AddisWalta - AW
45.3K subscribers
41.9K photos
204 videos
20 files
16.6K links
This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.

For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
Download Telegram
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለ #ጽዱ_ኢትዮጵያ የዲጂታል ቴሌቶን ሰጡ

ሚያዚያ 20/2016 (አዲስ ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአንድ ወር ደሞዛቸውን አስተዋፅኦ በማድረግ “ፅዱ ኢትዮጵያ” የዲጂታል ቴሌቶን ላይ መሳታፋቸውን አስታወቁ፡፡

ከከንቲባዋ ባሻገር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮችም የ"ጽዱ ጎዳና -ኑሮ በጤና" ንቅናቄን ተቀላቅለዋል፡፡

በዚህም ጥሪውን በፍጥነት ሰለተቀላቀላቹ በከተማ አስተዳደር ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

ያልተቀላቀሉ አመራሮችም ካምፔኑን እንዲቀላቀሉ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በተጨማሪም ለአላማው መሳካት ሁሉም ሰው ያገባኛል በሚል በንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248 የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄን እንዲቀላቀል ጥሪ አቅርበዋል::
የፊታችን እሁድ ግንቦት 4/2016 ዓ.ም ለ#ጽዱ_ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 50 ሚሊዮን ብር የማሰባሰብ ዲጂታል ቴሌቶን ይቀላቀሉ

#ጽዱ_ኢትዮጵያ
#CleanEthiopia
አዋሽ ባንክ ለ#ጽዱ_ኢትዮጵያ 10 ሚሊዮን ብር በማበርከት ንቅናቄውን ተቀላቀለ

ግንቦት 5/2016 (አዲስ ዋልታ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የሆነውን የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄ በርካታ ተቋማት እየተቀላቀሉ ሲሆን አዋሽ ባንክ 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በማድረግ አጋርነቱን አሳይቷል።

#ጽዱ_ኢትዮጵያ