AddisWalta - AW
45.4K subscribers
42.2K photos
208 videos
20 files
16.7K links
This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.

For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
Download Telegram
የፊታችን እሁድ ግንቦት 4/2016 ዓ.ም ለ#ጽዱ_ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 50 ሚሊዮን ብር የማሰባሰብ ዲጂታል ቴሌቶን ይቀላቀሉ

#ጽዱ_ኢትዮጵያ
#CleanEthiopia
ዛሬ ለጽዱ ኢትዮጵያ 50 ሚሊየን ብር በአንድ ጀምበር ለማሰባሰብ የዲጂታል ቴሌቶን ይካሄዳል

ግንቦት 4/2016 (አዲስ ዋልታ) በዛሬው ዕለት ለጽዱ ኢትዮጵያ 50 ሚሊየን ብር በአንድ ጀምበር ለማሰባሰብ የዲጂታል ቴሌቶን ይካሄዳል።

በጋራ ትርጉም ያለው በጎ ተፅዕኖ እንዲፈጠር፤ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ግንቦት 4 የሚከናወነውን የ#ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶችን በመገንባት ክብርን ጠብቆ የመፀዳዳት ባህልን ለማዳበር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ይፋ የሆነውን የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄ በርካቶች በመቀላቀል ድጋፍ እያደረጉ ይገኛል።

በዚህ ንቅናቄ እስካሁን ድረስ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ባለሃብቶች፣ የተለያዩ ተቋማት እንዲሁም በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ዜጎች አቅማቸው የፈቀደውን ገንዘብ በመደገፍ ለዓላማው መሳካት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

በርካቶች እየተቀላቀሉት ያለውን ይህን ንቅናቄ ዜጎች እንዲሳተፉ ለማድረግም ዛሬ በአንድ ጀምበር 50 ሚሊዮን ብር ዲጂታል ቴሌቶን ተሰናድቷል፡፡

ኢትዮጵያውያን በሙሉ በዛሬው ዕለት በሚካሄደው ለ #ጽዱኢትዮጵያ ዲጂታል ቴሌቶን ድጋፋቸውን በማበርከት እነዚህን ስኬቶች እንዲደግሙ ተጋብዘዋል።

ለ#ጽዱኢትዮጵያ
For a #CleanEthiopia
በንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248፣ በብሔራዊ ባንክ የዶላር አካውንት 0101211300016 እና በስዊፍት ኮድ NBETETAA የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄን ይቀላቀሉ።
50 ሚሊዮን ለአንድ ሰው ሸክሙ፣ ለ50,000 ሰው ግን ጌጡ።
#ጽዱኢትዮጵያ
#CleanEthiopia