AddisWalta - AW
45K subscribers
41.7K photos
204 videos
20 files
16.6K links
This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.

For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
Download Telegram
እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያ ከዋልታ ቴቪ ሰኔ 27/2014
https://fb.watch/e2e_4aFzJW/
ጠ/ሚ ዐቢይ መሰናክሎች የዕድገት እና የመሻሻል ዕድሎች ናቸው አሉ

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) በመንገዳችን ላይ የሚያጋጥሙንን ችግሮች ተቋቁመን ማለፍ ከቻልን መሰናክሎች የዕድገት እና የመሻሻል ዕድሎች ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ባለፍንባቸው ጊዜያት ጎን ለጎን በጎ ነገሮችንም መፍጠር ችለናል ብለዋል።

የተለያዩ መሰናክሎችን በመቋቋም ጭምር በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች የጠንካራ ሥራ ውጤቶች ናቸው ሲሉም አክለዋል።

ፕሮጀክቶቹ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተሰነቀው ራዕይ ማሳያ ምልክቶች ናቸውም ነው ያሉት።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነው

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በሁሉም ክፍለ ከተሞች እየተሰጠ ይገኛል።

በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎች ፈተናውን ያለምንም ችግር እየወሰዱ ሲሆን ፈተናው ለ3 ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል።

የፈተና ደኅንነት ለመጠበቅ እና የፈተናውን ሂደት ለመከታተልም ቀደም ሲል የተዋቀረው ኮማንድ ፖስት 10 የፀጥታ አካላት ማሰማራቱ ተጠቁሟል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ 179 የመፈተኛ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን በዚህም 71 ሺሕ 832 የሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ እንደሚገኙ ከከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ኢንስቲትዩቱ በአንዳንድ አካባቢዎች ከባድ ዝናብና ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊከሰት እንደሚችል አሳሰበ

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ እርጥበት አዘል አየር በአጭር ጊዜ ተጠናክሮ በሚቀጥሉት ቀናት ከባድ ዝናብ በመፍጠር ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ኅብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ።

በኢንስቲትዩቱ የአየር ሁኔታና የአየር ጸባይ ትንበያ ዳይሬክተር ጫሊ ደበሌ እንደገለጹት ከደቡባዊ ንፍቀ ክበብ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው እርጥበት አዘል አየር ካለፉት ሳምንታት በበለጠ በቀጣዮቹ ሳምንታት ሊጠናከር እንደሚችል ትንበያዎች ያሳያሉ።

በዚህም የጎርፍ አደጋ ሥጋት ያለባቸው አካባቢዎች ላይ አደጋ እንዳይፈጠር ከወዲሁ የመከላከል ሥራ ማከናወን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በተለይ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በሆኑ ወንዞችና ተዳፋታማ አካባቢዎች የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተጠናከረ የጥንቃቄ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በተለይ በከፍተኛ ቦታዎችና፣ በደጋ አካባቢ የሚዘንበው ዝናብ በዝቅተኛ አካባቢዎች ላይ የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል ስለሚችል አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
https://www.facebook.com/489211707826282/posts/pfbid02WehphEmXX2bTU9SHHVRWH9QNTc6r88p7VDwA7a1rbm3sdttdvKbzyYjPP3SwDovSl/?app=fbl
ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን አስጀመሩ

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በክልሉ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን አስጀመሩ።

በክልሉ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በሚሰጠው ፈተና 4 ሺሕ 900 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ፈተናውን ባስጀመሩበት ወቅት በክልሉ ለፈተናው አስፈላጊው ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን ገልጸው በተለይም በተማሪዎች መካከል ኩረጃ እንዳይኖር፣ ፈተናው እንዳይሰረቅ እና የፈተናው አሰጣጥ ውጤታማ እንዲሆን ከማስቻል አንፃር በቂ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

የክልሉ መንግሥት ለትምህርት ጥራት በተለይም የተማሪዎች ውጤት እንዲጎለብት በትኩረት እየሰራ መሆኑን አንስተው የሚመለከታቸው አካላትም የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በክልል ደረጃ በከተማና በገጠር በሚገኙ 24 የፈተና ጣቢያዎች ፈተናው እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ተስፋዬ ኃይሉ (ከሀረር)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
የቀን 6፡00 ዜና በቀጥታ ከዋልታ ቴቪ ሰኔ 27/2014
https://fb.watch/e2pAZiNlAP/
በገላን ከተማ በ613 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ናቸው

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) በገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ፒኤችዲ) የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ገላን ከተማ የተሰሩትን ፕሮጀክቶች እየመረቀ ይገኛል።

በገላን ከተማ በ613 ሚሊየን ብር የተገነቡ ለሕዝብ ጥያቄ ምላሽ የሆኑና የከተማይቱ መሰረተ ልማት የሆኑ 52 ፕሮጀክቶች ናቸው እየተመረቁ የሚገኙት።

በምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝን ጨምሮ ከፌዴራልና ከክልል የተወጣጡ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ለረጅም ዓመታት ስንጠይቅ የነበረ ጥያቄያችን ዛሬ ምላሽ ማግኘቱን የገለጹት የገላን ከተማ ነዋሪዎች ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው በመመረቃቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል።

በታምራት ደለሊ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ሊጉ የበጎ ፈቃድ መርኃ ግብሩን በደብረ ብርሃን ከተማ ጀመረ

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ የ2014/15 ዓ.ም በጎ ፈቃድ መርኃ ግብሩን በደብረ ብርሃን ከተማ ጀምሯል።

''በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ'' የሚል ስያሜ ያለው መርኃ ግብር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ፣ የደም ልገሳና ሞዴል የከተማ ግብርና ሥራዎች መጎብኘትን ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል ዓለሙ ስሜን (ፒኤችዲ) ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ካሳሁን እምቢአለ አባቶቻችን ነጻነቷ ሳይደፈር ያስረከቡንን ሀገር ወጣቱ ዘመኑ በሚጠይቀው መስዋዕትነት ሀገሩን በመተባበር ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል።

ወጣቶች ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊና ዘላቂ ግንባታ ያላቸውን ሚና መወጣት እንደሚኖርባቸው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ደን ልማት ዋና ዳይሬክተር ከበደ ይማም በበኩላቸው ኢትዮጵያ የአየር መዛባትን ለመከላከል የአረጓዴ አሻራ መርኃ ግብርን በመተግበር ላይ ነች ብለዋል።

ወጣቶችም የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ላይ ተሳትፎ በማድረግ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ዋና ዳይሬክተሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከነገ ጀምሮ ይሰጣል

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከነገ ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገለጸ፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና አሠጣጥን አስመልክቶ መግለጫ ሠጥቷል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሙላው አበበ የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁን ገልጸው ፈተናውም ከሰኔ 28 እስከ 30/2014 ዓ.ም ይሠጣል ብለዋል፡፡

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ፣ በማታ እና በግል የስምንተኛ ክፍል ትምህርታቸውን ለተከታተሉ ከ359 ሺሕ በላይ ተማሪዎች በ5 ሺሕ 395 ትምህርት ቤቶች ላይ ክልላዊ ፈተና እንደሚወስዱም ገልጸዋል።

ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ለማከናወን ከ10 ሺሕ በላይ መምህራን እንደሚሳተፉና የጸጥታ ችግር እንዳይከሰት የጸጥታ አካላት ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ተማሪዎች ፈተናውን በተረጋጋ እና ሥነምግባር በተሞላበት ሁኔታ እንዲፈተኑ መምህራን፣ ወላጆች እና የጸጥታ አካላት ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል።

በፈተና ወቅት ኩረጃ ሊያስከትል የሚችለውን ቅጣት በተዘጋጀው የፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ ላይ አብሮ የወረደ በመሆኑ ተማሪዎች ወደ ቅጣት እንዳይገቡ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

የወላጅ መምህር ኅብረት አባላት ፈተናው ታሽጎ ፈተና ጣቢያው ላይ መድረሱን እና በተማሪዎች ፊት መከፈቱን ማረጋገጥ እንደሚገባቸውና የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ማሳሰቡን የአሚኮ ዘገባ ያመለክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
መንግሥት ሀገራዊ ምክክሩ እንዲሳካ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነው - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) መንግሥት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራ እንዲሳካ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለፉት አራት ወራት ባከናወናቸው ሥራዎች ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መክሯል።

ሀገር እንድትረጋጋ እና ስርዓት ባለው መንገድ እንድትመራ እንዲሁም ሀገራዊ መግባባት እንዲፈጠር ትልቅ ትልም ይዞ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ ለመወጣት ጥሩ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

መንግሥት በኮሚሽኑ ሥራ ጣልቃ የመግባት ፍላት የለውም ያሉ ሲሆን እንደማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ተሳትፈን የውጤቱ ተካፋይ ለመሆን ነው ፍላጎታችን ብለዋል።

ስለሆነም ኮሚሽኑ የሚፈልገውን ድጋፍ ለማድረግ መንግሥት ቁርጠኛ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት ኮሚሽኑ ባለፉት አራት ወራት በእቅዱ መሠረት ተጨባጭ ሥራዎችን አከናውኗል፡፡

በዚህም ቀሪ ሥራዎችን እስከ መስከረም ድረስ በማጠናቀቅ የምክክር ሂደቱ በተያዘለት ጊዜ ለማካሄድ ዝግጅት ተጠናቋል ብለዋል።

በአስታርቃቸው ወልዴ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!
የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በዜጎች ላይ አደጋ እያደረሰ በመሸሽ ላይ ነው - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በዜጎች ላይ አደጋ እያደረሰ በመሸሽ ላይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕከት “የጸጥታ አካላት ከሚያደርሱበት ዱላ የፈረጠጠው የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በዜጎች ላይ አደጋ እያደረሰ በመሸሽ ላይ ነው” ብለዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ጭፍጨፋ ተፈጽሞባቸዋልም ነው ያሉት፡፡

“በዜጎቻችን ላይ በደረሰው መከራ እያዘንን ይሄንን አሸባሪ ቡድን እስከመጨረሻው ተከታትለን ከሕዝባችን ጋር እናስወግደዋለን” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!
የኦዲት ግኝቶች አበረታች የእርምት እርምጃዎች እንደተወሰደባቸው ኮሚቴው ገለጸ

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በፌዴራል ደረጃ የተከናወኑት አብዛኛዎቹ የኦዲት ግኝቶች አበረታች የእርምት እርምጃ እንደተወሰደባቸው ገለጸ።

ቋሚ ኮሚቴው የ2014 በጀት ዓመትን የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ፣ በበጀት ዓመቱ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤትን የኦዲት ግኝቶች መሠረት አድርጎ ባከናወናቸው የክትትል እና ድጋፍ ሥራዎች በኦዲት ሪፖርቶች የተመላከቱት ግኝቶች የተሻለ የእርምት እርምጃዎች እንደታየባቸው ገልጿል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ክርስቲያን ታደለ የተገኙ ውጤቶች እና በጎ ጅምሮች እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡

ከኦዲት ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በተደረጉት እንቅስቃሴዎች መንስዔም ከዚህ በፊት 14 በመቶ ተመላሽ ይደረግ የነበረው የገንዘብ ምጣኔ አሁን ወደ 40 በመቶ ከፍ ማለቱንም ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ውጤት በመነሳትም ተቋማት የአመራር፣ የክትትል እና ቁጥጥር ሥራቸውን እንዲያሻሽሉ በማድረግ የተሠሩ ሥራዎች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡

አያይዘውም ተቋማት በዋናነት የአሠራር ቅልጥፍናቸውን እና የአፈጻጸም ውጤታማነታቸውን በመጨመር ለዜጎች በታለመው ልክ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ተደራሽ ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡

ከተጠያቂነት አንጻር የተጀመሩ በጎ ጅምሮች ቢኖሩም ...
https://www.facebook.com/489211707826282/posts/pfbid028xbznWDphUx2ASmz7dBvLM5Bm2bCeHj952DGp4GCo3HwnLSXY4JrpHuuLgy63U1Zl/
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በአልጀሪያ 60ኛ ዓመት የነጻነት ቀን ክብረ በዓል ላይ ለመታደም አልጀርስ ገቡ

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በአልጀሪያ 60ኛ ዓመት የነጻነት ቀን ክብረ በዓል ላይ ለመገኘትና ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አልጀርስ ከተማ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቷ የአልጀሪያ አቻቸው ፕሬዚዳንት አብዱልመጅድ ተቡን በአገሪቱ 60ኛ ዓመት የነጻነት ቀን ክብረ በዓል ላይ እንዲታደሙ በላኩላቸው ግብዣ መሠረት ነው ወደ አልጀርስ ያቀኑት፡፡

በአልጀሪያ ቆይታቸውም ከፕሬዚዳንቱ ጋር በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የረጅም ጊዜ ግንኙነት በላቀ ሁኔታ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አልጀሪያ በፈረንጆቹ ከ1830 ጀምሮ የፈረንሣይ ቅኝት ግዛት የነበረች ሲሆን በፈረንጆች ሐምሌ 5 ቀን 1962 ከረጅም ዓመታት የትጥቅ ትግልና ከፍተኛ መስዋዕትነት በኋላ ነጻነቷን ለመቀናጀት መቻሏን የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት አስታውሷል።