ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.5K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
#የማንቂያ ደውል ይሁነን!

"ሳል፣ ትኩሳት፣ ለመተንፈስ መቸገርና የራስ ህመም የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምልክቶች ቢሆኑም አንዳንድ ሰዎች ምንም አይነት ምልክት ሳያሳዩ #ፖዘቲቭ ሊሆኑና ወደ ሌሎች ሰዎች የማስተላለፍ ዕድል ሊኖራቸዉ ስለሚችል ምልክቶች ታዩም አልታዩ የሚደረጉ መሰረታዊ የጥንቃቄ መመሪያዎችን መተግበር አማራጭ የሌለዉ ተግባር ነው" - አቶ አለማየሁ አልዬ (የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ)

#Stayhome
#staysafe
መርዶ
[በዕውቀቱ ሥዩም]
____________
ተምትም አሻግሬ የሚባል ጓደኛ ነበረኝ ። አይ ተምትም አሻግሬ !
ባሰብሁት ቁጥር ሳቄ ዝም ብሎ ይመጣል ።
ተምትም ንግግር በማስረዘም ተወዳዳሪ የለውም ። ለምሳሌ
አብረን አምሸተን ስንለያይ እኔ ''ቻው!'' እለዋለሁ። እሱ ግን
'' ....ደህና አምሸተህ ሌሊቱን በሰላም ታሳልፍ ዘንድ
እመኝልሃለሁ!'' ይላል ።
ቁርስ ልንበላ ስናዝዝ '' ቋንጣ ፍርፍር!'' ብሎ እንዳይገላገል ''
''እስቲ እባክሽ የኔ እመቤት ፣ ሽንኩርት ሳይታይ ፣አንድ ጥሩ የሆነ
ከቋንጣ የተሰራ የእንጀራ ና የልዩ ልዩ ነገሮች ፍርፍር አምጭልኝ
....'' ይላል ።
ተምትም እና እኔ አንድ ቀን የጓደኛችን የደመቀ ባይከዳኝን
ወንድም ሞት ሰማን። መርዶውን ለመናገር የታጨን ሁለታችን
ነበር። ''እኔ ቀስ ብዬ ብነግረው ይሻላል !....አንተ ታስረዝማለህ!''
አልኩት። እሱ ግን የንግግር ሱስ ስላለበት ተቃወመኝ።
''ምን ነካህ!....መርዶ እንዲህ ቀላል ነገር ነውንዴ ?....እኔ ነኝ
በዘዴ ልነግረው የሚገባ ....ይልቅ ራሱን የሳተ እንደሁ አንተ
ትደግፈዋለህ!'' አለኝ ።
ከብዙ ጭቅጭቅ በኃላ እሱ አሸነፈኝ ። በማግስቱ ሌሊት ወደ
ደመቀ ቤት ስንሄድ ''አደራ እንግዲህ እንዳታንዛዛው....ወንድምህ
በመኪና አደጋ ስላረፈ ርምህን አውጣ ! ማለት ብቻ ነው'' አልኩት
።።
እሺ ብሎኝ ገባን።
ደመቀ ከእንቅልፋ ተነስቶ በር ከፈተልን በኃላ {ምነው በደህና?}
አለን ። ምልክት ሳሳየው ተምትም ንግግሩን ለቀቀው ''ውድ
የተከበርከው ወንድማችን ደመቀ ባይከዳኝ....ወንድምህ ከሁለት
ቀናት በፊት እናቱን ለመጠየቅ መኪናውን እየነዳ መውጣቱን
ሳታስታውስ የምትቀር አይመስለኝም....ያን ቀን ከሌሎች ቀን
የከበደ ቀን ነበር ....ሰማዩ ርጉዝ አህያ መስሏል ።ወንድምህ
ምነው ዛሬ ቀፈፈኝ እያለ ለራሱ በመናገር መኪናውን በአባይ
ጎዳና ማሾር ጀመረ ...ጸጥ ያለ መንገድ ነበረ ...ምነው የሆነ
መልአክ ተመለስ ብሎ ሹክ ባለው !...ዋ! .....ጎደሎ ቀን ! ዋ
የተሰበረ ዕድል ....ምንኛ ያሳዝናል! ....በአባይ ሽለቆ ውስጥ
ሲገባ የመኪናውን ፍጥነት አልቀነሰም ፤ እናም ወደ ግራ
እዞራለሁ ሲል መኪናው እንደ ኳስ ነጠረች !... ከዚያም ሙሽራ
ሙሽሪትን እንደሚስም ሁሉ መኪናዋ ባቅራቢያው ካለ ቋጥኝ ጋር
ተሳሳመች....ግው! ጓ!
ወንድምህ ! ያ! ቅን ወንድምህ ከዚህ የጨቀየ ዓለም ወደ
ብርሃናዊውና የማይከስመው ዓለም የተሸጋገረው በዚህ ጊዜ
ነው !'' አለና ትንፋሹን ዋጠ።
ደመቀ ግን '' አልገባኝም !'' ብሎ ወደ እኔ ተመለከተ ።
'' ወንድምህ አርፏል !'' አልኩት በፍጥነት ። እሱም በፍጥነት
ወደቀ ።
#stayHome
#Staysafe
ʟօʋɛʀs ɛʍքɨʀɛ :
"እኔ_ደግሞ …."
(አሌክስ አብርሃም)

ምንድነው እንደዚህ - ፊቴን በብረሃን
ከንፈሬን በውብ ሳቅ - የሚያጥለቀልቀው፣
ምንድነው ከልቤ - ኮለል ያለ ሰላም - በጧት የሚፈልቀው?።
እያልኩ አስባለሁ ……

እኔ ደግሞ …..
ምንድነው ሰው ሁሉ- ነጫጭ ክንፍ አብቅሎ - መ,ላክ የመሰለው፣
ምንስ ነው ሰማዩ - እንዲህ ተጠቅልሎ -
በጀ የምይዘው - መሃረም ያከለው።

ኧረ ምን ታምር ነው - መሬት መዞር ትታ - በፎይታ ያቆማት፣
ምንድነው ጨረቃን - ከሰማይ አወርዶ - ምድር -ያሳረፋት?።
እያልኩ አስባለሁ

እኔ ደግሞ …..
የጠሉኝን ሁሉ - ድንገት የመውደዴ፣
መሬቱን ለቅቄ - ባየር ላይ መንጎዴ።

ምንድነው ሚስጥሩ-ቆይ ውስጤን ምን ነካው፣
አለም እንዲህ ጠቦ - በርምጃ ሚለካው።

ውቂያኖስ በፍኘ - ተጨልፎ የሚደርቅ፣
ተራራው በክንዴ - ተጎሽሞ ሚደቅ።

ማነው በመንገዴ - ሳልፍ እልል የሚለው አበባ ነስንሶ፣
ማነው ግማሽ ልቤን - ሸርፎ የወሰደው -በትልቁ ቆርሶ?።
ኧረ ምን ታምር ነው ?
እያልኩ አስባለሁ

እኔ ደግሞ …..
መንገዳኛው ሁሉ - የተከፋ ፊቱን -
በማን ተነጠቀ፣
ከጨፍጋጋ ፊቶች - የዚህ አይነት ብርሃን - እንዴት ፈነጠቀ።

ሚሊየን ህፃናት - ቀልብ በሚነሳ -
ስርቅርቅ ድምፃቸው፣
የት ቢዘምሩ ነው - ልቤ ሚሰማቸው።

በምን ተአምር ነው - ዛፎች የሚያረግዱት፣
በምን ጉድ አስማት ነው - የሰማይ ከዋክብት
ቁልቁል የሚበሩት።
እያልኩ አስባለሁ ….

እኔ ደግሞ ….
ቤሳ ቤስቲን ፍራንክ - ኪሴ ሳይጨመር፣
አመት የለበስኩት - ልብሴ ሳይቀየር።

የዘወትር ጉርሴ - ጣሙ ሳይነካ፣
እኔነት እኔ ውስጥ - ተቀይሯል ለካ።

እኮ በምን ምክንያት - እኔ ተቀየርኩኝ፣
እንዴት እኔ ነኝ ስል - እኔ ሌላ ሆንኩኝ።
እያልኩ አስባለሁ ……..
ለ ካ ስ ……………………..አፍቅሬሽ ነው!!!
#StayHome
#StaySafe