ውሉደ ብርሀን ሰ/ት/ቤ/ት🙏(ጫንጮ)
766 subscribers
84 photos
4 files
98 links
ሰንበት ትምህርት ቤት የመልካም ወጣት የመልካም ትውልድ መፍለቂያ ናት! ትውልድን ለበጎ ነገር የምታበቃ ናት፡፡


የጫንጮ ከተማ ደ/ብ/ቅ/እግዚአብሔር አብ እና ደ/ሲ/ቅ/ ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ ው/ብ/ሰ/ት/ቤት ቻናል
ለሀሳብ እና አስታየት @weldebirhanbot @ty1921 ይጠቀሙ

ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ መልካም ነው፡፡
Download Telegram
💥 እግዚአብሔር ድንቅ ሥም 💥

እግዚ-አብ-ሔር ማለት የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስን ስም የያዘ ቅዱስ ሥም ነው።

#እግዚ

አግአዘ - ነፃ አወጣ ነፃ ፍቃድ ሰጠ .. አግአዞ ለአዳም- አዳምን ከዲያቢሎስ ነፃ አወጣው

እግዚኦ - ጌታ ሆይ ነፃ አውጣን

ግእዝ - ነፃ መውጣት

እግዚእነ እግዚ-ኦ : እግዚ-አብ-ሔር:

እግዚ - አግአዚ ነፃ አውጪ አጋእዝት አጋዚያን "ጌታ /እግዚአብሔር አብ/ ጌታዬን / ኢየሱስ ክርስቶስን/ ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ በቀኜ ተቀመጥ አለው። መዝ.109፥10 - " እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።" (ዕብ 2:14-15)

ነጻ ያወጣን ኢየሱስ / ወልድ/ እግዚ ነው።


#አብ

አብ- አባ: አባት ዘላለማዊ አባት የሆነ እኛን ፈጥሮ ፈጣሪነቱን የገለፀና ቸርነቱን የአሣየን ነውና አባትነቱ ያለ የነበረ የሚኖር ዘላለማዊ ህይወት ሠጭ ነው "ሁላችን አንድ አባት የአለን አይደለምን? አንድ አምላክ የፈጠረን አይደለምን? " ሚል. 2፥10

#ሔር

ሔረ - ለገሰ:ሰጠ: ቸር ሆነ: ቅን ሆነ
ሔር -ቸር ለጋስ ደግ ቅን ሰጭ
ሒሩት- ቸርነት ደግነት ለጋሽነት ቅንንነት

ሔር-ቸር "ሃሌ ሉያ ቸር ነውና ምህረቱ ለዘለአለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑት" መዝ.105:1
"እግዚአብሔር ቸር እንደሆነ ቅመሱ እዩምበእርሱ የሚታመን ምስጉን ነው" መዝ.33፥8 " ከአንዱ እግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም" ማር.10፥18 ሉቃ. 18፥18

የእግዚአብሔር ፍቅሩ ይደርብን።

#ማጠቃለያ
እግዚ=ጌታ( ለወልድ)
አብ= አባት(ለአብ )
ሔር= ቸር (ለመንፈስ ቅዱስ )
@yeberhanljoche
@yeberhanljoche
@yeberhanljoche
✞በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሃዱ አምላክ አሜን✞
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ምስጢረ_ስላሴ_በጥቂቱ
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
እኛ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች የእግዚአብሔር አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው፤ ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በአንድነትና በሦስትነት የሚመሰገን አንድ ሕያው አምላክ በሆነው በእግዚአብሔር እናምናለን፡፡ #አንድ_ሲሆን_ሦስት_ሦስት_ሲሆን_አንድ_በአካል_ሦስት_ሲሆን_በመለኮት_በአንድ_አምላክ_በሆነው_በልዑል_እግዚአብሔር ብቻ ነው የምናምን፡፡ ይህ ምስጢር ስጋን በለበሰ ህሊናችን ተመራምሮ ማወቅ አይቻልም በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ካልሆነ በስተቀር፡፡ ለዛም ነው ቤተ ክርስቲያናችን አምስቱ አዕማደ ምስጢራትን ስታስተምር በመጀመሪያ ምስጢረ ስላሴን መማር እንዳለብን ያስቀመጠችልን፡፡ ምስጢር ማለት፦ እጅግ ጥልቅ፣ የተሰወረ፣ የረቀቀ፤ ከመሆኑ የተነሳ #ምስጢር ይባላል፡፡ #ስላሴ ማለት ደግሞ "ሰለሠ" ወይም ሦስት አደረገ ማለት ሲሆን ትርጉሙም፦ ሦስትነት ማለት ነው፡፡
✞✞✞
#የስላሴ_አንድነትና_ሦስትነት
✞✞✞
☞✞ #የስላሴ_አንድነት ፦ በአገዛዝ፣ በስልጣን፣ ይህን አለም በመፍጠርና በማሳለፍ፣ በህልውና፣ በመለኮት፣ በልብ፣ በቃል፣ በእስትንፋስ፤ በእነዚህ ሁሉ የመለኮት ባህርይ #አንድ ነው፡፡
#የእግዚአብሔር_ሦስትነት_ስንል፦እግዚአብሔር የማይለያይና የማይቀላቀል ፍጹም የሆነ ሦስትነት አለው ማለታችን ነው። የእግዚአብሔር ሦስትነትም፦ በስም፣ በግብር፣ በአካል ነው።
☞✞ እግዚአብሔር #በስም ሦስት ነው ስንል ሦስት የተለያዩ ስሞች አሉት ማለታችን ነው። እነዚህም፦ #አብ #ወልድ #መንፈስ_ቅዱስ የሚባሉት ሲሆኑ እርስ በርሳቸው አይወራረሱም፤ አንዱ በሌላው ስም አይጠራም። "ዘፍ፡1፥2 ፣ ምሳ፡30፥4" ።
☞✞ እግዚአብሔር #በግብር ሦስት ነው ስንል፤ ሦስት የተለያዩ የአካል ሥራዎች አሉት ማለት ነው። እነሱም፦
መውለድና ማስረጽ =የአብ፤
መወለድ=የወልድ፤ መስረጽ =የመንፈስ ቅዱስ፤ የሚሉት ሲሆኑ የአካል ግብር ይባላሉ። "መዝ፡2፥7"
☞✞ እግዚአብሔር በአካል ሦስት ነው ማለት ደግሞ
#ለአብ፦ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው።
#ለወልድ ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ።
#ለመንፈስ_ቅዱስ ፤ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ማለታችን ነው።
☞✞ የሦስቱ የእግዚአብሔር ስሞች ትርጉም፦
#አብ፦ ማለት አባት ማለት ሲሆን የሚወልድ፤የሚያሰርጽ ወይም የሚያስገኝ ያለ እናት ወልድን የወለደ፤ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸ ነው።
#ወልድ፦ ልጅ ማለት ሲሆን የሚወለድ ወይም ያለ እናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድህረ ዓለም የተወለደ ነው። "መዝ፡2፥7" #መንፈስ_ቅዱስ፦ ረቂቅ፣ ልዩ፣ ንፁህ ከፍጡራን መናፍስት ሁሉ የተለየ ማለት ነው። "እዮ፡26፥13"
✞በመጽሐፍ_ቅዱስም ከበቂ በላይ ሁኖ ተገልፆልናል፡፡
ዘፍ፡1፥26 ፣ ዘፍ፡11፥7 ፣ ኢሳ፡6፥1-3 ፣ ኢሳ፡48፥16 ፣ ማቴ፡3፥16 ፣ ማቴ፡28፥19 ሉቃ፡1፥35 ፣ ዮሐ፡14፥25 ፣ ማቴ፡21፥18 ፣ 1ኛ ቆሮ፡12፥3 ፣ 2ኛ ቆሮ፡13፥14 ፣ ዘፍ፡3፥22 ፣ ማር፡10፥6 ፣ ማር፡10፥18 ፣ ዘፍ፡1፥3 ፣ ዘፅ፡5፥1 ፣ ዘፅ፡7፥17 ፣ ኢያ፡3፥17 ፣ ሐዋ፡1፥23 ወዘተ.... ከዚህም በላይ ስለአንድነትና ሦስትነታቸው እናገኛለን፡፡


🌾✞✞✞ #​​ቅድስት_ሥላሴ ✞✞✞🌾

#ሥላሴን_ቅድስት_ሥላሴ_እያልን_የመጥራታችን_ምስጢር_ምንድን_ነው

💠 አንዲት ሴት ወይም እናት ልጆቿን አልወለደችም ተብላ አትጠረጠርም፤ ሥላሴም ይህንን ዓለም ፈጥረዋል እናም አልፈጠሩም ተብለው አይጠራጠሩም።

💠 አንዲት ሴት በባሕሪይዋ ልጅን ታስገኛለች፤ ሥላሴም ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተው ስለፈጠሩት በሴት አንጻር ቅድስት ተብለው ይጠራሉ።

💠 አንድም ሴት አዛኝ ናት፤ ለታናሹም ይሁን ለታላቁ ትራራለች ሥላሴም እንደዚሁ ለፍጥረት ሁሉ ያዝናሉ፥ ይራራሉ፥ ምህረት ይሰጣሉ።
👉 ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ ይላል። ምህረታችሁ ከልክም በላይ የበዛ በሴት አንቀጽ ቅድስት ተብላችሁ የተጠራችሁ ሥላሴ በማለት ያመሰጥራል። ስለዚህ ቅድስት ለምን ተባሉ ቢባል በረከታቸው፥ ርህራሄያቸውና፥ ይቅር ባይነታቸው መሆኑን ማወቅ አለብን።

💠 አንድም ሴት ልጇ ቢታመምባት አትወድም፤ ሥላሴም አንድም ልጅ በዲያብሎስ እጅ ተይዞ በኃጢአት እንዲታመሙ አይወዱም፥ አይፈቅዱም በመሆኑም ቅድስት ይባላሉ።

💠 አንድም ሴት ልጅ የልጇን ነውር አትጠየፍም ልጄ ቆሽሿል፥ ተበላሽቷል ብላ ፊቷን አታዞርም። ሥላሴም የሰውን በኃጢአት መቆሸሽ ሳይፀየፉ በቸርነታቸው ጎብኝተዉ ለንስሐ ያደርሱታል።

💠 ይህንን የፅድቅ አየር የምንምገው ያማረውንም ብርሃን የለበስነው ስለ ፅድቃችን ሳይሆን በሥላሴ ቸርነት ነውና ስለዚህም ሥላሴን በሴት አንቀፅ ቅድስት እንላቸዋለን።

💠 አንድም ሴት ልጆቿን ፈጭታና ጋግራ ትመግባቸዋለች ሥላሴም እንደዛው ናቸው። በዝናብ አብቅለው በፀሐይ አብሥልው ፍጥረታትን ሁሉ ይመግባሉ። ስለዚህ ሥላሴ እንደ እናት ሁሉንም ይመግባሉና በሴት አንቀጽ ቅድስት ይባላሉ።

የእግዚአብሔር አብ በረከት፣
የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣
የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት፣
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ልዑል ✞
@yeberhanljoche
@yeberhanljoche
@yeberhanljoche
💥 እግዚአብሔር ድንቅ ሥም 💥

እግዚ-አብ-ሔር ማለት የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስን ስም የያዘ ቅዱስ ሥም ነው።

#እግዚ

አግአዘ - ነፃ አወጣ ነፃ ፍቃድ ሰጠ .. አግአዞ ለአዳም- አዳምን ከዲያቢሎስ ነፃ አወጣው

እግዚኦ - ጌታ ሆይ ነፃ አውጣን

ግእዝ - ነፃ መውጣት

እግዚእነ እግዚ-ኦ : እግዚ-አብ-ሔር:

እግዚ - አግአዚ ነፃ አውጪ አጋእዝት አጋዚያን "ጌታ /እግዚአብሔር አብ/ ጌታዬን / ኢየሱስ ክርስቶስን/ ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ በቀኜ ተቀመጥ አለው። መዝ.109፥10 - " እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።" (ዕብ 2:14-15)

ነጻ ያወጣን ኢየሱስ / ወልድ/ እግዚ ነው።


#አብ

አብ- አባ: አባት ዘላለማዊ አባት የሆነ እኛን ፈጥሮ ፈጣሪነቱን የገለፀና ቸርነቱን የአሣየን ነውና አባትነቱ ያለ የነበረ የሚኖር ዘላለማዊ ህይወት ሠጭ ነው "ሁላችን አንድ አባት የአለን አይደለምን? አንድ አምላክ የፈጠረን አይደለምን? " ሚል. 2፥10

#ሔር

ሔረ - ለገሰ:ሰጠ: ቸር ሆነ: ቅን ሆነ
ሔር -ቸር ለጋስ ደግ ቅን ሰጭ
ሒሩት- ቸርነት ደግነት ለጋሽነት ቅንንነት

ሔር-ቸር "ሃሌ ሉያ ቸር ነውና ምህረቱ ለዘለአለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑት" መዝ.105:1
"እግዚአብሔር ቸር እንደሆነ ቅመሱ እዩምበእርሱ የሚታመን ምስጉን ነው" መዝ.33፥8 " ከአንዱ እግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም" ማር.10፥18 ሉቃ. 18፥18

የእግዚአብሔር ፍቅሩ ይደርብን።

#ማጠቃለያ
እግዚ=ጌታ( ለወልድ)
አብ= አባት(ለአብ )
ሔር= ቸር (ለመንፈስ ቅዱስ )
@yeberhanljoche
@yeberhanljoche
@yeberhanljoche