡራን አለም ከሰሩበት
በከተማ መሐል ገነት የሚመስል አነስተኛ ገነት ከቆረቆሩበት
አዎን እዛ ሰፈር አንድ ሁለት ብዬልሽ
ባየሁት ያልሽውን ስካር ሰክሬልሽ
ቆምያለው ብቻዬን አንቺን እያሰብኩኝ
ለሊቱ ተጋምሷል ለኔ ግን ነጋልኝ
ሰሞኑን አንቺዬ ያመጣሁት ፀባይ
ለሰው ሲጨልም ነው እኔ ንጋት የማይ
ብቻ ቆሜ ሳለው ድንጋዩን አየሁት የጎዳናውን ጠርዝ
ባሳቤ ውስጥ አየው የፍቅርን ስንደዶ ከሰፌዱ ስንመዝ
ቱ.. አፌን እሳት ይፍጀው
ታቦት ፅላቴን ነው ድንጋይ ነው የምለው?
ያ ድንጋይ ለኔማ ከአክሱም በላይ ነው
ፍቅርሽ እና ፍቅሬ በፍቅር የጠረበው
ያ ድንጋይ ለኔማ የምስጢር ፅላት ነው
በስውር መዳፋ ስውር ድብቅ ህመም እግዜር የቀረፀው
ሙሴው የኔ መዳፍ ናፍቆት ሊሰባብር ለሁለት የከፈለው
እናም ይሄ ፅላት የጎዳናው ማዕዘን
ከንፈር አነካክሶ ዙፋን ሲሸልመን
በንግስና ዳና የረገጥነው ወጉ
ያ ነው ለኔ ማለት የ1 እርምጃ ጥጉ
...
የሰካራም ነገር ምን አስቀባጠረኝ
ብቻ ምን አለፋሽ ከዚሁ ድንጋይ ስር እርምጃ ጀመርኩኝ
.....
ከቦሌ እስከ ማርያም አራት እርምጃ ነው
ናፍቆትሽ ሲመራኝ እኔ ምራመደው
ፅላቴን አልፌ አይኔን ስወረውር
ልቤ ተላተመ ከአንድ ደጅ እግር ስር
እግዜር ይቀድሰው የደጃፉን ሰሪ ያፀዱን ባለቤት
ከበራፉ አብቧል የፍቅራችን ትንፋሽ የፍቅራችን ሂወት
ለኔና ለልቤ ላንቺና ለልብሽ ከለላ ለመሆን ጥላውን የጣለው
እሳት ከከለለው ከገነት ደጅ ይልቅ ይሄ ደጅ ንዑድ ነው
እርምጃ ቁጠሪ ከደጁ ትይዩ እስከ ማርያም ድረስ
ሁለት ይቀረናል ፍቅርሽን ለመሸሽ ፍቅሬ ጋ ለመድረስ
----------------------------

ከቦሌ እስከ ማርያም አራት እርምጃ ነው
ስሰክር ስሰክር ወይ ሲለኝ ድንግር ግር
እኔ የምራመደው።
እህ በይኝ እና ልንገርሽ አንቺዬ ስሚኝ ባዛኝቱ
ባይጥምም አይመርም ያፍቃሪ እውነቱ
የናፍቆት ዝለቱ
እህ በይ እህ በይ እህ በይ በማርያም ሰሚው እውነታዬን
ስሰክር ስከፋ የምረግጠውን ሃቅ የውነት እርምጃዬን
ሶስተኛው እርምጃ ከሁሉም ይልቃል
እዚኛው ገፅ ላይ ልቤ ምት ያቆማል
ምክኒያቱም አለሜ
ይሄ ሰፈርሽ ነው የግዛትሽ ጥለት
በሌት አነደደኝ የፀሐይሽ ግለት
ሰማይ በዚ ቦታ ሁሌም የጠራ ነው
ጨለማውን ሊገልጥ ኮከብ ጨረቃ ነው
360 ቀን ፀሐይ አትዞርም
ለ30 ቀናት ጨረቃም አትጎልም
እንደ ፀባኦቱ ልክ እንደ ማደርያው
የመቅደስ እጣን ነው የዚ ሰፈር ሽታው
ለካንስ በሌሊት እንደኔ ሲሰክሩ
እዚ ሰፈር አለ የመለኮት ክብሩ
ብቻ ምን አለፋሽ
የዳዊት በገና የእዝራ መሰንቆ
እዚ ሰፈር አለ ቤትሽ ተደብቆ
በቦዘዘው አይኔ እጣኑን ብጠራ እግዚያርን ባየው
አልጠየቅ እኔ ይሄ ሰፈርሽ ነው
የማይጠፋው ፋኖስ የማያልቀው ሻማ
በርምጃዬ መሐል አለ ፍቅርሽ ' እማ '
ሰሶስተኛው እርምጃ እንደተረገጠ ነጋ መሰል ሌቱ
ድሮስ ከሰፈርሽ አይደለም አለሜ የዚ ንጋት ቤቱ?
-----------------------------
ከቦሌ እስከ ማርያም አራት እርምጃ ነው
አይንሽን ስራበው
ክንድሽን ስራበው
ልብሽን ስራበው
እኔ የምራመደው።
አራተኛው ዱካ የልቤ ማረፍያ
የእመቤቴ አፀድ የልፍኟ መኖርያ
ድሮም የፍቅር ገፅ ሲነበብ አርስቱ
ልብ ነው የሚደርስ ከገፁ ፍፃሜ ከማርያም ከእናቱ
ከቦሌ እስከ ማርያም አራት እርምጃ ነው
ልቤ ደጇን ሲራብ እናት ሲናፍቀው
እግሬ የሚራመደው
አናጭ አፍራሽ ልጅሽ የመንገዱ ጌታ የርምጃ ፈጣሪ
ቅድስት የተባረክሽ አስታርቀሽ አዳሪ
ታድያ ከደጃፍሽ ጋን የሚያስንቅ ልሳት የረከሰ ገላ
ይዤ ምቆምበት አላገኝም ጥላ
ይልቅ ተሻግሬ ከመንገዱ ማዶ
እኔ ልጅሽ አለኝ
የምነግርሽ ብስራት የማረዳሽ መርዶ
- ብስራት
የምስራች ማርያም
የማፈቅራት ፍቅሬ ያቺ ውብ አበባ
ልትሞሸርልሽ ከደጃፍሽ ቀርባ
ቀናቱን ቆርጣለች
እናቴ ጠብቂያት ተክሊል አዘጋጅተሽ
- መርዶ
ከሰፈሬ ደጅሽ እስክመጣ ድረስ የረገጥኩት መንገድ
ያደከመኝ እግሬ ስካሬም እስኪበርድ
ከዚው ከደጃፍሽ እንዳታስጠልይኝ
እማምላክ እናቴ ፍቃድሽን ስጪኝ
ስለ እማምላክ ብዬ ልብ እያራራውኝ
ጉርሴን እንድበላ ስምሽን አውሽኝ
በንተ ስምሽ ልኑር እስኪለቀኝ ስካር
ፈቅደሽ ካደረግሽኝ ያድባርሽ ስር አድባር
ልመና ነበረኝ ስለ ቸርነትሽ
ለኔ ተለመኝኝ እማምላክ እባክሽ
አበርችኝ እናቴ ልቤ እንዳይዝልብኝ
ሰርጓን ባላደምቅም እንቅፋት እንዳሎን ቀናት ለምኝልኝ።

ተፈፀመ።
ALONE : @termo_dynamics

©ቅንጭብጭብ ኢትዮጵያ