ዳኒሽ (HIKMA)
121 subscribers
204 photos
26 videos
1 file
94 links
አሰላሙ አለይኩም🖐🤝
የተወደዳችሁ የቻናላችን ተከታታዮች በአሏህ ፍቃድ እናንተን እያዝናናን ኢስላማዊ እውቀቶችን እና ጠቃሚ ምክሮችን እናስተላልፋለን🙏

ለማንኛውም አስተያየት እና መልእክት💌
👇
@A2yshd

@ethiodanishbot
Join ለማድረግ
Download Telegram
Forwarded from ዳኒሽ (HIKMA) (Servant of Allah)
🤲🤲ዱዐ🤲🤲

🤲ዱዐ:- ሁሉም ፍጡር ከአላህ ከጃይ ነው። አላህ ዘንድ ያለው ያስፈልገዋል። እርሱ(አላህ) ደግሞ ከፍጡራኑ የተብቃቃና ሀብታም ነው። አላህ የሚለምነውን ይወዳል። እሱን በመለመን ችክ ባዮቹንም ባሮች ይወዳል። ለዚህም ነው ሶሀቦች ለትንሽ ነገር ቢሆን እንኳን አላህን ከመለመን የማይቦዝኑት።

የዱዐ ደረጃ፡- ዱዐ አላህ ዘንድ ትልቅ ደረጃ አለው፤ የአላህን ቀደር ሊመልስ/ሊቋቋም/ ይችላል። ዱዐ ከእንቅፋቶች ከፀዳና ቅድመ ሁኔታው ከተሟላ ተቀባይነት አለው። አላህ(ሱ.ወ) እንዲህ ይላል «ጌታችሁም አለ ለምኑኝ እቀበላኋለው፤እነዛ እኔን ከመገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ጀሀነም ይገባሉ» 46፡60
«ባሮቼ በጠየቁህ ጊዜ እኔ ቅርብ ነኝ፣ የለማኝን ፀሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ…»02

ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ «ዱዐ እርሱ እራሱ አምልኮ ነው»
ቲርሚዚና ሌሎችም ዘግበውታል

በሌላ ቦታ ነቢዩ ሙሀመድ(ሰ.ዐ.ወ) በዘገቡት ሀዲስ «ዱዐ የኢባዳ መቅኒ ነው» ብለዋል።

ዱዐ በኢስላም ቁርዐንን ከማንበብና ከዚክር በመቀጠል በላጭ የሆነ ኢባዳ ነው።

🤲የዱዐ አይነቶች፡- ሁለት ሲሆኑ አምልኮታዊ(ሶላት፣ፆም…) ዱዐና የልመና(ጥያቄ) ዱዐ ይባላሉ። ለዱዐ ተቀባይነት የሚረዱ መስፈርቶች፡-
1.ግልፅ ምክንያቶች፡- ሰደቃ፣ውዱዕ፣ ሶላት፣ ወደ ቂብላ መዞር እጅን ማንሳት፣ አላህን በተገቢው ሁኔታ ማወደስ፣ በነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሶለዋት ማውረድ፣ ወንጀሉን ማመን፣ የአላህ ስሞችን እያነሱ መለመን… የመሳሰሉትን መጠቀም ናቸው።
2. ድብቅ ምክንያቶች፡- እውነተኛ ተውበትን ማስቀደም፣ በበደል የወሰዱትን ነገር መመለስ፣ ምግብን መጠጥን መኖሪያን ማሳመርና ከሀላል ማድረግ፣ ወንጀልና ከአጠራጣሪ ነገሮች መራቅ፣ ዱዐን ከልብ ማድረግ፣ በአላህ መተማመን፣ የተስፋ ስሜት ማዳበር፣ ወደ አላህ መጠጋት፣ ራስን ማስተናነስ፣ ችክማለት፣ ወደ አላህ መጠጋት፣ ሁሉን ነገር ወደርሱ ማስጠጋትና ከሌላው ተስፋ መቁረጥ ናቸው።

የዱዐ ወቅቶች፡- በለሊቱ መጨረሻ ላይ፣ በአዛንና በኢቃማ መካከል፣ ከውዱዕ በኋላ፣ በሱጁድ ውስጥ፣ ከሶላት ማሰላመት በፊት፣ ከሶላቶች በኋላ፣ በቁርዐን ማኽተሚያ ወቅት፣ ዶሮ ሲጮህ፣ ሙሳፊር ሰው፣ የተቸገረ ሰው፣ የአባት ዱዐ ለልጅ፣ ሙስሊም ወንድሙ በርቀት የሚያደርግለት፣ ከጠላት ጋር ሲገናኙ፣ በጁሙዐ ኩጥባ ሶላቱ እስኪያልቅና ከአሱር በኋላ፣ በረመዳን
በፊጥርና በሱሁር ወቅት፣ ለይለተል ቀድር፣ የአረፋ ቀን ናቸው።

🖼የዱዐ ቦታዎች፡- የዱዐ ቦታዎችን በተመለከተ በሁሉም መስጂዶች በተለይ ከካዕባ አጠገብ፣ መቃሙ ኢብራሂም ዘንድ፣ ሶፋና መርዋ ላይ፣ በሐጅ ጊዜ (በዐረፋ፣ በሙዝደሊፋና፣ በሚና) ላይ፣ ዘምዘምን በሚጠጡበት ጊዜ ናቸው።

#ዱዐን_ተቀባይነት_የሚያሳጡ_ነገሮች፡- በዱዐው ከአላህ ጋር ሌሎችን መለመን(ሽርክ)፣ በልመናው ውስጥ ዝርዝር ነገሮችን መጥቀስ፣ በራሱ ላይ ወይም በሌላው ላይ ዱዐ ማድረግ (በግፍ)፣ ለወንጀልና ዝምድናን ለመቁረጥ ዱዐ ማድረግ፣ ከፈለክ አድርግልኝ ስትፈልግ ማረኝ ማለት፣ መሰላቸት፣ በተዘናጋ ልብ ዱዐ ማድረግ፣ አላህ ፊት ተገቢውን ስርዐት አለመያዝ፣ በነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሶለዋት አለማውረድ፣ በግድ በግጥም መልክ ለማድረግ መልፋት፣ ድምፅን ከመጠን በላይ ማጉላት… የመሳሰሉት ናቸው።

ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) ቲርሚዚይ በዘገቡት ሀዲስ እንዲህ ብለዋል« ማንም ሙስሊም በወንጀልና ዝምድናን በመቁረጥ ባልተቀላቀለበት ዱዐ ካደረገ ከሶስት ነገሮች አንዱ ይሰጠዋል- የለመነውን ነገር በቀጥታ፣ ወይም ወደ አኺራ ተላልፎ ሊቀመጥለት፣ ወይም እንደ አቅሟ ሊያገኘው የነበረውን ክፉ ነገር በመከላከል ነው»

#ከዱዐ_መኩራራት፡- አላህ በርሱ ላይ የሚኩራሩትንና ተብቃቂ ለመሆን የሚሹትን በተለያዩ ቦታዎች ያስጠነቅቃል።
«…እነዛ እኔን ከመገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ጀሀነም ይገባሉ» 46፡60

ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) ኢብኑ ማጃህ በዘገቡት ሀዲስ «አላህ ልመናውን የተወን ሰው ይቆጣበታል» ብለዋል።

#በዱዐ_ድንበር_ማለፍ፡- በመጨረሻው ዘመን ሰዎች በዱዐ ላይ ድንበር እንደሚያልፉ ነቢዩ አስጠንቅቀዋል ይኸውም በአሁን ዘመን በመታየት ላይ ይገኛል።

ለምሳሌ፡- ድምፅን ከፍ አድርጎ መለመን፣ በጋራ ዱዐ ማድረግ፣ ቦታና ጊዜውን መወሰን… የመሳሰሉት ይገኙበታል ከሁሉ የከፋው ደግሞ ከአላህ ውጪ ያሉ አካለትን መለመን ሲሆን ነቢዩ እንዲህ ሲሉ ያስጠነቅቃሉ፡- «መለመን ስትፈልግ አላህን ብቻ ለምን፣ እርዳታ ብትፈልግ በአላህ ብቻ ተረዳ» ቲርሚዚ ዘግበውታል

አላህን በስርዐት ከሚገዙት ዱዐቸውንም ከሚቀበላቸው ባሮች ያድርገን።
አላሁመ አሚን!
#ተጨማሪ_ኢስላማዊ_እውቀቶችን_ከፈለጉ
@ethio_danish
@ethio_danish
@ethio_danish
@ethio_danish
☝️የአሏህ መልዕክተኛ ረሱል 【ሰ ዐ ወ】 እንዲህ ብለዋል ።

« እናንተ በምላሳችሁ አምናችሁ ኢማናችሁ ወደ ልባችሁ ያልገባ ሰዎች! ሙስሊሞችን አትሙ ፤ ነውራቸውን አታውሩ ፥ አትከታተሉም። የሙስሊም ወንድሙን ነውር ተከታትሎ ያወጣበት ፥ አላህ የእሱንም ነውር ያጋልጥበታል ፥ ከቤቱ ወስጥ ( ተደብቆ ) የሰራውን እንኳን ሳይቀር ። »
አቡ ዳውድ እንደዘገቡት
@ethio_danish
@ethio_danish
@ethio_danish
💵 ነጋዴው ሆይ ጠንቀቅ በል!💵
https://t.me/Ethio_Danish
ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-

“ነጋዴዎች አመፀኞች ናቸው
ሶሐቦች፡- የአላህ መልእክተኛ ሆይ “አላህ ንግድን ፈቅዶ የለ እንዴ?" ሲሉ ጠየቁ።
https://t.me/Ethio_Danish
ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ መለሱ፡-
“እንዴታ! ግን እነሱ
👉 ያወራሉ፡፡ ሲያወሩ ይዋሻሉ
👉 ይምላሉ፡፡ ሲምሉ ይወነጅላሉ"
አንተ ዘንድ ሌላ ሰው ሚፈልገው
ነገሮች ይኖራል‥
ሌላው ሰው ጋር
አንተ ምትፈልጋቸው ነገሮች ይኖራሉ
ማንም ሙሉ የሆነ ሰው የለም
አንዳችን ሌላኛውን ሙሉ ያደርጋልና
ሁሉም ከጌታችን የተሰጠን ነው
ስለሁሉም ረበል ዐለሚንን እናመስግነው!!


"الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ"
"ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው፤"
(ሱረቱል አል ፋቲሀ:2)

@ethio_danish
#አመስግን!!
#አልሃምዱሊላህ_በል

በኩላሊት እጥበት ጊዜ ደም ከሰውነታችን በቀዩ ቱቦ ይወጣና በ Dialysis Machine አልፎ በሰማያዊ ቱቦ ተመልሶ ወደ ሰውነታችን ይገባል።

እንዲህ እያለ ለ 4 ሰዓታት ይቆያል፤ ይህ Dialysis በሳምንት 3 ጊዜ በወር 12 ጊዜ ይደረጋል።

በአጠቃላይ በወር ለ 48 ሰዓታት ታማሚው ሳይንቀሳቀስ Dialysis ያደርጋል።

እኔ እና እናንተ ግን በቀን 36 ጊዜ ኩላሊታችን ራሱን ያጥባል፤ ያውም ያለ ምንም ህመምና ስቃይ።

በዚህ ህመም ለሚሰቃዩ አላህ ጤናቸውን ይመልስላቸው!

አንተ ግን ለተሰጠህ ጤና ለአፍታ ፈጣሪህን አታመሰግነውም!!
አልሃምዱሊላህ በል ፤ እንበል🙏🙏
#copy
@ethio_danish
አንዴ ብቻ በሰዎች ላይ ድንበር
ስታልፍባቸው ሁሌም ሊቀጡህ
ይፈልጋሉ አላህ ግን ሁሌም ድንበር
አልፈህበት እራሱ ይቅር ብሎህ
በጀነት ውስጥ ልያኖርህ ይፈልጋል
አልሀምዱሊላህ ያንተ ተገዢ ስላረከኝ...
@ethio_danish
@ethio_danish
🍁ተቀባይነት ያላቸው ዱኣዎች🌙

🌺የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል ፦ሦስት ዱዓዎች ተቀባይነት አላቸው።🌙
@ethio_danish
🌙ጾመኛ የሚያደረገው ዱዓ፤
🍂ተበዳይ የሚያደርገው ዱዓ፤
🍇መንገደኛ የሚያደርገው ዱዓ።
@ethio_danish
🍁 አልባኒ ሰሒህ ብለውታል ።
📚ሰሒህ አልጃሚዕ (3030)📚
@ethio_danish
#ምን_ተይዞ⁉️
.
.
"ለምን አታገባም?"
"ምን ተይዞ?"
.
ይህ የሁሉም ላጤ ምላሽ ነው። እኔ ምለው ግን ለትዳር ሲሆን የያዝነው ነገር የሚያሳስበንን ያህል ለአኼራው ጉዞ ቢያሳስበን ምናለ?
ምናለ "ምን ተይዞ አላህ ፊት ይቀረባል?" ብለን ቢጨንቀን?🤔
#Join
@ethio_danish
Channel photo updated
☞ከጓደኛ ምርጡ ማነው? ተብለው ሲጠየቁ
👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ በማለት መለሱ "አላህን እንድትፈራ የሚያስታውስህ መልካም ሲሰራ ስታየው ተግባሩን የምትከተል ለችግርህ
ስትጠራው የሚደርስልህ ነው አሉ አላህ ጥሩ ጥሩ ጓደኞችን ያብዛልን።
@ethio_danish
@ethio_danish
መልካም ጓደኛ የጭንቅ ቀን ጥላ ነው !!!
ልክ እንደኔ ጓደኛ!😘😍


❤️❤️❤️
❤️❤️
❤️


አላህ ሷሊህ ጓደኞቻችንን ይጠብቅልን ለሌለው አላህ ይወፍቀው!! 🙏 አላሁመ አሚን !!
@ethio_Danish
@ethio_Danish
@ethio_Danish
...ጓደኝነት...

አንድ ሰው የልብ ጉዋደኛዬ ነው ስንል . . .

➥ እኛ ለምንገባበት፣ ለሚደርስብን ነገር በሙሉ በቻለው አቅም ከጎናችን የሚቆም፣

➥ሚስጥራችን ሚስጥሩ የሆነ፣ ገበናችንን የሚደብቅልን፣

➥ በደስታም ሆነ በሀዘን ሰአት ከጎናችን በመሆን ጋሻ ከለላ የሚሰጠን ለችግራችን መፍትሄ መንገድ የሚያበጅ ወይም ራሱ መፍትሄውን ሆኖ የሚገኝ፣
@ethio_danish
➥ከጎናችን የሚሆን ስንወድቅ ሚያነሳ፣ ስናለቅስ እንባችንን የሚያብስ፣ የደስታችን ምንጭ፣ የጎደለንን ሚያሟላ ክፍተታችንን የሚደፍን፣

➥ስለኛ ራሱን እስከመሰዋትነት ለመክፈል የተዘጋጀ እና በእኛ ላይ ያለው እምነቱ እጅጉን የጠነከረ፣

➥ስንሳሳት ሚያርመን ፣እንድንበረታ የሚያደርገን አለኝታነቱን የሚያረጋግጥልን . . . ወ ዘ ተ
እነዚህ በዋናነት ተጠቀሱ እንጂ መሰል ነገሮችን የሚያደርግ በህይወታችን ላይ ለውጥ ማምጣት የሚችል ያ ሰው እውነት ጉዋደኛችን ነው፡፡

https://t.me/ethio_danish
Forwarded from ዳኒሽ (HIKMA) (Ⓐⓗⓑⓐⓑ Ⓐⓚⓜⓔⓛ)
▪️ጁሙዓ ነው ፤ ሰለዋት እናብዛ

🔻የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ በኔ ላይ አንድ ሰለዋትን ያወረደ ሰው ፤ አላህ በሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድበታል። ]
. (ሙስሊም ዘግቦታል).

اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد.
የዛሬው ጁምዓ አላህ ለጠበቀን ብቻ ደስ የሚል ተስፋ ይሆንልናል ዱሃ በማድረጋቹ አትርሱ የሚያምር ልብስ ይለበስ
አንዴ አንድ ሰው የሆነ ሜሴጅ እያነበበ እያለ
_🙏___
"ሱብሃንአላህ" ....አለ
ወደታች ተመለከተና
"አልሃምዱሊላህ".... አለ ማንበቡን ቀጠለ
_🙏___
"ላ ኢላሃ ኢለላህ" እንዳለ
የሆነ ጥሩ ስሜት ተሰማው እናም
"አላሁአክበር" አለ
ከዛ
"አስተግፊሩላህ"
"አስተግፊሩላህ"
"አስተግፊሩላህ"
_🙏____
የሚለውን አስከተለ በስተመጨረሻ
የነብዩ ሙሃመድን ስም አነበበና
"ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም" አለ
__🙏_____
ይሄን በማድረጉም ከአላህ ትልቅ ሽልማትን ተጎናፀፈ
__🙏_____
ይህ ሰው ማን እንደነበር ታውቃለህ
#አንተ_ነህ
#አንቺ _ነሽ

#ተጨማሪ_ኢስላማዊ_እውቀቶችን_ከፈለጉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@ethio_danish
@ethio_danish
@ethio_danish
#ረመዳን😍


ረመዳን~ቁርአን የወረደበት ወር

ረመዳን~የጀነት በሮች የሚከፈቱበት
የጀሀነም በሮች የሚዘጉበት ወር

ረመዳን~ሰይጣኖች የሚታሰሩበት ወር
ረመዳን~ከ1ሺህ ወር የምትበልጥ ሌሊት
ያለበት ወር

ረመዳን~ከምንጊዜውም በበለጠ ዚክርና
ቁርአን የሚቀራበት ወር

ረመዳን~'ሱንና' የሆኑ ነገሮች 'የፈርድ'
ግዴታ ደረጃ የሚሆኑበት _ዑምራ
መስራት እንደ ሀጅ የሚቆጠርበት ወር
ረመዳን~አላህ ለኔ ያለው ስራ ፆም
ከምንጊዜውም በበለጠ የሚከናወንበት ወር ቁርአን አንድን ባሪያ እንደሚያማልድ ፆምም አማላጅ እንደሚሆንም ተወስቷል

ረመዳን~አንድ ባሪያ አላህ ከፈቀደለት
ነገሮች ራሱን በማቀብ አላህን ፍራቻ
'ተቅዋ' የሚያገኝበት ወር

ረመዳን~ምንዳቸው ክፍያቸው ገደብ
ከሌላቸው ሰራዎች መካከል አንዱ
የሆነው ፆም; ወር ሙሉ የሚከናወንበት

═════ ═════
• እነዚህና ሌሎች መልካም ነገሮች
የሚገኝበት ወር በመሆኑ የአላህ መልክተኛ
ﷺ ጅብሪል ዐለይሂሰላም መጥቶ [አንድ ባሪያ የረመዳንን ወር አግኝቶ ወንጀሉን
ሳይማር ረመዳን የወጣበት እድለ-ቢስ ይሁን አሚን በል ሲላቸው ᐸአሚን>
ብለዋል
•••••••••••

አላህ በዚህ በተከበረ ወር መልካም ነገር ከሚሸምቱና ከእሳት ነፃ ከሚላቸው
ያድርገን !,,, ኣሚን
‍ የፆም ህግጋት
#ክፍል_1፦የፆም ግዴታዋች

https://t.me/Ethio_Danish
የፆም ግዴታዋች ሁለት ናቸው ።እነሱም፦
1.ኒያማድረግ፦ስፍራውም ልብ ነው፤ከአንደበት መውጣቱ ግዴታ አይደለም።ለእያንዳንዱ የረመዳን ቀን ኒያን ለሊት ማድረግ ግዴታ ነው።ፆም ያለንያ ትክክል እይሆንም።መደረግ ያለበት ከማፍጠርያ ሰዓትጀምሮ ፈጅር እስኪወጣ ድረስ ነው።በልቡ
"#ነወይቱ_ሲያመ_የውሚ_ገዲን_ሚን ሻህሪ_ረመዳን_ይላል።"
ትርጉም፦ᐸᐸከረመዳን ወር የሆነውን የነገውን እለት ለመፆም ኒያ አደረጋለሁ።>>
©.በለሊት ማድረግ ግዴታ የሚሆነው በፈርድ ፆም ሲሆን ፤የሱና ፆም ከሆነየዙህር ሶላት ወቅት ከመግባቱ በፊት ባለውጊዜ ማድረግ ይቻላል።
የወር አበባ ወይም የኒፋስ(የወሊድ) ደምበፆም ለሊት የቆመላት ሴት ባትታጠብም ቀጣዩን ቀን ለመፆም መነየት አለባት። ምክንያቱም ትጥበት ለሰላት እንጂ ለፆም ትክክለኛነት ቅድመ ሁኔታ (ሸርጥ) አይደለም።
ኒያ ካደረጉ በኋላ መብላት ፤የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ ከፈጅር በፊት እስከሆነ ድረስ ፆሙን አይጎዳውም።በሻፊዒ መዝሀብ ሌሊት ኒያ ሳያደርግ ተኝቶ ከፈጅር ቡሀላ የነቃ ሰው ፆሙን ከሚያበላሹ ነገሮች ታቅቦ መዋልና ቀዳእ መክፈል ይኖርበታል።
#ይቀጥላል

ለረመዳን ደርሰው ከሚፆሙት አላህ ያድርገን🤲🏻🤲🏻

#ክፍል_1፦የፆም ግዴታዋች

https://t.me/Ethio_Danish
የፆም ግዴታዋች ሁለት ናቸው ።እነሱም፦
1.ኒያማድረግ፦ስፍራውም ልብ ነው፤ከአንደበት መውጣቱ ግዴታ አይደለም።ለእያንዳንዱ የረመዳን ቀን ኒያን ለሊት ማድረግ ግዴታ ነው።ፆም ያለንያ ትክክል እይሆንም።መደረግ ያለበት ከማፍጠርያ ሰዓትጀምሮ ፈጅር እስኪወጣ ድረስ ነው።በልቡ
"#ነወይቱ_ሲያመ_የውሚ_ገዲን_ሚን ሻህሪ_ረመዳን_ይላል።"
ትርጉም፦ᐸᐸከረመዳን ወር የሆነውን የነገውን እለት ለመፆም ኒያ አደረጋለሁ።>>
©.በለሊት ማድረግ ግዴታ የሚሆነው በፈርድ ፆም ሲሆን ፤የሱና ፆም ከሆነየዙህር ሶላት ወቅት ከመግባቱ በፊት ባለውጊዜ ማድረግ ይቻላል።
የወር አበባ ወይም የኒፋስ(የወሊድ) ደምበፆም ለሊት የቆመላት ሴት ባትታጠብም ቀጣዩን ቀን ለመፆም መነየት አለባት። ምክንያቱም ትጥበት ለሰላት እንጂ ለፆም ትክክለኛነት ቅድመ ሁኔታ (ሸርጥ) አይደለም።
ኒያ ካደረጉ በኋላ መብላት ፤የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ ከፈጅር በፊት እስከሆነ ድረስ ፆሙን አይጎዳውም።በሻፊዒ መዝሀብ ሌሊት ኒያ ሳያደርግ ተኝቶ ከፈጅር ቡሀላ የነቃ ሰው ፆሙን ከሚያበላሹ ነገሮች ታቅቦ መዋልና ቀዳእ መክፈል ይኖርበታል።
#ይቀጥላል

ለረመዳን ደርሰው ከሚፆሙት አላህ ያድርገን🤲🏻
https://t.me/Ethio_Danish
👉 ሽርክ ሲያሰጋዎ የሚባል ዱዓ
@ethio_Danish
اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَعُوْذُ بِكَ أَنْ أُشْرِكَ بِكَ وَأَنَا أَعْلَمُ، وَأَسْتَغْفِرُكَ لِمَا لاَ أَعْلَمُ

‘አልሏሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ አን ኡሽሪከ ቢከ ወአን አዕለሙ፣ ወአስተግፊሩከ ሊማላ አዕለሙ
#ትርጉም
.አላህ ሆይ! እያወቅኩ በአንተ ላይ ከማሻረክ በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ሳላውቅ ለምፈፅመው የሽርክ ተግባር ምህረትህን እጠይቅሃለሁ፡፡
@ethio_Danish
@ethio_Danish
👌
"ጥሩ የሆኑ ከአላህ ጋር እንድትቃረብ የሚያነሳሱ ጓደኞች ማግኘት ካልቻልክ ፤ቢያንስ ከአላህ የሚያርቁ መጥፎ ጓደኞችን መራቅ ይገባሃል"።

@ethio_danish
@ethio_danish