AddisWalta - AW
45.3K subscribers
41.9K photos
204 videos
20 files
16.6K links
This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.

For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
Download Telegram
235 ሰዎችን የሚይዘው አሳንሰር (ሊፍት)
#ቴክኖ_ቅምሻ

በፊንላንድ ሊፍት ኩባንያ ኮን በ2022 በህንድ ሙምባይ በሚገኘው ጂዮ ወርልድ ሴንተር ህንፃ ውስጥ በዓለማችን የመጀመሪያ የሆነውን 235 ሰዎችን የሚይዘው አሳንሰር (ሊፍት) ገጥሞታል።

ይህ ትልቁ የመንገደኞች ሊፍት የስቲዲዮ አፓርታማ ያክላል የተባለ ሲሆን 16 ቶን የሚመዝንና በ9 የብረት ኬብሎች የተደገፈ ነው፡፡ አሳንሰሩ ሰዎችን ከማጓጓዝ በተጨማሪ ለሰርግና ለአርት ኤግዚብሽን ማሳያ እንዲሆን ተደርጎ የተሰራ ሲሆን 25.78 ስኩየር ሜትር ስፋት ያለውና ለተመልካች ውብ የሆነ እይታና የአትክልት ቦታ ያካተተ ነው።

አሳንሰሩ 18 ትላልቅ ፑሊዎች፣ 9 የብረት ኬብሎች እና በብረት ዓምዶች ላይ የተስተካከሉ ሀዲዶችን ባቀፈ አዲስ የፑሊ ጨረር ሲስተም ላይ የተሰራ ነው ተብሏል።

የዓለማችን ትልቁ የመንገደኞች አሳንሰር (ሊፍት) ልዩ ባለ አራት ፓነል የመስታወት በር፣ የመስታወት ግድግዳዎች ፓኖራሚክ እይታዎችን እና ክሪስታል-የተጣበበ ጣሪያን ያሳያል። በአምስት ፎቆች መካከል ብቻ የሚጓዝ ቢሆንም በሴኮንድ 1 ሜትር ፍጥነት በመጓዝ ሪከርድ ሰባሪው ሊፍትም ሆኗል።

ሊፍቱ ውስጥ ተጓዦች ሲደክማቸው አረፍ የሚሉበት 2 ምቹ ሶፋዎችም አሉት፡፡

የኮን ማኔጂንግ ዳይሬክተር ኢሚት ጎሳይን የዓለማችንን ትልቁን የህዝብ ማመላለሻ አሳንሰር (ሊፍት) ለደንበኞቻችን ችግር ፈች የሆነ ፕሮጀክት በመስራታችን ኩራት ይሰማናል ብለዋል፡፡
👇
https://shorturl.at/rT679
"የአፍሪካ ዋንጫን በ2029 ወይንም በ2031 ለማዘጋጀት እየሰራን ነው" የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ - አሁን 👇

https://shorturl.at/hOT48
አየር መንገዱ ወደ ካሜሩን ዱዋላ ከተማ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ወደ 11 አሳደገ

ሚያዝያ 17/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካሜሩን የንግድና የኢኮኖሚ ማዕከል ወደ ሆነችው ዱዋላ ከተማ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ወደ 11 ማሳደጉን ገለጸ።

በዚህም ከግንቦት 26/2016 ዓ.ም ጀምሮ በረራውን ወደ 11 ከፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት ወደ ከተማዋ 7 ጊዜ ሳምንታዊ በረራዎችን እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ውበት የሚያበቃበት ቀን የለውም የምትለው የ60 ዓመቷ ቁንጅና ተወዳዳሪ

የ60 ዓመቷ የሕግ ባለሙያ እና ጋዜጠኛ አሌጃንድራ ማሪሳ ሮድሪጉዝ በቅርቡ የሚስ ቦነስ አይረስን ውድድር በማሸነፍ ለሚስ አርጀንቲና የቁንጅና ውድድር ብቁ ሆናለች። ውበት የሚያበቃበት ቀን የለውም የምትለው አሌጃንድራ ማሪሳ የ2024 ሚስ ዩኒቨርስ አሸናፊ ለመሆንም ቆርጣ ተነስታለች።

እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር 1958 ጀምሮ በውድድሩ መሳተፍ የሚችሉት ከ18 እስከ 28 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች ብቻ ነበሩ፡፡ ባለፈው ዓመት ግን የዕድሜ ገደቡ ተነሳ። ይህ ለአርጀንቲናዊቷ የ60 ዓመት ቆንጆ “ሁኔታው ለእኔ ተመቸኝ” የሚያስብል ሆነና ተሳተፈች።

አርጀንቲናዊቷ ተወዳዳሪ ከበርካታ ወጣት ቆነጃጅት ሴቶች ጋር ተወዳድራ የሚስ ቦነስ አይረስን ማዕረግ ካሸነፈች በኋላ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አነጋጋሪ ሆናለች።

ውድድሩን ማሸነፏን ተከትሎ በመድረክ ላይ ንግግር ስታደርግ ለሁሉም ሴቶች ውበት እድሜ እንደሌለው እና እንቅፋቶችን ማፍረስ እንደምንችል ማሳየት እፈልጋለሁ ብላለች።
👇
https://shorturl.at/pxBGX
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

ሚያዝያ 17/2016 (አዲስ ዋልታ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 31ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
በዚህም፡-

1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የወጪ ንግድ የቀረጥ ማበረታቻ ሥርዓት አዋጅን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ለኢንደስትሪ ልማትና ኢንቨስትመንት የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ፣ በወጪ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች በማበረታታት ረገድ የታዩ ውስንነቶችን ለመቅረፍ እና የዘርፉን ተዋንያን የሚያበረታታ ሥርዓት በመዘርጋት ተወዳዳሪነት ማላቅ ይቻል ዘንድ ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም ረቂቅ ማሻሻያ አዋጁ ላይ ከተወያያ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የፌዴራል ህብረት ስራ ኮሚሽን ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚያስከፍለውን የአገልግሎት ክፍያ ለመወሰን በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ ኮሚሽኑ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ማስፋት፣ የአገልግሎቶቹን የጥራት ደረጃ ማሻሻል፣ ብሎም የተጠቃሚውን ማህበረሰብ አቅም ባገናዘበ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት ያወጣውን ወጪ በከፊል መሸፈን የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
👇👇
https://shorturl.at/rsJV1
“የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ አልዳባቢያን በመቀበሌ ደስታ ተሰምቶኛል። በውይይታችን ወቅት በቀጣናዊ የሰላም እና መረጋጋት፣ የኢኮኖሚ ትብብር፣ የሰው ኃይል ልውውጥ እና በሌሎች የጋራ ፍላጎት ጉዳዮችን አንስተናል።” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
አጓጊው ደሞ አዲስ መጪው እሁድ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ #በቀጥታ ስርጭት ለእናንተ ለተመልካቾቻችን ተወዳዳሪዎቹን ይዞላችሁ ይቀርባል።

በቀጥታ ስርጭትም ዳኞችና ተወዳዳሪዎች በተመልካቾች ድምፅ ይዳኛሉ።  በዕለቱም የተሰጣቸውን ኮድ በማስቀደም በ8970 SMS ድምጽ ይስጡ!

ያሬድ አበበ - B1
ታረቀኝ ረጃው - B3
እንግዳው አስፋው - B5
ኃይለኢየሱስ ታደገ - B6

#ደሞ_አዲስ #አዲስ_ዋልታ #music #idol

እሁድ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን 🎼
የገንዘብ ሚኒስትሩ ከአሜሪካ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

ሚያዝያ 17/2016 (አዲስ ዋልታ) የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ከተለያዩ የአሜሪካ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

የ2024 የዓለም ባንክ እና አይኤም ኤፍ ስብሰባዎች ጎን ለጎን በሚኒስትር አሕመድ ሺዴ የሚመራው ልዑክ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት አምባሳደር ሞሊ ፊ፣ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክል ሀመር እና የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ግምጃ ቤት ምክትል ፀሐፊ ጄይ ሻምባህ ጋር ተወያይቷል፡፡

ውይይቱ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ እንዲሁም የሀገሪቱን የማክሮ ኢኮኖሚ ማዕቀፍ ለማሻሻል በሚደረጉ ማሻሻያዎች ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተገልጿል።

ሁለቱ ወገኖች በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) እና የዓለም ባንክ በኩል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የሚያገግምበትን ሁኔታ ለመፍጠር፣ ሀገራዊ ትስስር እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ለማስፈን በሚያስፈልገው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ላይ መወያየታቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
ጃትሮፋ - ነዳጅ ለጋሹ ዛፍ

ጃትሮፋ - ነዳጅ ለጋሹ ዛፍ ቆላማ በሆኑ ጥቂት አካባቢዎች ላይ የሚበቅል የዛፍ አይነት ነው።

ጃትሮፋ ለአማራጭ የኃይል አቅርቦት የሚውል ሲሆን እንደ መደበኛው ዲዝል ከድፍድፍ ነዳጅ ዘይት የሚገኝ ሳይሆን ከእጽዋትና ከእንስሳት ተዋጽኦ (ዘይትና ሞራ) የሚመረት ለባዮ ዲዝል ምርት ግብዓት የሚሆን ነው።

በሀገራችን ኢትዮጵያ እንደ ወላይታ ሶዶ፣ ባቲ፣ መተማ፣ ኮምቦልቻ እና በመሳሰሉ ጥቂት ቆላማ አካባቢዎች ላይ ይገኛል።

በአንዳንድ የዓለም ሀገራት በገጠራማው አካባቢ የሚኖረው ማኅበረሰብ የዛፉን ፍሬ ለምግብ ማብሰያ እንደከሰል እና ለሳሙና መስሪያነት ይገለገሉበታል።

በወርልድ ቪዥን ስር የኤፍ ኤም ኤን አር (FMNR) አድቫይዘር የሆኑት ጌታቸው ታምሩ ከአዲስ ዋልታ ዲጂታል ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቆይታ የጃትሮፋ ዛፍን ጠቀሜታ አብራርተዋል።
👇👇
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid02fmetKkYfaMsbWcomMsQCXvrCSpTz5R8pyawfbTE6Bf8MM9G79qpY8eDToremBweUl
ጠ/ሚ ዐቢይ የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ድጋፍ ለኢትዮጵያ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው ገለጹ

ሚያዝያ 18/2016 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የሚሰጠው ድጋፍ ለኢትዮጵያ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ከሆኑት ማርክ ሱዝማን እና ቡድናቸው ጋር መወያታቸውን ጠቅሰው፤ በዚህም ደስታ እንደተሰማቸው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በግብርና፣ ጤና፣ በሥርዓተ-ምግብ፣ በአካታች የፋይናንስ ሥርዓት እና በሌሎች ዘርፎች የሚሰጠው ጠቃሚ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ዕድገት ከፍ ያለ አስተዋጽዖ እንዳለውም ጠቅሰዋል፡፡

ይህን ትብብር በማላቅ እና በአዳዲስ ዘርፎች በመተባበር እንሰራለን ሲሉም አረጋግጠዋል።
ቲክ ቶክ ይሸጣል?

የቻይናው የቲክ ቶክ እናት ካምፓኒ ባይትዳንስ ቲክ ቶክን ለመሸጥ ምንም እቅድ እንደሌለው አስታውቋል።

አሜሪካ ቲክቶክ እንዲሸጥ ወይም በአሜሪካ ውስጥ እንዲታገድ የሚያስገድድ ሕግ ማውጣቷን ተከትሎ የቲክ ቶክ እናት ካምፓኒ ቢዝነሱን የመሸጥ ፍላጎት እንደሌለው እየተናገረ ነው።

የአሜሪካን ውሳኔ ተከትሎ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ቲክ ቶክ “ሕገ-መንግስታዊ አይደለም” ያለውን ይህንን ሕግ እስከ ፍርድ ቤት ድረስ በመሄድ እንደሚቃወም ገልጿል።

ባይትዳንስ መግለጫውን ያወጣው “ቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪ” በተሰኘ ድረ-ገጽ ላይ ኩባንያው በአሜሪካ ውስጥ የቲክ ቶክ ኦፕሬሽን ከሚሰጠው ስልተ ቀመር (አልጎሪዝም) ውጭ ሊሸጥ የሚችለውን እየመረመረ ነበር የሚል መረጃ ከወጣ በኋላ ነው።

ኩባንያው ባይትዳንስ ቲክ ቶክን እንደሚሸጥ አድርገው የውጭ ሚዲያዎች የሚዘግቡት ከእውነት የራቀ፤ የውሸት ወሬ ነው ሲል ማጣጣሉን ቢቢሲ ዘግቧል።

የሽያጭ ወይም የእገዳ እርምጃውን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ረቡዕ እለት መፈረማቸው ይታወሳል…
ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ👇👇
https://waltainfo.com/am/%e1%89%b2%e1%8a%ad-%e1%89%b6%e1%8a%ad-%e1%8b%ad%e1%88%b8%e1%8c%a3%e1%88%8d/
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከጊፍት ሪል እስቴት ጋር በመሆን የ4 ሺሕ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ አስጀመረ

ሚያዝያ 19/2016 (አዲስ ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ በመንግስት እና በግል አጋርነት መርኃ ግብር ከጊፍት ሪል እስቴት ጋር የ4 ሺሕ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ አስጀመረ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው በመጀመሪያ ዙር ግንባታቸውን ያስጀመርናቸው 4 ሺሕ መኖሪያ ቤቶች ከ14 እስከ 22 ወለል ያላቸው ዘመናዊ ህንጻዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከንቲባዋ የግንባታ ተገቢ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ወደ ስራ ለገባው ጊፍት ሪል እስቴት በነዋሪዎቹ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችሉ አዳዲስ አማራጮችን ከህግና አሰራር ጋር በማጣጣም ተግባራዊ በማድረግ አዲስ አበባን ምቹ የስራና የመኖሪያ ከተማ ለማድረግ መስራታችንን ቀጥለናል ሲሉም አክለዋል።
ዛሬ በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ዌስትሃም ከሊቨርፑል ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

ሚያዝያ 19/2016 (አዲስ ዋልታ) ዛሬ በ35ኛው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ መርኃ ግብር ዌስትሃም ከሊቨርፑል ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

ዛሬ በሊጉ ሰባት ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን ከቀኑ 8፡30 ላይ ዌስትሃም ከሊቨርፑል ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ በጉጉት የሚጠበቅ ነው።

ሊቨርፑል ከዋንጫው ፉክክር ላለመራቅና በኤቨርተን ከደረሰበት አስደንጋጭ ሽንፈት ለመውጣት ከባድ ፉክክር እንደሚያደርግም ይጠበቃል።

በሊጉ ውጤት እየራቀ የመጣው ዌስትሃምም ከገጠመው ቀውስ ለመውጣት ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርግ ይገመታል።

ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ፉልሃም ከክሪስታል ፓላስ፣ ማንችስተር ይናይትድ ከበርንለይ፣ ኒውካስትል ከሽፊልድ ዩናይትድ እና ዎልቭስ ከሉተን ታውን የሚደረጉ የዕለቱ ጨዋታዎች ናቸው።

በተጨማሪም በዕለቱ ኤቨርተን ከብሬንትፈርድ 1 ሰዓት ከ30 ላይ እንዲሁም አስቶን ቪላ ከቸልሲ ምሽት 4 ሰዓት ላይ የሚደረጉ ተጠባቂ ጨዋታዎች ናቸው።

ሊጉን አርሰናል 34 ጨዋታዎችን አድርጎ በ77 ነጥቦች ሲመራ ማንችስተር ሲቲ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ76 ነጥቦች በሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሊቨርፑል በ74 ነጥቦች ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
አጓጊው ደሞ አዲስ ነገ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ #በቀጥታ ስርጭት ለእናንተ ለተመልካቾቻችን ተወዳዳሪዎቹን ይዞላችሁ ይቀርባል።

በቀጥታ ስርጭትም ዳኞችና ተወዳዳሪዎች በተመልካቾች ድምፅ ይዳኛሉ።  በዕለቱም የተሰጣቸውን ኮድ በማስቀደም በ8970 SMS ድምጽ ይስጡ!

ያሬድ አበበ - B1
ታረቀኝ ረጃው - B3
እንግዳው አስፋው - B5
ኃይለኢየሱስ ታደገ - B6

#ደሞ_አዲስ #አዲስ_ዋልታ #music #idol

ነገ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን 🎼
አትሌት መዲና ኢሳ የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር አሸነፈች

ሚያዝያ 19/2016 (አዲስ ዋልታ) የአዲዳስ ኩባንያ ባዘጋጀው አዲዜሮ የ5 ኪሎ ሜትር ከ20 ዓመት በታች ውድድር አትሌት መዲና ኢሳ የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር አሸነፈች፡፡

የ19 ዓመቷ አትሌት መዲና ርቀቱን በ14 ደቂቃ ከ38 ሰከንድ በማጠናቀቅ የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር ውድድሩን አሸንፋለች፡፡

በውድድሩ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት መልክናት ውዱ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ፎቲየን ተስፋይ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡

በወንዶች ዮሚፍ ቀጀልቻ በ13 ደቂቃ በመግባት ሲያሸንፍ ይሁኔ አዲሱ በ5 ሴኮንዶች ዘግይቶ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁን ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡
በቻይና ሻንጋይ በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸነፉ

ሚያዝያ 19/2016 (አዲስ ዋልታ) በቻይና ሻንጋይ በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ ውድድር አትሌት ሰሎሞን ባረጋ በ5 ሺሕ ሜትር ውድድር አሸናፊ ሆኗል።

አትሌቱ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 12 ደቂቃ ከ55 ሰኮንድ ከ68 ማይክሮ ሰኮንድ መውሰዱን የዓለም አቲሌትክስ መረጃ አመላክቷል፡፡

በሌላ በኩል በሴቶች የ5 ሺሕ ሜትር የቻይና ሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ 2024 ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ አራተኛ ደረጃ በመውጣት ውድድሩን በበላይነት አጠናቅቀዋል፡፡

በዚህም ውድድሩን በአንደኝነት ያጠናቀቀችው አትሌት መቅደስ ዓለምሸት ርቀቱን በ14 ደቂቃ ከ36 ሰኮንድ በሆነ ጊዜ በመግባት አሸንፋለች፡፡

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት አያል ዳኛቸው በ16 ማይክሮ ሰከንድ ብቻ ተቀድማ ሁለተኛ ደረጃን ስትይዝ ለተሰንበት ግደይ ሦስተኛ ደረጃ እንዲሁም ውብርስት አስቻለ አራተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸውን የዋች አቲሌትክስ መረጃ ያመላክታል፡፡
ሊቨርፑል ከዌስትሃም ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

ሚያዝያ 19/2016 (አዲስ ዋልታ) በ35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ መርኃ ግብር ዌስትሃም ዩናይትድ ከሊቨርፑል ያደረጉት ጨዋታ በ2 አቻ ውጤት ተጠናቀቀ፡፡

ዌስትሃሞች ከእረፍት በፊት ቀዳሚ የሚያደርጋቸውን ጎል በጃሬድ ቦውን አማካኝነት 43ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥረው ነበር።

ከእረፍት መልስ ሊቨርፑሎች በአንድሪው ሮበርትሰን የ48ኛ ደቂቃ ጎል አቻ እንዲሁም 65ኛው ደቂቃ ላይ አልፎንስ አሪኦላ በራሱ ላይ ባስቆጠረው ግብ መምራት ችለው የነበረ ሲሆን ሚካኤል አንቶኒዮ በ77ኛው ደቂቃ ለዌስትሃም አስቆጥሮ ጨዋታው በአቻ ውጤት ሊጠናቀቅ ችሏል።

ሊቨርፑሎቹ የኳስ ቁጥጥር እና የግብ ሙከራ የበላይነት ቢኖራቸውም ውጤቱን መቀልበስ ባለመቻላቸው ከዋንጫ ተፎካካሪነታቸው እየራቁ ይገኛሉ።